Get Mystery Box with random crypto!

ሃፍረት አይሰራም! ለምትወደው ነገር ሃፍረት ፣ እፍረት ፣ ይሉኝታ ብሎ ነገር የለም ። በምት | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ሃፍረት አይሰራም!

ለምትወደው ነገር ሃፍረት ፣ እፍረት ፣ ይሉኝታ ብሎ ነገር የለም ። በምትኩ ግን ስረዓት አለ ፣ ምግባር አለ ፣ ቅድመተከተል አለ ። ማድረግ የምትፈልገውን ለማድረግ ሃፍረት ከያዘህና የምትሸማቀቅ ከሆነ መቼም ሃሳብህን ማሳካትና መኖር አትችልም ። በሃፍረት ውስጥ ቀና ማለት የለም ፤ እራስን መግለፅ አይቻልም ፤ እንዳሰቡት ፣ እንዳቀዱት መጓዝ እጅግ አዳጋች ነው ። ህይወት አብዝተህ ስላሽቃበጥክላት ፣ ከሚገባት በላይ ስላከበድካት ፣ እሹሩሩ ስላበዛህባት ቀላልና አስደሳች አትሆንም ። የምትይዘው የምትጨብጠው እስክታጣ የምትሸማቀቀው ለማን ብለህ ነው ? በምታገኘው በረከት የማትኮራው ፣ በማንነትህ የማትደሰተው ፣ በጥልቁ መገለጫህ በስብዕናህ የማትረካው ለምንድነው ? አንተ ሳትቀየር ነገሮች ይቀየራሉ ብለህ የምታስብ ከሆነ አትሳሳት ። በይሉኝታ እየተሰቃየህ ፣ የሰዎችን ተቀባይነት እየተመኘህ ፣ ድጋፍን እየጠበክ ፣ እራስህን እያታለልክ በፍፁም ሌላ የሚቀየር ነገር እንዳትጠብቅ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሃፍረት አይሰራም ፤ የምትፈልገውን ለማግኘት መሸማቀቀ ፣ የሚገባህን ለማሳካት ይሉኝታና ሰቀቀን ቦታ የላቸውም ። ከልብህ መፈለግህን የምታውቀው ማንንም ሳትሰማ ማድረግ ስትጀምር ነው ። በእርግጥም ያለእርሱ መኖር እንደማትችል የምታውቀው በእርሱ ጉዳይ ይሉኝታን አሽቀንጥረህ ስትጥል ነው ። እራስህን አትሸውድ ፤ ከልብህ ከፈለክ ማንም እንደማያስቆምህ በሚገባ ታውቃለህ ። ሌላ ጊዜ የሚደረደሩ ምክንያቶች ከልብህ ለምትልገው ነገር ሲሆን ትዝም አይሉህም፤ ሰዎች የሚያወሩብህ ወሬ እንዴትም ሊቆጣጠርህ አይችልም ፤ ማናቸውም የሚያደርሱብህ ጫና ከቁብ የምትቆጥረው አይሆንም ። እይታህ ሁሉ ወደፊት ነው ፤ ትኩረትህ ፍላጎትህ ላይ ብቻ ነው ። ነገሮች እንደፈለከው ላይሆኑ ይችላሉ ፣ የጠበካቸው ሰዎች ላይመጡልህ ፣ ላይረዱህ ይችላሉ የፈለከውን ነገር ግን በእጅህ ታስገባለህ ።

አዎ! ከልቡ ለሚፈልግ ሰው ሁሌም አንድ ፍላጎቱን የሚያሳካበት ፣ ግቡን የሚመታበት ፣ እቅዱን ከዳር የሚያደርስበት መንገድ አለ ። ድፍረት ፣ ወኔ ፣ ተነሳሽነት ከፍላጎቱ የሚመነጩ ብርታቶቹ ናቸው ። ቀስቃሽ ባታገኝም እራስህን በእራስህ የምትቀሰቅሰውና የምታነቃቃው ልባዊ ፍላጎት ከማይናወጥ እምነት ጋር ሲኖርህ ነው ። ትላንትህ ትርጉም አልሰጠህም ይሆናል ፣ ታሪክህ በሃፍረትና በአይናፋርነት የለሞላ ሊሆን ይችላል ። ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው ። ከትናንትህ ካልተማርክ ምኑንም ከምኑ ለታዋህደው አይቻልህም ። የባከኑ የመሰሉህ አጋጣሚዎች ባይመለሱም ዛሬ አዲሶቹ ከፊትህ ተቀምጠዋል ። በማያሳምኑ ምክንያቶች ከሚመጥንህ ደረጃ ወደኋላ አትቅር ፤ በማይገልፅህ ባህሪ ተሰናክለህ አትመለስ ፤ በማይጠቅምህ አሉታዊ ልማድ የኋሊት አትጓዝ ። ከምኞት በላይ ለሙከራ ቅረብ ፣ ፍላጎትህን ከመተንተን በሻገር አድርገህ አሳክተሀው ተገኝ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q