Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 31.66K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2023-03-26 04:35:09 ልክ ነህ!

በምታውቀው ልክ ታስባለህ ፣ በገባህ መጠን ትኖራለህ ፤ የተረዳሀውን ትተገብራለህ ። በመረጥከው ምርጫ ፣ በምትጓዝበት መንገድ ፣ በሞከርካቸው ስራዎች ፣ በምታራምደው አስተሳሰብ ፣ በምታምነው እምነት ፣ በምትታወቅበት ርዕዮት ምንም ስህተት የለብህም ። መቀበል የሚገባህንና ማመን ያለብህን ስለተቀበልክ ነፃነትህን የሚነፍግህ ፣ ጫና ውስጥ የሚከትህና የሚያዋክብህ አካል የለም ። በእራስህ መንገድ ሁሌም ልክ ነህ ፤ እንደ ደረጃህ ሁሌም በትክክለኛው መንገድ ነህ ። የሚመጥንህን የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ ፤ ከልብ የሚያስደስህን የምታውቀው አንተ ነህ ። የማስተዋል አቅምህ ፣ አረዳድህና ፍላጎትህ የማንነትህ ማሳያ ቢሆኑም እንኳን በእራስህ ልኬት ልክ መሆንህን አያጠፉትም ።

አዎ! ጀግናዬ..! ልክ ነህ! ብዙዎች ባለመኑበት በማመንህ ልክ ነህ ፤ አይሆንም ብትባልም እንደሚሆን አምነህ በመጀርህ ልክ ነህ ፤ በብዙዎች የሚጠላን ነገር ወደህ መገኘትህ ምንም ስህተት የለውም ። እያንዳንዳችን የየራሳችን ፍላጎትና ምርጫ አለን ፤ ይህም ምንም ነገር ስናደርግ በእራሳችን እይታና አረዳድ እንድናደርገው ያደርገናል ። ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ነገር መውደድ አይጠበቅበትም ፤ ሊወድም አይገባም ። እያንዳንዳችን እንደ መልክና ቁመናችን የግል አቋም ፣ አመለካከትና እይታ አለን ። ልክ ለመሆናችን የሚዳኘን ውጫዊ አካል እስከሌለ ድረስ የሚያሳምነንና በሙሉ ልባችን ተቀብለን የምናደርገው ነገር ሁሉ ልክ ነው ። በትክክለኛው መንገድ እንደምትጓዝ የምታውቀው " ምንያክል በፍላጎትህና በችሎታህ አቅጣጫ ላይ ነህ ? " የሚለውን ስታረጋግጥ ነው ።

አዎ! እኔ ብቻ ልክ ፣ እኔን ብቻ ስሙኝ ፣ የእኔ ብቻ ያዋጣል የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ። የእነርሱ ብቸኛና ትክክለኛ መንገድ ግን አንተ ጋር ሲመጣ ትክክልና አዋጭ ላይሆን ይችላል ። ማናችንም ዛሬ ላይ ከመድረሳችን በፊት በተለያየ ጎዳና ላይ ስንጓዝ ነበር ከአሁን ቦሃላም ጉዞዓችን ለየቅል መሆኑ የግድ ነው ። ህብረት ፣ አንድነት ፣ መተሳሰብ መልካም ነው ። ነገር ግን አንዱን ልክ ሌላውን ስህተት ማድረግ አይጠበቅበትም ። በሚያስማማው ትስማማለህ ፣ በሚያለያየው ትለያያለህ ። የሚያዋጣህን ካንተ በላይ ማንም አያውቅልህም ፤ የልብ መሻትህ እስከምን እንደሚገፋህ ማንም አይገነዘብም ። ያዋጣኛል በምትለው መንገድ ቀጥል ፤ ልክ እንደሆንክ የሚሰማህን ጉዳይ ከማድረግ አትቦዝን ። ተመርጦልህ በምትኖረው ሳይሆን መርጠህ በምትኖረው ህይወት እንደሚያልፍልህ እርግጠኛ ሁን ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
123 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 04:32:47 በልዩነት እመን!

በልዩነት ስታምን በልዩነት ማድረግ ትጀምራለህ ። እምነትህ ሳይሆን የእምነት ደረጃህ ለውጤት ያበቃሃል ፤ ምርጫህ ሳይሆን በምርጫህ ላይ ያለህ ፅናት ፍሬህን ያሳይሃል ። ሁሉም ሰው በፈጣሪውም ሆነ በእራሱ የሚያምን ቢመስለውም እምነቱ በልዩነት ካላቆመውና አስደናቂ ነገር ካላስደረገው ገና እምነት የሚባለው ደረጃ ላይ አልደረሰም ማለት ነው ። በህይወትሽ የሆነው ነገር በሙሉ እንደሚስተካከል የምታምኚ ከሆነ መተው ያለብሽን ለመተው ፣ መልቀቅ የሚገባሽን ለመልቀቅ ፣ መለየት ያለብሽን ለመለየት አትፍሪ ። በፍረሃት ውስጥ እምነት ሊኖር አይችልም ፤ በእምነት ውስጥም ላይሆን ይችላል የሚባል ፍረሃትና ስጋት አይኖርም ። ማመን ካለብሽ የምታምኚው ደመነፍስሽ ነው ። እምነትሽ ሙሉ ሰውነትሽን ሲያንቀሳቅስ ትመለከቺዋለሽ ። በወራጅ ወንዝ ስትወሰጂ እራስሽን ብታገኚና በመሃል የምትይዢው ዲንጋይ ቢያጋጥመሽ ደንጋዩን ይዘሽ በእርሱ ተማምነሽ አምላክሽንም አንተ አድነኝ ማለት አትችይም ። የአምላክን ፍፁም ማዳን ለመመልከትና ማመንሽን ለማረጋገጥ ድንጋዩን ለቀሽ ነፃ መሆን ይጠበቅብሻል ።

አዎ! ጀግናዬ..! በልዩነት እመን ፤ በልዩነት አድርግ ፤ በልዩነት እራስህን ስጠው ። በምንም ነገር ስኬታማና ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ ብትፈልግ ፣ ፍላጎትህ ብቻ በቂ እንዳልሆነ እወቅ ። ከፍላጎትህ ባሻገር እንደምታደርገውና እንደምታሳካው ማመን የግድ ይልሃል ። ማመንህም ከማንኛውም የእምነት ደረጃ ከፍ ያለና ወደፊት የሚነዳህ መሆን ይጠበቅበታል ። የውስጥህ ሃይል የማይናወጠው እምነትህ ፅኑ ሲሆን ነው ። ከተለመደው እምነት ከፍ ያለ እምነት ከተለመደው የላቀ ተግባር ላይ እንድትሳተፍ ያደርግሃል ። የምትችላቸው ነገሮች መጨረሻቸው የሚያምረው በፍፁም ልብህ እንደምታደርጋቸው አምነህ ስታደርጋቸው ብቻ ነው ። ለስኬትህ አንድ ምርጫ የሌለው አማራጭ ቢኖር እርሱም እምነትህ ነው ። እምነትህን በምንም ልትተካው አትችልም ፤ ለማንም በምትፈልገው ልክ ልታስረዳውም አትችልም ።

አዎ! የምፈልገው ነገር ይገባኛል ፤ የእኔ መሆን አለበት ብለህ የምታስብ ከሆነ እምነትህን ከፍ አድርግ ፤ ፅናትህን አጎልብት ፣ እስከመጨረሻው ለመታገስ እራስህን አዘጋጅ ። የቅዱስ መፅሐፍን ቃል አስታውስ "የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል እምነት ቢኖራችሁ ፣ ይህን ተራራ ፣ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወደዚያ ሂድ’ ብትሉት ይሄዳል ፤ የሚሳናችሁም ነገር አይኖርም ። " ብሏል ጌታ ለደቀመዛሙርቱ ። በማንም ከማመንህ በላይ በአምላክህ ማመን ይኖርብሃል ፤ ከሃሳብህ ጀምሮ እያንዳንዱ ተግባርህ በልዩነት ወዳንተ የመጡት በምክንያት እንሆነ ልታምን ይገባል ። በፍፁም ልብህ ያመንከውን ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትልምና የምትፈልገው ነገር ላይ ልባዊ እምነትህን አሳርፍ ፤ ባመንክበት ልክም በልዩነት ተፋለምለት ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
151 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 20:30:12
"ወደ ከፍታው በመብረር የጠላትን ፍላጎት ማክሰምና ማሸነፍ"!!!

ንስር የሚደፈረው በቁራ ብቻ ነው ፡፡ ምክንያቱም ቁራ ልኩን አያውቅም ። ይህ ቁራ ከንስሩ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ሲያበቃ የንስሩን አንገቱን ይነክሳል ። ለማሸነፍ ፣ አንገት ለማስደፋት ፣ እኔ እበልጥሃለሁ ለማለት ይሞክራል ።

ነገር ግን ንስሩ ለዚህ ተንኮለኛ መልስ አይሰጥም ። ከቁራ ጋርም አይጣላም ። ጊዜውንና ጉልበቱን አያባክንም ። ነከሰኝ ብሎ አይበሳጭም ። ያሸንፈኛል ብሎ ከቁብ አይቆጥረውም ። ይልቁንም በተረጋጋ ትዕግስቱ ታጅቦ ክንፎቹን ዘርግቶ በሰማይ ላይ ከፍ ብሎ ከፍ ወዳለው ስፍራ መውጣት ይጀምራል ። በረራውንም ወደ ከፍታው ያደርጋል ።

ቀስ በቀስ ወደ አሰበት ከፍታ ለመድረስ ይገሰግሳል ። ታዲያ በረራውን በጨመረ ቁጥር ቁራው መተንፈስ ይከብደዋል ። ንስሩ ከፍታውን እየጨመረ በሄደ ቁጥር ያ ተንኮለኛ ቁራም በኦክስጅን እጥረት ምክንያት ከንስሩ ጀርባ ላይ ተነጥሎ ይወድቃል ። ተንኮሉንም እንደያዘ ወደ ታች ይወርዳል ።

ከቁራ ጋር ጊዜ ማባከን አያስፈልግም ፡፡ ምክንያቱም የራሳቸውን የቅዠት አውሎ ንፋስ በአንተ ላይ ለማንዣበብ ይሞክራሉ ።

ዝም ብለህ ወደ ከፍታህ ብረር እንጂ ተንኮለኞች በራሳቸው ጊዜ ቦታቸውን ይይዛሉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 06:05:49 እራስህ ላይ ሰልጥን!

ህይወትህ በስሜትህ ጥላ ስር ነው። በሚፈራረቀው ሰሜትህ የህይወትን ገፅ ትመለከታለህ። እያንዳንዱ የህይወት ክስተት ላይ ያለህ ስሜት ሲቀየር ህይወትህ ይቀየራል። የስሜት ብስለትህ፣ ስሜትህ ላይ ያለህ ስልጣን እራስህ ላይ እንድትሰለጥን ያደርግሃል፤ ወደፊት እንድትጓዝ፣ ለተሻለው እንድትበቃ፣ ተምሳሌትነትህን እንድታስመሰክር፣ ግብህን እንድትመታ፣ ህልምህን እንድትኖር ያደርግሃል። ሁን ብለውም ይሁን በአጋጣሚ ለተከሰቱብህ ክስተቶች የምትሰጣቸው ምላሾችህ ላይ መጠንቀቅ ከቻልክ እራስህን መቆጣጠር አይከብድህም። እራስ ላይ መሰልጠን አንድም ብስለት ሌላም እውቀት ነው። መጥፎ ስሜትህ በነዳህ ከመነዳትህ በፊት ጉዳቱን ጠንቅቀህ እወቅ፤ የሚያስከትለውን መጥፎ ሁነት ተገንዘብ።

አዎ! ጀግናዬ..! እራስህ ላይ ሰልጥን! ስሜትህን ግዛው፤ ባህሪህን እወቀው፤ ማንነትህን ተረዳው፤ ፍላጎትህን ተገንዘብ። መኖርህ በስሜት ክልል ይገለፃል፤ ደመነፍስህ የሚታየው ወዶቹ ስሜቶችህ መልክ ነው። ምንም ነገር ይግጠምህ ስለምትሰጠው ምላሽ ደጋግመህ አስብ፤ በምንም ውስጥ ተገኝ ከደረጃህ የሚያንስ ግብረ መልስ አትመልስ። ለእራስህ ከምታደርገው ውድ ነገር አንደኛው እራስህን መግዛት፣ ስሜትህን መቆጣጠር፣ አስተውሎትህን ማስፋት፣ ጥንቃቄህን መጨመር እንደሆነ አስተውል። መጥፎ ስሜቶች መጥፎ የተባሉት በሰዓቱ በሚያመጡት መጥፎ ውጤት ወይም እያደር በሚያስከትሉት ጎጂ ነገር ነው። በሰዓቱ ችግር ባይኖርም ስሜታችን ግን የሚያረጋጋውን የትኛውንም መልስ ለመስጠት ይቸኩላል።

አዎ! ስሜቶችህ ያንተ ናቸውና ልትቆጣጠራቸው ትችላለህ፤ መነሻቸው አንተ ነህና የሚያስከትሉትን ጉዳት መቀነስ ትችላለህ። መልካምና አስደሳች በሆኑትም የማትረፉና የማደጉ ምርጫ ያንተው ነው። ገዢ ሃይል ውስጥህ አለ፤ የምታምንበት ትክክለኛ ሰሜት በማንነት መልክ ይገለጣል። በምታምነው ልክ የማስተናገድና በሚጠቅምህ መጠን ስራ ላይ ማዋሉ ያንተ ድርሻ ነው። ሙሉ ሰውነትህ እንዲደሰት በሃዘን ውስጥ እስክታል መጠበቅ አይኖርብህም፤ ሰላምን ለማጣጣም የሰላም ማጣትን ጉዳት መመልከት አይጠበቅብህም፤ በአድናቆት ለመደመም ግዴታ ትቺትና መገፋት ሊገጥምህ አይገባም። እያንዳንዱን ስሜት እንደ አመጣጡ ለማስተናገድና ለማጣጣም ውስጣዊ ንቃትና የመንፈስ ጥንካሬ ያስፈልጋል። ስሜትህን በመግዛት እራስህ ላይ ሰልጥን፤ እራስህን በቀናው መንገድ ምራው፤ በምትፈልገው ልክ ከስሜቱ በላይ እንዲሆን የምትመኘውን ሰው በእውን ሁነው።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  03:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 06:05:20 ከኋላቀር ስህተት ተቆጠብ!

የማይሳካልህ ስለፈራህ እንጂ እውነትም ስለማትችል አይደለም፤ ወደፊት የማትጓዘው በእራስህ ስለማትተማመን እንጂ አቅሙ አንሶህ አይደለም፤ ስምህን በጥሩ የማታስነሳው በእርግጥም መጥፎ ስራ ስለሰራህ ሳይሆን በማይመጥንህ ስፍራ ስለተገኘህ ነው። ደረጃህ በእጅህ ሆኖ ሳለ በሌሎች ደረጃ (standard) ውስጥ ለመካተት አትጣደፍ። እድገትህ ተግባራዊ የሚሆነው በዙሪያህና ባንተ ላይ ነው። በዘመናዊነት እሳቤ ሰዎችን እየሰሙ ከአላማ መሰናከል፣ ወደኋላ መመለስ፣ ማንም ከምንም ተነስቶ በሚያራምደው የወረደ አቋም ተደናቅፎ መቅረት ፈፅሞ አይቻልም። ዘመናዊነት በሃሳብም በተግባርም ነው። አንዳንዴ ጆሮ የማያስፈልጋቸው፣ ምንም ቁብነገርና ጠቃሚ ነገር የማይወጣቸው፣ ወሬያቸው በሙሉ አለመቻል፣ ደካማነትና አሉታዊነት የሆኑ ሰዎች አሉ። ለመስማት የሚቀልህን ሳይሆን ብትሰማው የሚጠቅምህንና የሚደግፍህን ንግግር ብቻ ስማ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከኋላቀር ስህተት ተቆጠብ! ሰዎች ስላንተ የሚነገግሩህን ሁሉ ማመን ኋላቀር ስህተት ነው፤ ማንም የሚሰጥህን መጥፎ ስም መቀበል ያለፈበት ስህተት ነው፤ በማትፈልገውና በማይገልፅህ የስራ ዘርፍ ስኬትን መጠበቅ ድካም ነው። ኋላቀር የተባለው ስህተት ከስህተትነትም አልፎ የሚደጋገምና ማንነትህን የሚቆጣጠር ከሆነ እራስህን መጠየቅ ያለብህ አንተ ነህ። ስህተት በስህተት ሲደገም ከውድቀት ውጪ ትርፍ የለውም። በሚሰራህ ስህተት እራስህን መገንባትና ማሻሻል እንደምትችል እወቅ። አለም አለኝ ከምትላቸው ተፀዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ አንዱ የሆነው አለማቀፍ ባለሃብቱ ዋረን ቡፌት (Warren Buffet) አብሮት የሚሰራውን ሰው የሚመርጠው በስህተቱና በውድቀቱ ልክ ነው። ቢያንስ አንዴ ካልተሳሳተ ሰው ጋር ስራ መስራት አይፈልግም። የስህተትን አስፈላጊነት በዚህ ተረዳ።

አዎ! ያልሞከረ ሰው ሊሳሳት አይችልም፤ ሊወድቅ አይችልም፤ ሊተችና የማይሆን ስም ሊሰጠው አይችልም። መደበኝነት ሲያስረሳህ ተለይተህ መታየትህ ደግሞ ታዋቂ ያደርግሃል። በተለመደው የህይወት መልልስ መጠመድህ ትኩረት ሲያሳጣህ ሁሌም በሙከራና እራስን በማብቃት ውስጥ ማለፍህ ትክረት እንድትስብ፣ አይኖችም አንተ ላይ እንዲሆኑ ያደርጋል። መፍራት ያለብህ ሞክረህ መሳሳትን ሳይሆን በኋላቀር ስህተት ታስረህ መቅረትን ነው፤ መፍራት ያለብህ በሰው እይታ ዋጋቢስና የማትረባ መባልን ሳይሆን ከአብዛኛው ሰው ጋር ተመሳስለህ እምቅ አቅምህን አሳንሰህ መቅረትህን ነው። ስህተትን ስራ ነገር ግን እንዳትደግመው፤ ከኋላቀር ስህተት ተቆጠብ፤ በመሳሳት ውስጥ ተማር፣ በውድቀትህ ላይ ተሻግረህ ከከፍታህ ድረስ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
988 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  03:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 06:04:56 አንቀሳቃሹ አንተ ነህ!

ምንም ያክል ሰዎች ቢያምኑብህ፣ ቢተማመኑብህ፣ ወደፊት ቢገፉህና ቢደግፉህ በእራስህ ካልተማመንክና እራስህን የማታበረታ ከሆነ ምንም ማምጣት አትችልም። እሳቱ ያለው አንተ ውስጥ ነው፤ ነበልባሉ የሚወጣው ካንተ ነው፤ የማያቋርጠው ልባዊ መሻት መነሻው አንተ ነህ። ሰዎች የሚያበረቱህ ሲያገኙህ ነው፤ አንተ ግን ሁሌም ከእራስህ ጋር ነህና የውስጥ ጩሀትህንና በእራስህ ላይ ያለህን ጥርጣሬ ባዳመጥክ ቁጥር ሚዛንህን ለመሳት የፈጠንክ፣ በእራስህ ለማዘን የምትቸኩል ትሆናለህ። ሞተሩ አንተ ሆነህ ምናልባትም ለመግፋት የተወሰነ ሃይል የሚጨምሩልህ ሌሎቹ ሊሆኑ ይችላሉ። በእራስህ ካመንክ፣ ሃሳብህን ምድር ላይ አውርደህ መመልከት ከቻልክ፣ ህልምህ እውን እንደሚሆን ካመንክ፣ እያንዳንዷን ጥረትህን ዋጋ ከሰጠሃት ያምታስበውን አይነት ህይወት የማትኖርበት ምንም ምክንያት አይኖርም። በማይታይ ሃሳብ የሚታይ ውጤት እንደምታመጣ አትጠራጠር።

አዎ! ጀግናዬ..! አንቀሳቃሹ አንተ ነህ! ጀማሪውም፣ አድራጊውም፣ ፈፃሚውም አንተው እራስህ ነህ። የምኑ? የራዕይህ፣ የግብህ፣ የአላማህ፣ የህልምህ። ደጋፊ ሊኖርህ ይችላል፣ ተከታይ ልታፈራ ትችላለህ፣ አድናቂዎችህ ሊበዙ ይችላሉ። አንዴ ጥፋት ብታጠፋ ወይም ብትሳሳት ግን እነዛ አብረውህ የነበሩና ሲደግፉህ፣ ሲያጨበጭቡልህ የነበሩ ሰዎች በሰዓቱ አብረውህ ስለመሆናቸው ምንም ዋስትና የለህም። መስሎህ እንጂ ዋናው ነገር የሰዎች ተቀባይነት ሳይሆን የእራስህ ተቀባይነትና በእራስመተማመን ነው። ተቀባይነትን ለማግኘት የደከምክበት ጊዜ፣ ደጋፊ በማጣትህ ያዘንክበት ወቅት፣ በሰዎች የወረደ ንግግር በእራስህ ያፈርክበት ሰዓት የሚቆጭህ ጊዜ ይመጣል። ቀና ባልክ ቁጥር የምታያቸው ሰዎች ይቀያየራሉ፤ አንተ የምታየውና የምትሰራው ግን ያው ነህ።

አዎ! በእርግጥ የህይወት አላማህን የምትኖር በምድር ላይ ነው ነገር ግን ያንተ ሃሳብ እንዲሳካና አላማህ ምድር ላይ እንዲወርድ የአለም ሰው ሁሉ ሊደግፍህና ሊያምንብህ አይገባም። ከምንም በላይ እራስህንም ሆነ ሰዎችን እንዲያምኑብህ የሚያደርጋቸው ስራህና ስራህ ነው። ሃሳብህን አድርጎ ለመገኘት በእራስህ መተማመን ይጠበቅብሃል፤ በእራስህ ለመተማመንም አድርጎ መገኘት ይኖርብሃል። ከጎንህ የሚቆም ሰው ባይኖር እንኳን እራስህን ደግፈህ ቁም፤ ብዙዎች ቢቃወሙህም በምታምንበት አቋምህ ፅና። በጉጉት የምትጠብቀውና ተስፋ ያደረከው የሰዎች ድጋፍ ያላንተ ብርታትና ጥንካሬ ምንም እንደማያመጣ እወቅ። አንተ ባላመንክበትና ምንም ስሜት በማይሰጥህ ነገር ላይ ብዙዎች ቢደግፉህና ቢያበረታቱህ እንኳን ከድካም ውጪ ትርፍ አታገኝም። ከልብህ በእራስህ እመን፤ ያመንክበትን ከማድረግ አትቦዝን፤ ከማንም በላይ ለእራስህ ታምነህ ተገኝ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
837 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 22:58:54 በህይወትህ ሁለት ነገሮችን መንከባከብ አለብህ።
#ብቻህን_ስትሆን
ብቻህን ስትሆን ሃሳብህን አስተሳሰብህ ተንከባከብ… ብዙ ሰዎች ሃሳብ አታብዛ አትተክዝ ይሉሃል አትስማቸው ህይዎትህን በራስህ መንገድ መኖር ካለብህ አእምሮህን በራስህ ሃሳብ መሞላት አለበት…

ምንም ያህል ጎበዝ ብትሆን አስተሳሰብህ ድንቅ ቢሆን ነገሮች በቦታቸው ላይ አይመጡልህ… ለምሳሌ የሆነ ሰው የሆነ ነገር ቢጠይቅህ በጠየቅህ ደቂቃ አእምሮህ መልስ አያፈልቅም process አለው ያንን process አንተ ብቻህን ልመደው አንዱን አንስተህ ሌላውን ጣል አንዱን ሃሳብ ገምብተህ ሌላውን አፍርስ የሃሳብ ድርዳራ የሃሳብ ግንባታ ከራስህ ጋር ሆነህ ተለማመድ…

ብቻህን መሆን ብቸኛ መሆን ከመሰለህ ተሸውደሃል እራስህን የምታገኘው ብቻህ ስትሆን ብቻ ነው…

ብቻህን መሆን አትፍራ መዝናናት ከራስ ጋር ሲሆን ጣዐሙ ልዩ ነው ማሰብ ከራስህ ጋር ሲሆን ጥልቅ ነው የሚያቆምህ የሚረብሽህ ተሳስተሃል ትክክል ነህ የሚልህ ሳይኖር ማሰብ ጣዐሙ ልዩ ነው…

ከራስህ ጋር ተከራከር ተሟገት አንድ የምታምንበት የራስህን ማንነት ጨምቀህ ታወጣለህ… የራስህ የማትቀይረው ማንነት ከሌለህ የሌሎች ሰዎች ሃሳብ ፌርማታ ነው የምትሆነው ተጠንቀቅ።



#ከሰው_ጋር_ስትሆን

ከሰው ጋር ስትሆን ምላስህን ቃላቶችህ ተቆጣጠር… አንዳድ ሰዎች ከሰው ፊት ሲቀርቡ ይለዋወጣሉ ያለእውቀታቸው አዋቂ ያለንፁህነታቸው ንፁህ ፃዲቅ መሆን ያበዛሉ…

እሰዎች ፊት ስትቀርብ ተረጋግተህ ውስጥህን አዳምጣህ የተነገራህን ሰምተህ የምትናገረውን መርጠህ ወደንግግርህ ስትገባ ጥሩ ቃላትን ከጥሩ አነጋገር ጋር ለሰዎች ትሰጣለህ።

የምትሽቀዳደም ለማውራት የምትጓጓ ከሆነ ግን ትሳሳታለህ ከራስህ ጋር ያልተግባባህበትን ነገር ትናገራለህ ያን አደረክ ማለት ደሞ ሰዎች ጋር ያለህን ቦታ ታጣለህ ሰዎች ጋር ያለህን ቦታ ካጣህ ደሞ ላራስህ ያለህን ትልቅ አመለካከት ታጣለህ በራስ መተማመንህ ይቀንሳል…

ለራስህ ያለህን ጥሩ አመለካከት አጣህ ማለት ደሞ ከሰው ጋር አብረህ መቆም ይከብድሃል።

አሁን አሁን ሰዉ ሁሉ የአስገራሚ ባህሪ ባለቤት እየሆነ ነው ሳይሰማህ ሳትጠይቀው የሚመልስ የሚያወራ ሰው እየበዛ…

አንዳዴ ሁለት ሰዎች እያወሩ የሚጣሉ ነው የሚመስለው እኩል ያውራሉ የጯጯሃሉ በቃ መደማመጥ መወያየት የለም ይሄን ባህሪህን ተወው።

ቃላቶችን ቆጥብ ሃሳብህን ቀምመህ መልስህን አዘጋጅ ከዚያ ታወራለህ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 14:05:26 እየኖርክ ተጎዳ!

የህይወትን ምሉዕነት ስናስብ ጉዳትና ጥቅም፣ ደስታና ሃዘን፣ ማግኘትና ማጣት፣ ህመምና ፈውስ የሚፈራረቁበት ስጦታችን እንደሆነ እናስተውላለን። አንዳንዴ ባሉበት መቀመጥ፣ ምንም ነገር ለመለወጥ አለመሞከር፣ እዛው በእዛው የሆነ ህይወት መኖር በእራሱ ትርፍ አልባ ጉዳት አለው። አዲስ ነገር ባለመሞከር ውስጥ ትምህርት የለም፣ እውቀት የለም፣ ለውጥ የለም፣ እድገት የለም፣ ብርታት ጥንካሬ የለም። እራስህን መፈተን ካልቻልክ የህይወት አሰልቺነትና ያንተ መካከለኛነት እንደቀጠለ ነው። መኖር ጉዳት ካለው፣ በህይወትህ ውስጥ ለብዙ ፈተናና ችግሮች ከተጋለጥክ በመኖር ውስጥ ተጎዳ፤ በፈተና ውስጥ ህይወትን አጣጥም፤ በመልቀቅ ውስጥ ሌላውን የተሻለ ነገር ጨብጥ፤ ትርፍ አልባውን ትተህ ጠቃሚውንና ትርፋማውን ያዝ።

አዎ! ጀግናዬ..! እየኖርክ ተጎዳ! እያተረፍክ ታመም፣ እያገኘህ ተገፋ፣ እየተጠቀምክ፣ እየተደሰትክ ወድቀህ ተነሳ። በፈለከው መንገድ መኖር ስትፍክ፣ የመረጥከውን ማግኘትና ማሳካት ስትፈልግ ወደድክም ጠላህም በሰዎች ትገፋለህ፣ ስራህን ታጣለህ፣ በማጣት ውስጥ ታልፋለህ፣ በደል ይደርስብሃል፣ አጣብቂኝ ውስጥ ትገባለህ፣ ትጨነቃለህ፣ ትከዳለህ፣ ጥላቻ ይገጥምሃል። ነገር ግን ከዚህ ውጪ የመቀየርና የማደግ መንገድህ እጅግ ጠባብ ነው። መኖር ማለት ሰውን ተደግፎ፣ በእራስ ምንም ነገር ማድረግ ሳይችሉ በጥበቃና በምሬት ብቻ መቆየት ማለት አይደለም። በመኖር ውስጥ የግል ፍላጎቶች አሉህ፣ ምርጫዎችና ምኞቶች ይኖሩሃል። እነርሱን ለማግኘትና በእጅህ ለማስገባት ደግሞ ጉዳት የሌለው የተመቻቸ መንገድ የለም። ቢያንስ እንቅልፍህን ማጣትህ አይቀርም፣ በሰዎች መተቸትህ የግድ ነው፣ ሃላፊነትን መውሰድህ፣ ከሌሎች ተለይተህ መታየትህ፣ የልዩነትን ጫናዎች መቀበልህ ግዴታ ነው።

አዎ! በሙከራ ውስጥ ያለውን ህመም ለመኖር ተጠቀመው፤ ጠቃሚ ልማድ በማዳበር ውስጥ ያለው ፈተና ስሜት እንዲሰጥህ፣ ህይወትህን እንዲቀይር አድርገው። ተለይቶ በመታየት ውስጥ የመገፋትና የመገለል ጉዳት ይኖራል።  ህመሙ ግን ለመኖር ነው፤ ጉዳቱ እራስን ፈልጎ ለማግኘት፣ እራስን ለመሆንና ለመቻል ነው፤ ለመለወጥና ለማደግ ነው፤ ፈተናው ህይወትን ሙሉ ለማድረግ ነው። በመከዳት ውስጥ ያላለፈ የመታመን ዋጋ ብዙ ላይገባው ይችላል፣ ጥላቻን ያልቀመሰ የፍቅር ዋጋ ሊያንስበት ይችላል፣ በማጣት ያልተፈተነ የማግኘት ውድነት ላይገባው ይችላል። ከባድ አጋጣሚዎች ሁሌም ለመልካሙና አስደሳቹ መንገድ በር ከፋች ናቸው። የተሟላውን የህይወትን ስሜት ለማግኘት በጉዳት ውስጥ እለፍ፣ ፈተናን ምረጥ፣ አደጋን ተፋለም፣ ችግርን አትፍራ። ከማጣት አትርፍ፤ በመጎዳት ውስጥ የህይወት አላማህን ፈልገህ አግኝ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 04:00:43 ድንገት የመጣ..!

አዎ! ድንገት የመጣ ድንገት ይሔዳል፤ ጊዜ የድንገቴ አመጣጥንም ሆነ ቆይታውን የሚወስን ነው። የማናችንም ህይወት በሰዎች የተሞላ ነው፤ ምናልባትም ሰዎቹ በአጋጣሚ የሚመጡ ወይም ፈልገንና ሁን ብለን ወደ ህይወታቸውን የምናስገባቸው ይሆናሉ። የማንነታቸው ልኬት ግን ጊዜና ጊዜ ብቻ ነው። በትውውቅህ ወቅት መልዓክ የነበረ ሰው ከቆይታ ቦሃላ ወደ ሴይጣንነት እንደማይቀየር እርግጠኛ መሆን አትችልም። በክፋቱ ምክንያት የተዋወከው ሰው በጊዜ ሒደት መልካምነቱን ሊገልጥ እንደሚችል እርግጠኛ መሆን አትችልም። ሂደት አንድም ለእድገታችን ሌላም የሰዎችን ማንነት ለማወቅ ይጠቅመናል። አንዳንዴ ለእኛ ድንገት የሚመስለን እነርሱ ግን አቅደውና ፈልገው ወደ ህይወታችን የሚመጡ ሰዎች አሉ። አጋጣሚ በሚመስል ግጥምጥሞሽ ይከሰታሉ የሚፈልጉትን ሲያገኙም አጋጣሚ በሚመስል ሁኔታ ከህይወታችን ይወጣሉ። ሁሉም ምክንያት ሳለው ምክንያት እንደሌለውና ያልታሰበ ክስተት እንደሆነ ለመቀበል እንገደዳለን።

አዎ! ጀግናዬ..! ምክንያት አለው፤ አላማ አለው፤ ሊያሳካው የፈለገው ግብ ነበረው። ወዳጅ መምሰልና እውነተኛ ወዳጅ መሆን ለየቅል ናቸው፤ አፍቃሪ መምሰልና ታማኝ አፍቃሪ መሆን የተለያዩ ናቸው፤ ለመወደድ ማክበርና የክብርን አስፈላጊነት አምኖ ማክበር ለየቅል ናቸው። ሌላው ቢቀር በማስመሰል ውስጥ የሚታሰብ ሌላ ፍላጎት አለ፤ በቀረቤታና በወዳጅነት ምክንያት ሊገኝ የሚታቀድ ጥቅም አለ። ድንገቴ የመሰለው ክስተት በጊዜ ሲፈተሽ ከጀርባው ጥናትና ጥቅም ፈላጊነት ተከስቶ ይገኛል። ሊሔድ የመጣ መሔዱ አይቀርም። ምናልባት የሚፈልገው ንብረትህን፣ የተለየ ጥቅምህን ወይም የግል ሚስጥርህን ሊሆን ይችላል። የሰውየውን እውነተኛ ማንነት ሳታረጋግጥ የግሌ የምትለውን ነገር የማጋራት ግዴታ እንደሌለብህ አስተውል። ለመጣ ሁሉ የግል ታሪክና ሚስጥር አይወራም፤ ማንነት ተቆርሶ አይሰጥም።

አዎ! ደንገት በሚመስል ክስተት፣ አጋጣሚ እንደሆነ በምታስበው ሁነት በፍጥነት የቀረቡህንና ወደ ህይወትህ የመጡ ሰዎችን ለመመርመር ጊዜ ውሰድ። ቆይቶ የመጣ፣ ያለምንም እውቅና የተከሰተ አይን አወጣ እንደተባለው። ምንም እንኳን የግንኙነቱ ጊዜ ብቁ ባያደርገውም ከቆይታው በላይ ቀረቤታን መፍጠር የሚፈልግ፣ አጉል ጥቅምን ለማግኘት የሚሯሯጥ፣ በጥድፊያ የተሞላ አብሮነትን የሚመርጥ ሰው በሚገባ ሊታወቅ ይገባል። እውቀተህ አንደም አንተን ከጥፋትና ጉዳት ያድንሃል፣ ሌላም የሰውየውን ትክክለኛ ማንነት ይገልጥልሃል። " ዛሬ አቀውቄው፣ ዛሬ አውቆኝ ይህን እንዴት ሊያደርግልኝ ቻለ? " የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ በጀመርክ ቁጥር ለሁኔታዎች ጊዜ መስጠትና እራስህንም መጠበቅ ትጀምራለህ። ምንም ነገር ከማድረግህ በፊት አጋጣሚ የሚመስለውን ግንኙነትህን በጊዜ ወንፊት ውስጥ ማሳለፉን እወቅበት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
24 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 04:00:19 መሔድ ይኖርብሃል!

ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀህ ላይመስልህ ይችላል ነገር ግን ከመዳረሻህ ለመድረስ መሔድ አለብህ፤ ያሰብከውን ላታገኝ ትችላለህ ነገር ግን እንቅስቃሴ ያስፈልግሃል፤ ከባቢህ መቹና ለእንቅስቃሴ የተስተካከለ ላይሆንልህ ይችላል ነገር ግን በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነህ መንቀሳቀስ፣ መሔድ፣ መጓዝ፣ ወደፊት መገስገስ ይጠበቅብሃል። የምትችለው አንድ ነገር ቢኖር ዛሬ ካለህበት ስፍራ የተወሰነ ፈቀቅ ማለት ነው፤ በየቀኑ 1% እራስህ ላይ መጨመር ነው፤ በሂደት ማንነትህን ማጎልበት ነው። አስተዋይ አዕምሮ ሁሌም መደፊት ያስባል፤ አሁን ካለበት ሁኔታ ወጥቶ የሚደርስበትን ስፍራ ያቅዳል፤ ስለሚገጥመው የወደፊት ክስተት እራሱን ያዘጋጃል፤ በምላሹ ለመጠንከርና በቂ መልስ ለመስጠት ነቅቶ ይጠብቃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ምንም ከባድ ቢሆን፣ ምንም ምቾት ባይኖረው፣ ደጋፊ ባታገኝ፣ የተለየ እርዳታ ባይደረግልህ፣ ገንዘብ ባታገኝ፣ ብርታት ባይጨመርልህ እንክን ወደፊት መጓዝ፣ መሔድ ይኖርብሃል። ጠንክረህ የምትሰራው ለመሻሻል ነው፤ ተሻሽለህ እራስህን የምታገኘውም በመጪዎቹ ጊዜያት ነው። እድሜያችን ወደኋላ ሲሔድ አቅማችን ያንሳል፣ ድካም ይመጣል፣ ዝለት ይከተላል። ስለዚህ ሩጫህ በጉብዝናህ ወቅት ነው፤ ትጋትህ በብርታትህ ጊዜ ነው። ሰውነትህ ጠንካራ በሆነ ሰዓት በተስፋ ትሞላለህ፣ በትንሽ ነገር ትነቃቃለህ፣ የምታየውና የሚደርስብህ ነገር ብርታትና ድጋፍ ይሆንሃል። እውቀትን እንደ እውቀት፣ ጥበብንም እንደ ጥበብ በህይወትህ መተግበር ትጀምራለህ። ለእራስህ አንተ ታውቃለህ፣ እውቀትህ ደግሞ ወደፊት የሚያሻግርህና ለተሻለው መዳረሻ የሚያበቃህ ነው።

አዎ! በትንሹ በመራመድ ከሰለቸህ የህይወት አጠቅት ውጣ፤ በጥቂቱ በመንቀሳቀስ ከታከተህ አጉል ልማድ ተላቀቅ፤ በሂደት እየሞከርክ የሚገባህን ኑሮ መኖር ጀምር። በአንዴ የምታቆመው አጉል ልማድ፣ በፈለከው ሰዓት የምታወርደው የሃብት መና፣ ባሰኘህ ጊዜ የሚኖርህ ንብረት የለም። ሁሉም በሒደት ያልፋሉ፤ ሂደታቸውም ወደፊት ከማሰብ፣ እቅድ ከማውጣትና ጉዞን ከመጀመር ይመጣል። በየጊዜው እራስን በማሻሻል፣ ወደፊት በመመልከት፣ እራስን በማበርታት፣ አዳዲስ ተግባሮችን በመሞከር የሚገነባህ ልማድና የሚያኮራህ የህይወት ደረጃ ላይ መድረስህ የማይቀር ጉዳይ ነው። ቀላል ባይሆንም ስለሚያስፈልግህና ነፃ ስለሚያወጣህ ብቻ አድርገው፤ ወደፊት ተጓዝ፤ እለት እለት እደግ፣ ተሻሻል፤ እራስህን አጎልብት፣ ከፍ በል።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
27 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ