Get Mystery Box with random crypto!

መሔድ ይኖርብሃል! ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀህ ላይመስልህ ይችላል ነገር ግን ከመዳረሻህ ለመድረስ መሔድ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

መሔድ ይኖርብሃል!

ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀህ ላይመስልህ ይችላል ነገር ግን ከመዳረሻህ ለመድረስ መሔድ አለብህ፤ ያሰብከውን ላታገኝ ትችላለህ ነገር ግን እንቅስቃሴ ያስፈልግሃል፤ ከባቢህ መቹና ለእንቅስቃሴ የተስተካከለ ላይሆንልህ ይችላል ነገር ግን በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነህ መንቀሳቀስ፣ መሔድ፣ መጓዝ፣ ወደፊት መገስገስ ይጠበቅብሃል። የምትችለው አንድ ነገር ቢኖር ዛሬ ካለህበት ስፍራ የተወሰነ ፈቀቅ ማለት ነው፤ በየቀኑ 1% እራስህ ላይ መጨመር ነው፤ በሂደት ማንነትህን ማጎልበት ነው። አስተዋይ አዕምሮ ሁሌም መደፊት ያስባል፤ አሁን ካለበት ሁኔታ ወጥቶ የሚደርስበትን ስፍራ ያቅዳል፤ ስለሚገጥመው የወደፊት ክስተት እራሱን ያዘጋጃል፤ በምላሹ ለመጠንከርና በቂ መልስ ለመስጠት ነቅቶ ይጠብቃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ምንም ከባድ ቢሆን፣ ምንም ምቾት ባይኖረው፣ ደጋፊ ባታገኝ፣ የተለየ እርዳታ ባይደረግልህ፣ ገንዘብ ባታገኝ፣ ብርታት ባይጨመርልህ እንክን ወደፊት መጓዝ፣ መሔድ ይኖርብሃል። ጠንክረህ የምትሰራው ለመሻሻል ነው፤ ተሻሽለህ እራስህን የምታገኘውም በመጪዎቹ ጊዜያት ነው። እድሜያችን ወደኋላ ሲሔድ አቅማችን ያንሳል፣ ድካም ይመጣል፣ ዝለት ይከተላል። ስለዚህ ሩጫህ በጉብዝናህ ወቅት ነው፤ ትጋትህ በብርታትህ ጊዜ ነው። ሰውነትህ ጠንካራ በሆነ ሰዓት በተስፋ ትሞላለህ፣ በትንሽ ነገር ትነቃቃለህ፣ የምታየውና የሚደርስብህ ነገር ብርታትና ድጋፍ ይሆንሃል። እውቀትን እንደ እውቀት፣ ጥበብንም እንደ ጥበብ በህይወትህ መተግበር ትጀምራለህ። ለእራስህ አንተ ታውቃለህ፣ እውቀትህ ደግሞ ወደፊት የሚያሻግርህና ለተሻለው መዳረሻ የሚያበቃህ ነው።

አዎ! በትንሹ በመራመድ ከሰለቸህ የህይወት አጠቅት ውጣ፤ በጥቂቱ በመንቀሳቀስ ከታከተህ አጉል ልማድ ተላቀቅ፤ በሂደት እየሞከርክ የሚገባህን ኑሮ መኖር ጀምር። በአንዴ የምታቆመው አጉል ልማድ፣ በፈለከው ሰዓት የምታወርደው የሃብት መና፣ ባሰኘህ ጊዜ የሚኖርህ ንብረት የለም። ሁሉም በሒደት ያልፋሉ፤ ሂደታቸውም ወደፊት ከማሰብ፣ እቅድ ከማውጣትና ጉዞን ከመጀመር ይመጣል። በየጊዜው እራስን በማሻሻል፣ ወደፊት በመመልከት፣ እራስን በማበርታት፣ አዳዲስ ተግባሮችን በመሞከር የሚገነባህ ልማድና የሚያኮራህ የህይወት ደረጃ ላይ መድረስህ የማይቀር ጉዳይ ነው። ቀላል ባይሆንም ስለሚያስፈልግህና ነፃ ስለሚያወጣህ ብቻ አድርገው፤ ወደፊት ተጓዝ፤ እለት እለት እደግ፣ ተሻሻል፤ እራስህን አጎልብት፣ ከፍ በል።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q