Get Mystery Box with random crypto!

በልዩነት እመን! በልዩነት ስታምን በልዩነት ማድረግ ትጀምራለህ ። እምነትህ ሳይሆን የእምነት ደረ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

በልዩነት እመን!

በልዩነት ስታምን በልዩነት ማድረግ ትጀምራለህ ። እምነትህ ሳይሆን የእምነት ደረጃህ ለውጤት ያበቃሃል ፤ ምርጫህ ሳይሆን በምርጫህ ላይ ያለህ ፅናት ፍሬህን ያሳይሃል ። ሁሉም ሰው በፈጣሪውም ሆነ በእራሱ የሚያምን ቢመስለውም እምነቱ በልዩነት ካላቆመውና አስደናቂ ነገር ካላስደረገው ገና እምነት የሚባለው ደረጃ ላይ አልደረሰም ማለት ነው ። በህይወትሽ የሆነው ነገር በሙሉ እንደሚስተካከል የምታምኚ ከሆነ መተው ያለብሽን ለመተው ፣ መልቀቅ የሚገባሽን ለመልቀቅ ፣ መለየት ያለብሽን ለመለየት አትፍሪ ። በፍረሃት ውስጥ እምነት ሊኖር አይችልም ፤ በእምነት ውስጥም ላይሆን ይችላል የሚባል ፍረሃትና ስጋት አይኖርም ። ማመን ካለብሽ የምታምኚው ደመነፍስሽ ነው ። እምነትሽ ሙሉ ሰውነትሽን ሲያንቀሳቅስ ትመለከቺዋለሽ ። በወራጅ ወንዝ ስትወሰጂ እራስሽን ብታገኚና በመሃል የምትይዢው ዲንጋይ ቢያጋጥመሽ ደንጋዩን ይዘሽ በእርሱ ተማምነሽ አምላክሽንም አንተ አድነኝ ማለት አትችይም ። የአምላክን ፍፁም ማዳን ለመመልከትና ማመንሽን ለማረጋገጥ ድንጋዩን ለቀሽ ነፃ መሆን ይጠበቅብሻል ።

አዎ! ጀግናዬ..! በልዩነት እመን ፤ በልዩነት አድርግ ፤ በልዩነት እራስህን ስጠው ። በምንም ነገር ስኬታማና ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ ብትፈልግ ፣ ፍላጎትህ ብቻ በቂ እንዳልሆነ እወቅ ። ከፍላጎትህ ባሻገር እንደምታደርገውና እንደምታሳካው ማመን የግድ ይልሃል ። ማመንህም ከማንኛውም የእምነት ደረጃ ከፍ ያለና ወደፊት የሚነዳህ መሆን ይጠበቅበታል ። የውስጥህ ሃይል የማይናወጠው እምነትህ ፅኑ ሲሆን ነው ። ከተለመደው እምነት ከፍ ያለ እምነት ከተለመደው የላቀ ተግባር ላይ እንድትሳተፍ ያደርግሃል ። የምትችላቸው ነገሮች መጨረሻቸው የሚያምረው በፍፁም ልብህ እንደምታደርጋቸው አምነህ ስታደርጋቸው ብቻ ነው ። ለስኬትህ አንድ ምርጫ የሌለው አማራጭ ቢኖር እርሱም እምነትህ ነው ። እምነትህን በምንም ልትተካው አትችልም ፤ ለማንም በምትፈልገው ልክ ልታስረዳውም አትችልም ።

አዎ! የምፈልገው ነገር ይገባኛል ፤ የእኔ መሆን አለበት ብለህ የምታስብ ከሆነ እምነትህን ከፍ አድርግ ፤ ፅናትህን አጎልብት ፣ እስከመጨረሻው ለመታገስ እራስህን አዘጋጅ ። የቅዱስ መፅሐፍን ቃል አስታውስ "የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል እምነት ቢኖራችሁ ፣ ይህን ተራራ ፣ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወደዚያ ሂድ’ ብትሉት ይሄዳል ፤ የሚሳናችሁም ነገር አይኖርም ። " ብሏል ጌታ ለደቀመዛሙርቱ ። በማንም ከማመንህ በላይ በአምላክህ ማመን ይኖርብሃል ፤ ከሃሳብህ ጀምሮ እያንዳንዱ ተግባርህ በልዩነት ወዳንተ የመጡት በምክንያት እንሆነ ልታምን ይገባል ። በፍፁም ልብህ ያመንከውን ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትልምና የምትፈልገው ነገር ላይ ልባዊ እምነትህን አሳርፍ ፤ ባመንክበት ልክም በልዩነት ተፋለምለት ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q