Get Mystery Box with random crypto!

በህይወትህ ሁለት ነገሮችን መንከባከብ አለብህ። #ብቻህን_ስትሆን ብቻህን ስትሆን ሃሳብህን አስ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

በህይወትህ ሁለት ነገሮችን መንከባከብ አለብህ።
#ብቻህን_ስትሆን
ብቻህን ስትሆን ሃሳብህን አስተሳሰብህ ተንከባከብ… ብዙ ሰዎች ሃሳብ አታብዛ አትተክዝ ይሉሃል አትስማቸው ህይዎትህን በራስህ መንገድ መኖር ካለብህ አእምሮህን በራስህ ሃሳብ መሞላት አለበት…

ምንም ያህል ጎበዝ ብትሆን አስተሳሰብህ ድንቅ ቢሆን ነገሮች በቦታቸው ላይ አይመጡልህ… ለምሳሌ የሆነ ሰው የሆነ ነገር ቢጠይቅህ በጠየቅህ ደቂቃ አእምሮህ መልስ አያፈልቅም process አለው ያንን process አንተ ብቻህን ልመደው አንዱን አንስተህ ሌላውን ጣል አንዱን ሃሳብ ገምብተህ ሌላውን አፍርስ የሃሳብ ድርዳራ የሃሳብ ግንባታ ከራስህ ጋር ሆነህ ተለማመድ…

ብቻህን መሆን ብቸኛ መሆን ከመሰለህ ተሸውደሃል እራስህን የምታገኘው ብቻህ ስትሆን ብቻ ነው…

ብቻህን መሆን አትፍራ መዝናናት ከራስ ጋር ሲሆን ጣዐሙ ልዩ ነው ማሰብ ከራስህ ጋር ሲሆን ጥልቅ ነው የሚያቆምህ የሚረብሽህ ተሳስተሃል ትክክል ነህ የሚልህ ሳይኖር ማሰብ ጣዐሙ ልዩ ነው…

ከራስህ ጋር ተከራከር ተሟገት አንድ የምታምንበት የራስህን ማንነት ጨምቀህ ታወጣለህ… የራስህ የማትቀይረው ማንነት ከሌለህ የሌሎች ሰዎች ሃሳብ ፌርማታ ነው የምትሆነው ተጠንቀቅ።



#ከሰው_ጋር_ስትሆን

ከሰው ጋር ስትሆን ምላስህን ቃላቶችህ ተቆጣጠር… አንዳድ ሰዎች ከሰው ፊት ሲቀርቡ ይለዋወጣሉ ያለእውቀታቸው አዋቂ ያለንፁህነታቸው ንፁህ ፃዲቅ መሆን ያበዛሉ…

እሰዎች ፊት ስትቀርብ ተረጋግተህ ውስጥህን አዳምጣህ የተነገራህን ሰምተህ የምትናገረውን መርጠህ ወደንግግርህ ስትገባ ጥሩ ቃላትን ከጥሩ አነጋገር ጋር ለሰዎች ትሰጣለህ።

የምትሽቀዳደም ለማውራት የምትጓጓ ከሆነ ግን ትሳሳታለህ ከራስህ ጋር ያልተግባባህበትን ነገር ትናገራለህ ያን አደረክ ማለት ደሞ ሰዎች ጋር ያለህን ቦታ ታጣለህ ሰዎች ጋር ያለህን ቦታ ካጣህ ደሞ ላራስህ ያለህን ትልቅ አመለካከት ታጣለህ በራስ መተማመንህ ይቀንሳል…

ለራስህ ያለህን ጥሩ አመለካከት አጣህ ማለት ደሞ ከሰው ጋር አብረህ መቆም ይከብድሃል።

አሁን አሁን ሰዉ ሁሉ የአስገራሚ ባህሪ ባለቤት እየሆነ ነው ሳይሰማህ ሳትጠይቀው የሚመልስ የሚያወራ ሰው እየበዛ…

አንዳዴ ሁለት ሰዎች እያወሩ የሚጣሉ ነው የሚመስለው እኩል ያውራሉ የጯጯሃሉ በቃ መደማመጥ መወያየት የለም ይሄን ባህሪህን ተወው።

ቃላቶችን ቆጥብ ሃሳብህን ቀምመህ መልስህን አዘጋጅ ከዚያ ታወራለህ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q