Get Mystery Box with random crypto!

እራስህን ፈልግ! ከምትፈልጋቸው በላይ እራስህን ፈልግ፤ ከሚያስፈልጉህ በተሻለ ለእራስህ ታስፈልጋለ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

እራስህን ፈልግ!

ከምትፈልጋቸው በላይ እራስህን ፈልግ፤ ከሚያስፈልጉህ በተሻለ ለእራስህ ታስፈልጋለህ። ከተደገፍካቸው በተሻለ አምላክህና እራስህ ላይ ተደገፍ፤ ከምትጠብቃቸው አምላክህንና እራስህን ጠብቅ። በህይወትህ ሰዎች ያስፈልጉሃል፤ ከጎንህም ሊሆኑ ይገባል። ነገር ግን አብሮነታቸው ሙሉ ማንነትህን ሊያጠፋና የነርሱ ተመፅዋችና ተረጂ ሊያደርግህ አይገባም። ከቤተሰቦችህ ውጪ ሁሌም በህይወትህ የሚከሰቱ ሰዎች ቋሚ አይደሉም። ትናንትና ዛሬ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ተገኝተሃል፤ ፍላጎትህ ለመደገፍና በእነርሱ በኩል እንዲያልፍልህ ከሆነም ከትርፍህ ይልቅ ኪሳራህ በዝቶ ታገኘዋለህ። የድጋፍህን አስተማማኝነት ካላወክ ላለመውደቅህ ምንም ዋስትና የለህም። በሰዎች የተደገፉ፣ ሰዎችን የያዙ መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደለም። አምነህ ታምነህበት ሙሉ ጊዜህን ሰተሀው ስትጠብቀው የነበረው ሰው ምናልባትም አንተንም የሚረሳበት ጊዜ ሊፈጠርብህ ይችላል።

አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን ፈልግ! አምላክህን አግኘው፤ በንፁ መንፈሱ ተመራ። አንዳንዴ ቀጥተኛ መንገዶች ብቻ ትክክል ላይሆኑ ይችላሉ፤ አቋራጭ መንገዶችም ትክክል የሚሆኑበት ጊዜ ይኖራል። ነገር ግን ዋጋቸውንና ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋዎች ስናነፃፅር አቋራጭ የተባሉትና ግልፅነት የጎደላቸው፣ ከእራሳችን በላይ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን በማመን የገባንባቸው መንገዶች አደጋቸው ይከፋል፤ ችግር አይጠፋቸውም። ሊደግፉን የሚችሉ ሰዎችን፣ ሊረዱን የሚችሉ ባለስልጣናትን፣ ሊያግዙን የሚፈልጉ የቅርብ ሰዎችን መጠበቅ፣ ከእራሳችን በላይ ሙሉ እምነታችንን እነርሱ ላይ መጣል ለተጨባጭ እርምጃ ሳይሆን ወደፊት ለማሰብ እንኳን እንድንቸገር ያደርገናል።

አዎ! ውስጥህ ለለውጥ ዝግጁ ባልሆነበት ሁኔታ በብዙ አጋጣሚዎች ብትከበብ እንኳን ለውጥ ልታመጣ አትችልም። እራስን ከመፈለግና በእራስ ከመተማመን ውጪ የተሻለ ምርጫ እንደሌለህ እመን። ባለህ ነገር ከመጀመር ውጪ ይህ ነው የምትለው በእምነት ጠብቀህ በእጅህ የሚገባ ነገር የለም። ከእነርሱ ለምታገኘው ጥቅም በቻ ብለህ ደጃቸውን የምትጠና፣ የምትማፀናቸው፣ ሙሉ ትኩረትህንና ጊዜህን እነርሱን በመጠበቅ ላይ የምታውለው ከሆነ በእነርሱ ፍቃድና ፍላጎት ላይ የመውደቅህ እድል በጣም ሰፊ ነው። የምትጠብቀው ትልቅ ነገር ካል ከአምላክህ ጠብቅ፤ በአንተ ላይ ስራውን እንዲሰራ ፍቀድ። የተመኘሀው እንዲሆንልህ ትኩረትህን ከሌሎች ላይ አንሳ፣ እራስህን በጥልቀት ተመልከት፤ ከምትችለው በላይ ሳይሆን በችሎታህ ልክ፣ እንዳቅምህ እራስህ ላይ ስራ፤ ከሌላው ስትጠብቀው የነበረውን አበርክቶት ለእራስህ አድርግ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q