Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ #ደህና_ሁኝ ወንድ ሁን ከማለት ወንድነቴን ንቀሽ፣ ቅድሚያ ወንድነትን እወቂ ጠንቅቀሽ፣ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

​​​​ #ደህና_ሁኝ
ወንድ ሁን ከማለት ወንድነቴን ንቀሽ፣
ቅድሚያ ወንድነትን እወቂ ጠንቅቀሽ፣
ባንቺ ልዩ አፈታት ባንቺ አማርኛ፣
ወንድን ወንድ የሚያሰኝ የአቅሙ መመዘኛ፣
.........................ዱላው ድብድቡ፣
......................... ዛቻ እና ስድቡ፣
ብለሽ ከደመደምሽ ካመንሺበት ደፍረሽ፣
በመታቀፍ ፋንታ መመታት ካመረሽ፣
ክፋትሽን መቻሌ ፋቅሬ ካስጨከነሽ፣
በቁልምጫው ፋንታ ስድብ ከናፈቀሽ፣
ትዕግስቴ ሴትነት ውርደት ከመሰለሽ፣
በእኔ መመዘኛ አንቺም ሴት አይደለሽ፣
ስለዚህ ደህና ሁኝ እኔም ካንቺ አልዘልቅም፣
...................ምክኒያቱም.....................፣
ሴት ስትሳም እንጂ ስትመታ አላውቅም

https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q