Get Mystery Box with random crypto!

የሚጠብቁህ ነፍሳት አሉ! ባትኖር ባለመኖር ውስጥ ምንም የለምና የምታጣው ነገር አይኖርም ፤ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የሚጠብቁህ ነፍሳት አሉ!

ባትኖር ባለመኖር ውስጥ ምንም የለምና የምታጣው ነገር አይኖርም ፤ ብዙዎች ግን ያጡሃል ፤ ብዙ ነገር ታጎድላለህ ፤ ብዙዎች ባንተ ምክንያት ይሰበራሉ ፤ አለም ካንተ የምታገኘውን ታጣለች ፤ ገፅታዋ ይቀየራል ፤ ድርሻህ ይጠፋል ። ይህም ጉድለት ብዙዎች ላይ ተፅዕኖ (impact) መፍጠር በቻልከው መጠን እየጨመረ ይሔዳል ። ካንተ በላይ በሰዎች ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖህ ስፍራህን ይወስናል ። ቀላል ህይወት አለ ፣ ከሃሳብ በላይ ለመኖርና ለመፈፀም የሚቀል በህይወት አላማ ውስጥ ሊጠቃለል የሚችል ህይወት ። ህይወትን ታግለህ አታሸንፍም ፤ በሙላት ነፃ ሆነህ ኖረሃት ግን እጅ ታሰጣታለህ ። አለም ላይ ተፅዕኖ የምትፈጥረው ተጨንቀህና ታመህ አይደለም ። የኔ የምትለውን የህይወት አላማ ማግኘት ከቻልክ ባትፈልግም ህይወትህ ቀላልና የተረጋጋ መሆኑ አይቀርም ። ምቾት የምትለውን ምህዳር በየትኛው ውጣውረድ ውስጥ ታገኘዋለህ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ልትደርስላቸው የሚባህ ፣ ካንተ እንጅ አስተዋፅዖ የሚፈልጉ ፣ ባንተ ደርጊት አምላካቸውን የሚያመሰግኑ ፣ በመኖርህ የሚደሰቱ ፣ ባንተ በኩል ህይታቸው የሚፈካ ብዙ የሚጠብቁህ ነፍሳት አሉ ። ለእራሴ ኖሬ አልፋለሁ አትበል ። ላንተ አንድ እንጀራ ትበቃሃልች ፤ ላንተ የተወሰነ ገቢ በቂህ ነው ። ነገር ግን የመኖርህ ትርጉም እርሱ አይደለም ፤ ወደ ምድር የመጣሀው ፣ በሰውነት የተፈጠርከው ለዚህ ብቻ አይደለም ። ካንተ በላይ ለሆነ ነገር እንደተፈጠርክ ማሰብ ጀምር፤ ኖሮ ከመሞት ለሚልቅ አላማ እንደመጣህ አስተውል ። በመኖር ውስጥ ብዙ ታውቃለህ ፣ ብዙ ትማራለህ ፣ ብዙ ታደርጋለህ ፣ እንዲሁም ታድጋለህ ። የስሜት እድገትህ ግን ልህቀትህን ይጨምራል ፤ አስተዋፅዖህን ያጎላል ፤ ተደራሽነትህን ያሰፋል ። ህይወት ለብቻ ሳይሆን በመደጋገፍ የምትመራ ፣ በመረዳዳት ስሜት የምትሰጥ ነች ።

አዎ! ማናችንም ትልቅ ዋጋ አለን ፤ ዋጋችንም አሳርፈን በምናልፈው አሻራ ልክ ይመዘናል ። ለእራስ ኖሮ ፣ በልቶ ጠጥቶ ፣ አግብቶ ወልዶ መኖር ለአንዳንዶቻችን ከባድ ሊመስል ይችላል ፣ ነገር ግን እርሱን ማድረግ የህይወታችን ግብ እንደሆነ ቆጥረን ለእርሱ ብቻ ስንሯሯጥ የድካም ጊዜያችን ላይ አንደርሳለን ። መኖር ከእራስ እርካታና ደስታ በላይ ነው ፤ ህይወት መጥቶ ከመሔድ የላቀ አላማ አላት ። የሚጠብቁህን ነፍሳት በፀጋህ ማገልገል ሳትችል ለእራስህም ሳትሆን ማለፍህ ሊያሳስብህ ይገባል ። በትንሽ መኖር ሳይሆን ለብዙዎች መትረፍን የህይወት ግብህ አድርግ ። እራስህን ብቻ ማስደሰትና ማሳረፍ ብቻ ሳይሆን የሚጠብቁህንም ማሳረፍ ፣ ማስደሰትና ማርካት እንዳለብህ አስተውል ። በመኖርህ ውስጥ አገልግሎትን ፣ በአገልግሎትህም ለብዙዎች መትረፍህን በተግባር አስመስክር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q