Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 31.87K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 24

2023-03-08 20:55:51 የሰዎች አቅም ይኸው ነው!
፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨
ሰዎች የሚያደርጓቸውም ሆነ የሚናገሯቸው ነገሮች እንደ አቅማቸውና እንደግንዛቤያቸው መጠን መሆኑን አትርሱ፡፡ ሰዎች አንዳንድ ተገቢ ያልሆኑ ነገር ባደረጉባችሁ ወይም በተናገሯችሁ ቁጥር ግራ እንዳንትጋቡ ከፈለጋችሁ ይህንን አመለካከት ማዳበር አስፈላጊ ነው፡፡

ሰዎቹ ከዚህ የተሻለ ቢያውቁ ወይም የተሻለ ስብእና ቢኖራቸው ኖሮ ይህንን አሁን የሚያደርጉትን ጤና ቢስ ነገር አያደርጉም ነበር፡፡ እኛም ብንሆን እኮ የተሻለ ብናውቅ ኖሮ አንዳንድ ተግባሮቻችንን እንቀይር ነበር፡፡ በሌላ አገላለጽ ማንኛውንም አይነት ክፉ ነገር የሚያደርግ ሰው ከዚያ የተሻለ ማንነትና አመለካከት ቢኖረው ኖሮ ያንን ነገር አያደርግም ነበር፡፡ ይህ ማለት የሰዎቹ አቅም ይህ ስለሆነ ዝም ብለን ራሳችንን አጋልጠን እንስጥ ማለት አይደለም፡፡ ራሳችንን ከእንደዚህ አይነት ሰዎች የመጠበቃችንና ሰዎቹን በጥበብ የመያዛችን ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አይነቱ ወደ አዎንታዊው በሚያደላ አመለካከት ሁኔታውን በማለፍ አላማችን ላይ ልናተኩር ይገባል፡፡

ክፉዎች የደረሱበት የደረጃ ከፍታ ክፋት ነው፡፡ ዘረኞች የሚያውቁት ብቸኛ እውቀት ዘረኝነት ነው፡፡ ተሳዳቢዎች የገባቸው ብቸኛ መንገድ ሰውን ማዋረድ ነው . . . ፡፡ ከዚህ የተሻለው መንገድ ቢገባቸው ኖሮ እንደነዛ የከበረ ማንነትና ግንዛቤ እንዳላቸው እንደምናከብራቸው ሰዎች ይሆኑ ነበር፡፡ ስለዚህ ሰዎች አቅማቸውንና ደረጃቸውን አሻሽለው ከዚህ ወደተሻለ ንግግርና ተግባር እንዲያድጉ እሱን ለእነሱ እንተውላቸውና እኛ የራሳችንን ዓላማ መከታተልን እንቀጥል፡፡

ሶስት መመሪያዎች

1.  ሰዎች የማይሆን ባህሪይ በገለጹ ቁጥር ስሜታዊ እየሆናችሁ ከዓላማችሁ አትገቱ፡፡

2.  ሰዎች የማይሆን ባህሪይ በገለጹ ቁጥር እነሱን ልክ ለማስገባት ስትሉ እንደነሱ ከመሆን ተጠበቁ፡፡

3.  ለእናንተ ጨዋ አመለካከትና ስነ-ምግባር የሚመጥኑ ሰዎችን በዙሪያችሁ አድርጉ፡፡
/ከደ/ር ኢዮብ ማሞ አንደበት/
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 20:53:57 ያዝ የሚያበረታህን!

ምድር ስትናወጣ፣ መልካም ዜና ሲጠፋ፣ ሰው በሰው ላይ ሲነሳ፣ ሰው ለሰው እንቅልፍ ሲያጣ ሰው ሆኖ መገኘት ነው ሰው የሚያስብለው፤ ሰው የሚያሰኘው። ደጋጎች ምድርን ቢሞሉ፣ መልካሞች አለመን ቢመሩ የቅዱስ አምላክ በረከት ምነኛ በተትረፈረፈ ነበር። ነገር ግን በመጥፎው አለም ውስጥም የእግዚአብሔር (የአላህ) በረከት አብሮን አለ፤ ሁሌም ይጠብቀናል፣ ከፊታችንም ይቀድማል። ያለ ፈጣሪ ፍቃድ ምንን ማየት ብንፈልግ ምንን እናያለን? ያለ አምላክ ይሁንታ ምን ተመኝተን ከምን እንደርሳለን? ያለ ቸርነቱ የትኛው ምግባራቸን ቀናትን ያሻግረናል? ያለ ርህራሔው የትኛው ስራቸን ከፊቱ ያቆመናል? የወደቀን ሲያነሳ አይተናል፤ እያንዳንዳችንን ኬት ወዴት እንዳመጣን እናውቃለን፤ ለማን ምንን እንዳደረገ ተረድተናል። ምንም አለም ብትከፋ፣ ፊቷን ብታዞርበት፣ ስራውን ብትዘነጋ የአምላክ ምህረትና ጥበቃ ግን ልጆቹን ሲታደግ ኖሯል፤ ወደፊትም ለፍጥረቱ የማይተኛ፣ የከፈተውን አፍ የሚዘጋ፣ የፈጠረውን ፍጥረት የሚደግፍ፣ የሚመግብ አምላክ አለህና መቼም በእርሱ ተስፋ አንዳትቆርጥ።

አዎ! ጀግናዬ..! እንደ ልቤ የተባለው ነብየ አምላክ ንጉስ ዳዊት ማንም በማያስታውሰው የብላቴናነት እድሜው እግዚአብሔር ግን ለንግስና ጠረው፤ ከበጎች የእረኝነት ስፍራ ለላቀው ክብርና ዙፋን መረጠው፤ ህዝቦቹን ይመራለት ዘንድ ሃይልና ብርታት ሆነው። አምላኩን የያዘ ሰው በተዓምራት የተሞላ ህይወት ይኖረዋል፤ በፈጣሪው የታመነ፣ እንዲረዳው፣ እንዲረዳው፣ በእርሱ ላይ ስራውን እንዲሰራ የፈቀደ ሰው በእርግጥም ህይወቱ ምሉዕ ነው። ሁሉንም ያሚያበጃጅ፣ ሁሉን የሚያዘጋጅ፣ በሁሉ ላይ አድሮ ሁሉን የሚሰራ፣ ድንቅን የሚያደርግ፣ ከብርታት በላይ የሚያበረታ አምላክ ነውና ያዝ የሚያበረታህን፤ ተደገፍ የሚደግፍህን፤ ታመን በሚታመንልህ፣ ተማመን ዳግም በሚሰራህ፣ ተደገፍ ከሞት አፋፍ በሚያነሳህ፣ አጥብቀህ ያዝ ዳግም ነፍስ የሚዘራብህን፣ እራስህን ስጥ ከትቢያ አንስቶ ለዙፋን ለሚያበቃህ።

አዎ! ማንም የአምላክን ስራ መመስከር ቢፈልግ ከእራሱ ህይወት የሚበልጥ ማስረጃና ምስክር አያገኝም። ኬት ተነስተህ የት እንደተገኘህ አንተ ታውቀዋለህ፤ የተደረገልህን፣ ያልተደረገልህን፣ የተጠበቅበትን፣ የተሰጠህለትን፣ የተመረጠልህን አንተ ታውቃለህ። በመከራ መሃል ብርታት የሚሆን ቅዱስ አምላክ ድንቅን ማድረግ ባህሪው ነውና ዘወትር በህይወታችን ድንቅን እያደረገ ለዛሬ አብቅቶናል። የሚታየን ጥቂት ነው፤ የምናውቀው እጅግ ኢምንት ነው። ብናውቀው ባናውቀው ለውጣ የማያመጣውም ሰው መሆናችን፣ ለሰውነት መመረጣችን፣ በአምሳያው መመረጣችን ነው። በአምሳሉ ከመፈጠር በላይ የሚልቅ ምን ክብርና ሞገስ ይኖር ይሆን? ለድንቅ ስራ ከመታጨት በላይ ምን ክብር ይኖር ይሆን? የተደረገልህን በፍፁም እንዳትረሳ፤ በምስጋናህ ልክ የሚጨመርልህን እንዳትዘነጋ፤ በተመረጥከው ልክ ያለፍከውን መንገድ እንዳትረሳ። ሁሌም ባለህበት ለአምላክ በረከት በርህን ክፈት፤ ለፈጣሪ ድንቅ ስራ እራስህን አዘጋጅ። በምታልፈው አንተ ውስጥ የማያልፍ ስራን የሚሰራ ፈጣሪ ብቻ እንደሆነ አስታውስ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 07:22:19 መታደስ ትችላለህ!

እንደ አዲስ ፣ ቀድሞ እንዳልነበረ ፣ ሆነህ እንደማታውቀው ፣ በማንም እንደማትታወቀው እንደሌላ ሰው በሌላ ማንነት ፣ በሌላ አመለካከት ፣ በሌላ አስተሳሰብ እንደገና መታደስና መሰራት ትችላለህ ። ያለፈው ታሪክህን እንደ አዲስ መፃፍ ፣ የተበላሸው ስብዕናህን ዳግም መገንባት ፣ ያጠፋሀውን ጥፋት ማረምና ማስተካከል ትችላለህ ። ያለፈው ማንነትህ የአሁን መገለጫህ አይደለም ፤ የቀድሞው መታወቂያህ አንተን አይደለም። በልብህ የያዝከው ፣ በውጥህ የሚመላለሰው የጥፋተኝነት ስሜት የሚከስምና ሊጠፋ የሚችል ነው ። እንደነበር ሊቀጥል የሚችለው የተኛውም ነገር ሲፈቀድለትና ሲፈቀድለት ብቻ ነው ። ህይወት አንድ ነችና ውድ ነች፤ መተኪያ የላትም ። በዚህ ህይወትም እራስህን በጥፋተኝነት ስሜት እየወቀስክ የምታጠፋው ጊዜ ሊያሳስብህ ይገባል ። የተበላሸው ቢበላሽ ስለሚስተካከለውና መታረም ስለሚችለው ነገር ማሰብ ይኖርብሃል ።

አዎ! ጀግናዬ..! መታደስ ትችላለህ! ከቀድሞ ታሪክህ ምን አተረፍክ ? ከነበርክበት የፍቅር ህይወት ምን አገኘህ ? ከከበቡህ ሰዎች ምን ተሰጠህ ? ከጓደኞችህ ምን ተማርክ ? ትናንት ከባድ ችግር ውስጥ ነበርክ ፤ ትናንት የሚያልፍ ያልመሰለህ አጣብቂኝ ውስጥ ነበርክ ። ነገር ግን የማያልፉት የለምና ያ ሁሉ ከባድ የህመም ጊዜ ፣ የስቃይ ጊዜ ፣ የመከዳት ጊዜ ፣ ፊት የመነሳት ፣ የመገፋት ፣ የመጠላት ጊዜ ሁሉ አብቅቷል ። ነገሮች ሁሉ አብቅተው አዲስ ሰው ለመሆን በቅተሃል ። የየለት እድሳትህ አዲስ ማንነትን ከተለየ ስብዕና ጋር ያድልሃል ። ለመታመምህ ምክንያት የሆነን ሰው የመተው አቅም እንዳለህ አስታውስ ። መቼም ዋጋ እንዳለህ እንዳትረሳ ፤ መቼም ብትወድቅ ዳግም መነሳት እንደምትችል እንዳትረሳ ፤ መቼም ከቁስና ከገንዘብ የላቀ ማንነት እንዳለህ እንዳትረሳ ፤ ትላንትህ ዛሬህን እንደማይወስን እወቅ ፤ ዛሬህ ነገህን እንደማይለካ ተረዳ ።

አዎ! ምቾት ያለው እድሳት የለም ፤ አልጋ በአልጋ የሆነ ለውጥ አይኖርም ። ለእራስህ እንደምታዝን እያሰብክ የሚመችህን ብቻ እየመረጥክ ልታደርግ ሰትችላለህ ፣ ነገር ግን የትናት ታሪክህን ከመድገም ሌላ ነገር አትሰራም ። እራስህን ለማድስ ፣ በአዲስ ማንነት ለመመለስ ፣ የተለየውን አንተ ለመፍጠር የሆነብህን ፣ የደረሰብህን ነገር በሙሉ መናገርና ማስረዳት አይጠበቅብህም ። የሆድህን በሆድህ ይዘህ ፣ ህመመህን እንደ ሃይል ተጠቅመህ ፣ ስቃይህን እንደተለየ ወኔ ወስደሀው አዲሱን አንተ መፍጠር ትችላለህ ። ገና ያልተፃፈባቸው ባዶ ገፆች ከፊትህ ይጠብቁሃል ። በማትወደው ማንነት አዲስ ታሪክ መፃፍ አትችልምና የምትችለውን እድሳት በቻልከው ፍጥነት ከውነው ። የማያኮራህን ትናንት እርሳው ፤ አዲስ ታሪካዊና አኩሪ ዛሬን ወደመፍጠር ተሸጋገር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.8K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 19:24:33
#እባካችሁን_ሼር_አድርጉ_ይህንን!
_______
ውድ የፌስቡክ ተከታዮች ሠላማችሁ ይብዛ
እስኪ ለዚህ ፍቅር ለሆነ ወጣት አብነት መኪና እንግዛለትና መላው ኢትዮጵያን እየዞረ ህዝባችንን ያገልግል ።

ከንግግሩ መኻል የተቀነጨበ ፥ "መኪና መግዛት አቅቶኝ አይደለም ፣ መኪና ለመግዛት ሳስብ ሳይበላ የሚያድር ቤተሰብ ትዝ ይለኛል ። እኔ እጅና እግር አለኝ እንቀሳቀሳለሁ ፤ ለማይንቀሳቀስ ሰው ዊልቸር መግዛት ትዝ ይለኛል።...ወዘተ"ስለዚህ ለዚህ ደግ ሰው ያለንን በማካፈል ለብዙዎች እንዲደርስ የድርሻችንን እንወጣ

ንግድ ባንክ አካውንቱ 1000052738378 abinet kabede
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:12:18 በወጥነት እመን!

ፈጣን ውጤት ጠባቂዎች ከስራቸው በላይ ውጤቱን በመጠበቅ ፣ ለውጡን በመናፈቅ ጊዜ ያጠፋሉ ። የወደዱት ሰው ወዲያው ምላሽ እንዲሰጣቸው ይመኛሉ ፤ የጀመሩት እንቅስቃሴ በቶሎ የሰውነት አቋማቸውን እንዲያስተካክል ይፈልጋሉ ፤ የመረጡት የስራ ዘርፍ በቀናት ወይም በወራት ውስጥ ትርፋማ እንዲያደርጋቸው ይናፍቃሉ ። ስለዚህ የማይለካና የማይመዘን ለውጥ ስላልተመለከትክ ታቆማለህ ፤ የጠበከው ውጤት ባሰብከው ጊዜ ስላልመጣ ተስፋ ትቆርጣለህ ፤ የምትናፍቀው ነገር በፈለከው ፍጥነት እጅህ ስላልገባ ተነሳሽነት ታጣለህ ። ለውጥህ ስትፈልገው የሚመጣ ሳይሆን ወጥ በሆነው ጥረትህ የሚመጣ ነው ። ፍላጎትህ እውን የሚሆነው ፣ የተመኘሀውን የምታገኘው ፣ ያሰብከው የሚከሰተው በወጥነት (consistency) ብቻ ነው ። ከችሎታዎች ሁሉ የላቀ ችሎታ ቢያስፈልግህ ፣ ከክህሎት የላቀ ክህሎት ቢያስፈልግህ እንደ ወጥነት (consistency)በጀመርከው ስራ ስኬታማ የሚያደርግህ ነገር የለም ።

አዎ! ጀግናዬ..! በወጥነት እመን!(Believe in Consistency)ከፍላጎትህ በተሻለ በማያቋርጠው ጥረትህ ተማመን ። የሚወራብህን ወሬ በስራህ አሸንፈው ። ስኬትህ ጀምሮ በመተው ሳይሆን እለት እለት እያደገ በሚመጣ ድካምና ስራ የሚገኝ ነው ። ትሰራለህ ምንም ውጤት የለም አሁንም ስራ ፤ ትደክማለህ ምንም ለውጥ የለም ድካምህን ቀጥል ፤ አብዝተህ ትጥራለህ የተለየ ነገር አልተመለከትክም ጥረትህን ቀጥል ። ብዙ ጊዜ ቶሎ የማይጠፋ ውጤት በቶሎ አይገኝም ፤ በልፋት የሚመጣ ለውጥም በቀላሉ አይጠፋም ። እየለፋህም ሳትለፋም ጊዜ እንደሚሔድ አስታውስ ፤ የማይገባህን ለማግኘት መጣርህ የቀደመው ድካምህንም ዋጋ እንዳያሳጣው ተጠንቀቅ ። ክህሎትህ በማይቋረጥ ጥረት ካልታገዘ መባከኑ ብሎም መጥፋቱ አይቀርም ።

አዎ! ትክክለኛውን አቅምህን ከማያቋርጠው ጥረትህ ቦሃላ ለካው ። ስኬትህን ከመጨረሻው በተሻለ በሂደት ውስጥ ፈልገው ። እያመመህ በምትሰራው ውስጥ ፣ እንቅልፍ እያማረህ በምትነቃው ውስጥ ፣ እያንገሸገሸህ በምትታገለው ውስጥ ፣ ትዕግስትህን እየተፈተንክ በምትታገሰው ውስጥ ፈልገው ። ምቾትን እየጠበክ ፣ ሽንፈትን እየተጠየፍክ የሚመጣ ድልም ሆነ ስኬት የለም ። በማይቋረጥ ጥረት ውስጥ ውድቀት አለ ፤ ስብራት አለ ፤ ስህተት አለ ፤ መገፋት አለ ፤ ትኩረት ማጣት አለ ፤ መሰናክል አለ። ነገር ግን በዚህ ሁሉ አልፎ ለውጤት የሚበቃ ብቻ የወጥነትን መርህ ይተገብራል ። ምንም ቢያጋጥምህ ያሰብከውን አይነት ሰው ሳትሆን እንዳታቆም ፤ ምንም ቢመጣ ከእቅዶችህ ፈቀቅ እንዳትል ። የዛሬ እንቅፋቶችህ ፀፀትን እንጂ ድልን አያጎናፅፉህም ፤ የዛሬ ሰበቦችህ ውድቀትን እንጂ ስኬትን አያመጡልህም ። ዛሬ በግልፅ በማይታየው ውጤት ሳይሆን ከድካሙ ባሻገር ውስጥህ በተቀረፀው የከፍታ ስዕል ምክንያት ጥረትህን እየጨመርክ ጉዞህን ቀጥል ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 06:16:21 ለታላቅነት ተፋለም!

ትልቁ ሃሳብህ ታላቅነት ነው ፤ ዋናው እቅድህ የተትረፈረፈ ህይወት ነው ፤ እረፍት የማይሰጥህ ግብ ከእራስ በላይ ለሌሎች መኖር መቻል ነው ። በህይወትህ ሁለት ነገር ብቻ አለህ ፣ ምክንያት ወይም ውጤት ። አስታውስ ፣ ምክንያት የትም አያደርስም ፤ ሰበብ ለምንም አያበቃም ። ውጤት ግን ትግልን ቢፈልግም መጨረሻው እረፍት ነው ፤ ውጤት በውጣውረድ ውስጥ ማለፍን ቢጠይቅም በስተመጨረሻ ግን ለእርካታ ያበቃል ። ምንም ቢፈጠር ውጤት አይዋሽም ። የስራህ ውጤት ቢዘገይም መገለጡ አይቀርም ። ያሳበብክበት ሳይሆን የሰራህበት ይከፍልሃል ፤ ምክንያት የደረደርክበት ሳይሆን ጨክነህ የተፋለምክለት ከዳር ያደርስሃል ። ውጤት ከፈለክ ቀላሉን መንገድ እርሳው ፤ በምቾት የተሞላውን ጎዳና ተወው ። ተፈላጊው ውጤት በተመረጠውና በማይጎረብጠው መንገድ አይመጣም ።

አዎ! ጀግናዬ..! ለታላቅነት ተፋለም! ላሰብከው መዳረሻ ተሟሟት ፤ ውስጥህ ለቀረው የማያባራ ምኞት መሱዓትነት ክፈል ፤ መስጠት ያለብህን ስጥ ። ወጥነት ያለው ጉዞህ መቼም ጥሎ አይጥልህም ፤ የማያባራው ጥረትህ እንዴትም ውጤት አይነሳህም ። ጊዜ ቢፈጅም መሆን ያለበት መሆኑ አይቀርም ፤ ዋጋ ቢያስከፍልም የታለመው መሳካቱ አይቀርም ፤ ቢያሳምም ፣ ቢያሰቃይም ፣ ቢያስተችም ፣ ቢያሰድብም ግቡን መምታቱ አይቀርም ። ብዙ የሚያቆሙህ መሰናክሎች አሉ ፤ እጅግ የተወሳሰቡ የአሰራር ችግሮች ይገጥሙሃል ፤ ያልታሰበው ጫና ከየአቅጣጫው ይመጣል ፤ ነገር ግን ስትጀምር ያሰብከው ታላቅነት በዚህ የሚቆም አይደለም ። አንድ ተክል የሚለካው በሚያፈራው ፍሬ ነው ፤ ያንተም ማንነት በውጤትህ ላይ የተመሰረተ ነው ። ስላሰበው የሚያወራ ሰው ሞልቷል ፤ እቅዱን የሚተነትን ፣ ህልሙን የሚያብራራ ፣ ምኞቱን የሚያውቅ ፣ ፍላጎቱን የሚገልፅ ሰው በጣም ብዙ ነው ። ልዩነቱ ግን ወሬ ውጤት አለማምጣቱ ነው ።

አዎ! ታላቅነት የወሬ ሳይሆን የልፋት ፣ የትጋት ፣ የድካምና የስራ ውጤት ነው ። የታላቅነት ፍላጎት ፣ ምኞት ፣ አምሮትና ናፍቆት ሊኖርህ ይችላል ። ነገር ግን ተግባር የሌለው ፍላጎት ፣ ጥረተ አልባ ምኞት፣ ያልተለፋበት አምሮት ምንም ነው ። ምናልባትም ቆራጥነትህ ለመካከለኛነት ወይም ለታላቅነት ፣ ለሰበበኛነት ወይም ለተዓምረኛት ፣ ለደስተኛነት ወይም ለሃዘንተኛነት ፣ ለጀግንነት ወይም ለውርደት ይሆናል ። ባለህበት መቆየትህ በእራሱ ላለህበት ሁኔታ ያለህን ቆራጥነት ያሳያል ። ለታላቅነት የቆረጠ ፣ ለተዓምረኛነት የወሰነ ፣ ደስተኝነትን የመረጠ ልብ ይኑርህ ። ከሚወራው ፍላጎትህ በላይ አተገባበሩ ላይ አተኩር ፤ ምኞትህን በስራ ግለጠው ፤ አምሮትህን በተግባር አሳይ ። ውጤት ባለው ልፋትህ ተመራ ፤ ቁብነገር ላይ ለሚያደርስህ ትጋት ቅድሚያ ስጥ ። በስራህ እደግ ፤ በተግባርህ ተቀየር ፤ በትጋትህ የታላቅነትን ጫፍ ተቆናጠጥ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.9K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 13:44:24 ህልምህን ተከተለው!

ምንም ሰበብና ምክንያት አያስፈልግህም ህልምህን ከልብህ ተከተለው ፤ ራዕይህን አሳደው ፤ ግብህን እግር በእግር ተከታተለው ። የምታቀርበው ምክንያት ጥቅም የለውም ፤ የምትደረድረው ሰበብ በምንም መንገድ ውሃ አያነሳም ። ሃሳብ እስካለህ ፣ ራዕይ እስካለህ ድረስ ማንም እርሱን ከመከተል እንዲያስቆምህ አትፍቀድ ፤ ማንም እንዴትም የተለየውን የስኬት ጉዞህን እንዲቀማህ አትፍቀድ ፤ ካመንክበት ጉዳን እንዲያስቀርህ አታድርግ ። ህልምህ ከፊትህ አለ አንተ ከኋላው ትከተለዋለህ ፤ ራዕይህ ይመራሃል አንተ በቅርብ ርቀት አብረሀው አለህ ፤ የህይወትህ አላማ እንዲሰራህና እንዲያሳድግህ ፈቅደሃል ፤ ዙሪያህ በሙሉ በህልምህ ደጋፊዎችና በአጋዦችህ ተሞልቷል ፤ የምትኖርለት አላማህ ካንተም በላይ ብዙዎችን እየጠቀመ ይገኛል ። ህልም ስላለህ የህይወት አረዳድና እይታህ ተቀይሯል ፤ ራዕይህን ስላስቀመጥክ መንገድህ ፈር ይዟል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ህልምህን ተከተለው ፤ ራዕይህን አጥብቀህ ያዝ ፤ ከግብህ ጋር ተወዳጅ ። በአምላክ መልካም ፍቃድ በህይወት በመኖርህና በምድር ላይ በመመላለስህ ብቻ የምትጠቅማቸው ፣ የምታሳርፋቸውና የምትታደጋቸው ብዙ ነፍሳት እንዳሉ አስብ ። ህልምህን መኖርህ ፣ የህይወት አላማህን ማሳካትህ ፣ ራዕይህን ከግብ ማድረስህ ጥቅሙ ላንተ ብቻ አይደለም ። ብዙዎች በድፍረትህ ይነቃቃሉ ፣ በስራህ ይማራሉ ፣ በብርታትህ ይበረታሉ ፣ በወኔህ ይጀግናሉ ፤ በውጤትህ ይደሰታሉ ፤ በአበርክቶትህ አምላክን ያመሰግናሉ ። ህልምህ ከመገልገልህ በላይ እንድታገለግል መንገዱን ይከፍታል ፤ አላማህ ከመጠቀም በተጨማሪ ብዙዎችን እንድትጠቅም ያስችልሃል ፤ ራዕይን መሰነቅህና በእርሱም ላይ መስራትህ ከእራስህ ጥንካሬ በተጨማሪ ብዙዎችን ያጠነክራል ፣ ወደፊትም ይመራቸዋል ።

አዎ! እራስህን ማወቅህ ብቻውን ውስጣዊ አቅምህን እንድትረዳ ያደረግሃል ፤ ማንነትህን መለየትህ ብቻውን የሚመጥንህንና አዋጩን መንገድ ይጠቁምሃል ። በተለመደው የህይወት መንገድ ለመኖር ብዙ እድሎች የመኖራቸውን ያክል ባልተለመደውና ህልምን ለማኖር በሚያስችለው ከባድ መንገድ ለመኖርም እድሎች አሉ ። ሰበቦች ሁሌም አሉ ፤ ምክንያቶች ተለይተውን አያውቁም ፤ የስንፈታችን መንስኤዎች ዘወትር አብረውን አሉ ። ነገር ግን ሰበብና ህልም አብረው አይሔዱም ፤ ምክንያትና ራዕይ በፍፁም አይጣጣሙም ፤ ስንፍናና ስኬት ምንም ወዳጅነት የላቸውም ። ብርታትህ አንድም ለእራስህ ፣ ሌላም ለወገንህ ነው ። ጠንክረህ አጠንክር ፣ በርትተህ አበርታ ፤ ጀግነህ አጀግን ፤ በህልምህ መንገድ ተሰርተህ ብዙዎችን ለመስራት እራስህን አዘጋጅ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 13:43:54 ሳትጀምር አትሸነፍ!

በፖውሎ ኮኤልሆ የተፃፈው ዘ-አልኬሚስት (The Alchemist) የተሰኘው ድንቅ መፅሃፍ አንድ ግሩም ቁብነገር አስፍሮልናል ። እርሱም እንዲህ ይላል ፣ " ህልማችን እንዳይሳካ የሚያደርገው አንድ ነገር ብቻ አለ ፤ እርሱም የውድቀት ፍራቻ ነው ። " ማናችንም በትልቁ ማሰብ አይከብደንም ፤ ማናችንም ስለ አስገራሚ ነገሮች ማውራትና መተንተን አይከብደንም ነገር ግን የላይሳካ ይችላል ፍረሃት ፣ የውድቀት ፍረሃት ፣ የይሉኝታ ፍረሃት ትልቅ ሆኖ ትልቅ ሊያደርገን ከሚችል ግሩም ሃሳብ ጋር እንድናረጅ ያደርገናል ። ከዚህ በፊት ሰርተህ የማታውቀውን ስራ ልትጀምር ነው ። እናም ልትከስር እንደምትችል እያሰብክ ተጨንቀሃል ? ይህን አስታውስ መክሰርም ማትረፍም በእጅህ ላይ ነው ። እርሱን የምታውቀው ደግሞ ወደስራ ከገባህ ብቻ ነው ። ፍረሃት በእራሱ የሌለውን ኪሳራ ወይም ትርፍ አምጥቶ አይሰጥህም ። የሚታይ ተግባር በሌለበት ቦታ ስለ ውድቀት ፣ ስለ ኪሳራ ፣ ስለ ውጫዊ ጫና ፣ ስለ መገለል ማውራት አይቻልም ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሳትጀምር አትሸነፍ ፤ እግርህን ሳታነሳ አትሰበር ፤ ባልሆነው አትሸበር ፤ ባልተከሰተው አትታሰር ፤ ገና ለገና ሊመጣ ይችላል በተባለ የወረደ መላምት ትልቁን ሃሳብህን አትቅበረው ። ውድቀትም ይግጠምህ ስኬት ሞክሮ ማየትን የመሰለ ነገር የለም ። ምንም ነገር ልታልም ትችላለህ መሳካቱን ልታውቅ የምትችለው ግን ስታደርገውና ስታደርገው ብቻ ነው ። ምንም ነገር ሊሆንም ላይሆንም የሚችልበት መንገድ እኩል ነው ። የህይወትህ ሚዛን እምነትና አመለካከትህ ነው ። እንዲሳካ የምትፈልገው ነገር ቢኖር በፍረሃት ውስጥም ሆነህ ማድረጉ ካለማድረግ የተሻለ ነው ። ድፍረት ፣ እድገት ፣ መነቃቃት ፣ ስኬትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በድርጊት ውስጥ ሆነህ የሚፈጠሩ ነገሮች ናቸው ። የበይ ተመልካች የምግቡን ጠዓም ሊያውቅ አይችልም ፤ በፍረሃት ታስሮ ፣ በስጋት ውስጥ ወድቆ ሳይሞክር የቀረም ሊገጥመው የሚችለውን መልካም ነገር ሊያውቅ አይችልም ።

አዎ! ትርፍና ኪሳራውን ፣ ውድቀትና ስኬቱን ፣ አድናቆትና ስድቡን ፣ ፍቅርና ጥላቸውን የምታውቀው ወደ ተግባር ከገባህ ብቻ ነው ። ውጪ ሆነህ ሲያስጨንቁህ የነበሩ ነገሮች ከጅማሬህ ቦሃላ በእርግጥም መኖራቸውን ታረጋግጣለህ ፤ ሲያስፈራህ የነበረው ውድቀት በተግባር ውስጥ ሆነህ በእውን መከሰቱን ታውቃለህ ። ያለና ተጨባጭ የሆነን ነገር መፍራት ምክንያታዊ አመክንዮ ይኖረሃል ፤ ባለሆነና ለመሆኑም ላለመሆኑም እኩል እድል ባለው ነገር ምክንያት መጨነቅና ሃሳብን ወደኋላ መግፋት ሁለተኛውን ውድቀት ያስከትላል ። ውድቀትን ፈርትህ ህልምህን ካለመኖር የላቀ ውድቀት እንደሌለ አስተውል ። ያላየሀውን የማይጠቅምና እንቅፋት የሚሆን ውድቀት ማመንህን ትተህ ያየሀውንና የምታውቀውን እውነተኛ ሃሳብና ህልምህን አምነህ ተግባርህን ጀምር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 13:43:22 መንፈሳዊነትህ ነው!

በመንፈስ ታደስ ፤ ውስጥህን አረጋጋ ፤ ነፍስህን ህያዉ ቃል መግባት ፤ ማንነትህን ለአምላክህ አቅርብ ፤ በሙሉ ልብህ እመነው ። የተስፋ ማጣትህ ሚስጥር የእምነትህ ጉድለት እንደሆነ አስተውል ፤ ደስታ የራቀህ የአምላክን አብሮነት በመዘንጋትህ እንደሆነ ተረዳ ። ፈጣሪ ሲቀድምልህና ብቻህን ስትሮጥ ትርፍህን አስተውል ። ከግዝፈቱ የተነሳ ልዩነቱ እጅግ አይሎብህ ትመለከታለህ ። እጅህ ላይ ያለውን መመልከት አቁመህ ፣ ያመለጠህን እየቆጠርክ ፣ ስለመጪው ጊዜ እየተጨነክ ፣ ከፈጣሪህ መግቦት በተለየ በዓለም ውዥንብር ተሸብረህ እየኖርክ ፣ መንፈስህን ረስተህ ፣ ነፍስህን ዘንግተህ በስጋህ ብቻ እየተመላለስክ ደስታህንም ሆነ መረጋጋትን ማግኘት አትችልም ።

አዎ! ጀግናዬ..! መረጋጋትህ ፣ ሰላምህ ፣ ደስታህ ፣ ሃሴትህ መንፈሳዊነትህ ነው ፤ በአምላክ እቅፍ መመላለስህ ነው ፤ በህያው ቃሉ መታነፅህ ፣ መገንባትህ ነው ። አለም ብዙ ጫወታ አላት ፤ አንደኛውና ዋነኛው ጫወታዋም አንተን ከአምላኳ ማራቅና በስጋው እንዲመካ ማድረግ ነው ። ፈጣሪህ አብሮህ ሳይኖር ያለህ ቢመስልህ የለህም ፤ መንፈስህ ሳይታደስ የተረጋጋህ ቢመስልህም አልተረጋጋህም ። እውነተኛውን ሰላም በፍፁም አለም ልትሰጥህ አትችልም ፤ ያፈራሀው ንበረት ፣ የፈጠርከው ወዳጅነት ፣ የምትሰራው ስራ ፣ የምታየው አጓጉዊ ቁስ ሊሰጥህ አይችልም ። እውነተኛው ሰላም ፣ መረጋጋት ፣ ፍቅር ፣ ሃሴት ያለው ቸሩ አምላክ ቤት ብቻ ነው ። ምንም ያክል በእውቀት ልትረቅ ትችላለህ ፣ ምንም ያክል በአለም ተቀባይነት ልታገኝ ትችላለህ ፣ ምንም እንኳን ተፅዕኖ ፈጣሪነትህ ጎልቶ ቢታይም መንፈስህ ባይታደስና በአምላክ ፅኑ ቃል ባይሞላ የአለም ስጦታ ሁሉ ምንም ነው ።

አዎ! መመካት አምላክ በሰጠህ ንብረት ፣ ዝናና ገንዘብ ሳይሆን ቸር አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ወይም አላህ በሰጠህ ክብርና ሞገስ ነው ፤ በማንነትህ በተገለጠው ህልውናው ነው ፤ በዘላለማዊ ፍቅሩ ነው ፤ በመልካም ፍቃዱ ነው ። ነገ የሚጠፋ ነገር አያስመካም ፤ ነገ የሚረግፍ ውበት አያኮራም ። መመካትም ሆነ መኩራት በአምላክ እቅፍ ውስጥ በመመላለስ ልክ ነው ። በመንፈሳዊነትህ አትደራደር ፤ የአምላክህን መግቦትና ማዳን ጥያቄ ውስጥ አታስገባው ፤ በፈጣሪህ እርዳታና ፈዋሽነት ቅንጣት ጥርጣሬ እንዳይኖርህ ። ከአለም ጊዜያዊ ቁስ በተሻለ በአለም ፈጣሪ ላይ ሙሉ እምነት ይኑርህ ፤ በመንፈሳዊነትህም እራስህን አንፅ ፣ ሁሉነገርህንም አስተካክል ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.9K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 05:10:32
ጀግና ጊዜ ብቻ ነው! ዛሬ መብረር ትችል ይሆናል ነገ ግን ለመራመድም የሌላ እርዳታ ሊያስፈልግህ ይችላልና ሁሌም መብረር እንዳለ ሁሉ መውደቅም አለ በል ። በሁለቱም ሁናታዎች ጥሩ መሆን ደግሞ እጅግ ጥሩው መንገድ ነው ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ