Get Mystery Box with random crypto!

ህልምህን ተከተለው! ምንም ሰበብና ምክንያት አያስፈልግህም ህልምህን ከልብህ ተከተለው ፤ ራዕ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ህልምህን ተከተለው!

ምንም ሰበብና ምክንያት አያስፈልግህም ህልምህን ከልብህ ተከተለው ፤ ራዕይህን አሳደው ፤ ግብህን እግር በእግር ተከታተለው ። የምታቀርበው ምክንያት ጥቅም የለውም ፤ የምትደረድረው ሰበብ በምንም መንገድ ውሃ አያነሳም ። ሃሳብ እስካለህ ፣ ራዕይ እስካለህ ድረስ ማንም እርሱን ከመከተል እንዲያስቆምህ አትፍቀድ ፤ ማንም እንዴትም የተለየውን የስኬት ጉዞህን እንዲቀማህ አትፍቀድ ፤ ካመንክበት ጉዳን እንዲያስቀርህ አታድርግ ። ህልምህ ከፊትህ አለ አንተ ከኋላው ትከተለዋለህ ፤ ራዕይህ ይመራሃል አንተ በቅርብ ርቀት አብረሀው አለህ ፤ የህይወትህ አላማ እንዲሰራህና እንዲያሳድግህ ፈቅደሃል ፤ ዙሪያህ በሙሉ በህልምህ ደጋፊዎችና በአጋዦችህ ተሞልቷል ፤ የምትኖርለት አላማህ ካንተም በላይ ብዙዎችን እየጠቀመ ይገኛል ። ህልም ስላለህ የህይወት አረዳድና እይታህ ተቀይሯል ፤ ራዕይህን ስላስቀመጥክ መንገድህ ፈር ይዟል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ህልምህን ተከተለው ፤ ራዕይህን አጥብቀህ ያዝ ፤ ከግብህ ጋር ተወዳጅ ። በአምላክ መልካም ፍቃድ በህይወት በመኖርህና በምድር ላይ በመመላለስህ ብቻ የምትጠቅማቸው ፣ የምታሳርፋቸውና የምትታደጋቸው ብዙ ነፍሳት እንዳሉ አስብ ። ህልምህን መኖርህ ፣ የህይወት አላማህን ማሳካትህ ፣ ራዕይህን ከግብ ማድረስህ ጥቅሙ ላንተ ብቻ አይደለም ። ብዙዎች በድፍረትህ ይነቃቃሉ ፣ በስራህ ይማራሉ ፣ በብርታትህ ይበረታሉ ፣ በወኔህ ይጀግናሉ ፤ በውጤትህ ይደሰታሉ ፤ በአበርክቶትህ አምላክን ያመሰግናሉ ። ህልምህ ከመገልገልህ በላይ እንድታገለግል መንገዱን ይከፍታል ፤ አላማህ ከመጠቀም በተጨማሪ ብዙዎችን እንድትጠቅም ያስችልሃል ፤ ራዕይን መሰነቅህና በእርሱም ላይ መስራትህ ከእራስህ ጥንካሬ በተጨማሪ ብዙዎችን ያጠነክራል ፣ ወደፊትም ይመራቸዋል ።

አዎ! እራስህን ማወቅህ ብቻውን ውስጣዊ አቅምህን እንድትረዳ ያደረግሃል ፤ ማንነትህን መለየትህ ብቻውን የሚመጥንህንና አዋጩን መንገድ ይጠቁምሃል ። በተለመደው የህይወት መንገድ ለመኖር ብዙ እድሎች የመኖራቸውን ያክል ባልተለመደውና ህልምን ለማኖር በሚያስችለው ከባድ መንገድ ለመኖርም እድሎች አሉ ። ሰበቦች ሁሌም አሉ ፤ ምክንያቶች ተለይተውን አያውቁም ፤ የስንፈታችን መንስኤዎች ዘወትር አብረውን አሉ ። ነገር ግን ሰበብና ህልም አብረው አይሔዱም ፤ ምክንያትና ራዕይ በፍፁም አይጣጣሙም ፤ ስንፍናና ስኬት ምንም ወዳጅነት የላቸውም ። ብርታትህ አንድም ለእራስህ ፣ ሌላም ለወገንህ ነው ። ጠንክረህ አጠንክር ፣ በርትተህ አበርታ ፤ ጀግነህ አጀግን ፤ በህልምህ መንገድ ተሰርተህ ብዙዎችን ለመስራት እራስህን አዘጋጅ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q