Get Mystery Box with random crypto!

ሳትጀምር አትሸነፍ! በፖውሎ ኮኤልሆ የተፃፈው ዘ-አልኬሚስት (The Alchemist) የተሰኘ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ሳትጀምር አትሸነፍ!

በፖውሎ ኮኤልሆ የተፃፈው ዘ-አልኬሚስት (The Alchemist) የተሰኘው ድንቅ መፅሃፍ አንድ ግሩም ቁብነገር አስፍሮልናል ። እርሱም እንዲህ ይላል ፣ " ህልማችን እንዳይሳካ የሚያደርገው አንድ ነገር ብቻ አለ ፤ እርሱም የውድቀት ፍራቻ ነው ። " ማናችንም በትልቁ ማሰብ አይከብደንም ፤ ማናችንም ስለ አስገራሚ ነገሮች ማውራትና መተንተን አይከብደንም ነገር ግን የላይሳካ ይችላል ፍረሃት ፣ የውድቀት ፍረሃት ፣ የይሉኝታ ፍረሃት ትልቅ ሆኖ ትልቅ ሊያደርገን ከሚችል ግሩም ሃሳብ ጋር እንድናረጅ ያደርገናል ። ከዚህ በፊት ሰርተህ የማታውቀውን ስራ ልትጀምር ነው ። እናም ልትከስር እንደምትችል እያሰብክ ተጨንቀሃል ? ይህን አስታውስ መክሰርም ማትረፍም በእጅህ ላይ ነው ። እርሱን የምታውቀው ደግሞ ወደስራ ከገባህ ብቻ ነው ። ፍረሃት በእራሱ የሌለውን ኪሳራ ወይም ትርፍ አምጥቶ አይሰጥህም ። የሚታይ ተግባር በሌለበት ቦታ ስለ ውድቀት ፣ ስለ ኪሳራ ፣ ስለ ውጫዊ ጫና ፣ ስለ መገለል ማውራት አይቻልም ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሳትጀምር አትሸነፍ ፤ እግርህን ሳታነሳ አትሰበር ፤ ባልሆነው አትሸበር ፤ ባልተከሰተው አትታሰር ፤ ገና ለገና ሊመጣ ይችላል በተባለ የወረደ መላምት ትልቁን ሃሳብህን አትቅበረው ። ውድቀትም ይግጠምህ ስኬት ሞክሮ ማየትን የመሰለ ነገር የለም ። ምንም ነገር ልታልም ትችላለህ መሳካቱን ልታውቅ የምትችለው ግን ስታደርገውና ስታደርገው ብቻ ነው ። ምንም ነገር ሊሆንም ላይሆንም የሚችልበት መንገድ እኩል ነው ። የህይወትህ ሚዛን እምነትና አመለካከትህ ነው ። እንዲሳካ የምትፈልገው ነገር ቢኖር በፍረሃት ውስጥም ሆነህ ማድረጉ ካለማድረግ የተሻለ ነው ። ድፍረት ፣ እድገት ፣ መነቃቃት ፣ ስኬትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በድርጊት ውስጥ ሆነህ የሚፈጠሩ ነገሮች ናቸው ። የበይ ተመልካች የምግቡን ጠዓም ሊያውቅ አይችልም ፤ በፍረሃት ታስሮ ፣ በስጋት ውስጥ ወድቆ ሳይሞክር የቀረም ሊገጥመው የሚችለውን መልካም ነገር ሊያውቅ አይችልም ።

አዎ! ትርፍና ኪሳራውን ፣ ውድቀትና ስኬቱን ፣ አድናቆትና ስድቡን ፣ ፍቅርና ጥላቸውን የምታውቀው ወደ ተግባር ከገባህ ብቻ ነው ። ውጪ ሆነህ ሲያስጨንቁህ የነበሩ ነገሮች ከጅማሬህ ቦሃላ በእርግጥም መኖራቸውን ታረጋግጣለህ ፤ ሲያስፈራህ የነበረው ውድቀት በተግባር ውስጥ ሆነህ በእውን መከሰቱን ታውቃለህ ። ያለና ተጨባጭ የሆነን ነገር መፍራት ምክንያታዊ አመክንዮ ይኖረሃል ፤ ባለሆነና ለመሆኑም ላለመሆኑም እኩል እድል ባለው ነገር ምክንያት መጨነቅና ሃሳብን ወደኋላ መግፋት ሁለተኛውን ውድቀት ያስከትላል ። ውድቀትን ፈርትህ ህልምህን ካለመኖር የላቀ ውድቀት እንደሌለ አስተውል ። ያላየሀውን የማይጠቅምና እንቅፋት የሚሆን ውድቀት ማመንህን ትተህ ያየሀውንና የምታውቀውን እውነተኛ ሃሳብና ህልምህን አምነህ ተግባርህን ጀምር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q