Get Mystery Box with random crypto!

የሰዎች አቅም ይኸው ነው! ፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨ ሰዎች የሚያደርጓቸውም ሆነ የሚናገሯ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የሰዎች አቅም ይኸው ነው!
፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨
ሰዎች የሚያደርጓቸውም ሆነ የሚናገሯቸው ነገሮች እንደ አቅማቸውና እንደግንዛቤያቸው መጠን መሆኑን አትርሱ፡፡ ሰዎች አንዳንድ ተገቢ ያልሆኑ ነገር ባደረጉባችሁ ወይም በተናገሯችሁ ቁጥር ግራ እንዳንትጋቡ ከፈለጋችሁ ይህንን አመለካከት ማዳበር አስፈላጊ ነው፡፡

ሰዎቹ ከዚህ የተሻለ ቢያውቁ ወይም የተሻለ ስብእና ቢኖራቸው ኖሮ ይህንን አሁን የሚያደርጉትን ጤና ቢስ ነገር አያደርጉም ነበር፡፡ እኛም ብንሆን እኮ የተሻለ ብናውቅ ኖሮ አንዳንድ ተግባሮቻችንን እንቀይር ነበር፡፡ በሌላ አገላለጽ ማንኛውንም አይነት ክፉ ነገር የሚያደርግ ሰው ከዚያ የተሻለ ማንነትና አመለካከት ቢኖረው ኖሮ ያንን ነገር አያደርግም ነበር፡፡ ይህ ማለት የሰዎቹ አቅም ይህ ስለሆነ ዝም ብለን ራሳችንን አጋልጠን እንስጥ ማለት አይደለም፡፡ ራሳችንን ከእንደዚህ አይነት ሰዎች የመጠበቃችንና ሰዎቹን በጥበብ የመያዛችን ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አይነቱ ወደ አዎንታዊው በሚያደላ አመለካከት ሁኔታውን በማለፍ አላማችን ላይ ልናተኩር ይገባል፡፡

ክፉዎች የደረሱበት የደረጃ ከፍታ ክፋት ነው፡፡ ዘረኞች የሚያውቁት ብቸኛ እውቀት ዘረኝነት ነው፡፡ ተሳዳቢዎች የገባቸው ብቸኛ መንገድ ሰውን ማዋረድ ነው . . . ፡፡ ከዚህ የተሻለው መንገድ ቢገባቸው ኖሮ እንደነዛ የከበረ ማንነትና ግንዛቤ እንዳላቸው እንደምናከብራቸው ሰዎች ይሆኑ ነበር፡፡ ስለዚህ ሰዎች አቅማቸውንና ደረጃቸውን አሻሽለው ከዚህ ወደተሻለ ንግግርና ተግባር እንዲያድጉ እሱን ለእነሱ እንተውላቸውና እኛ የራሳችንን ዓላማ መከታተልን እንቀጥል፡፡

ሶስት መመሪያዎች

1.  ሰዎች የማይሆን ባህሪይ በገለጹ ቁጥር ስሜታዊ እየሆናችሁ ከዓላማችሁ አትገቱ፡፡

2.  ሰዎች የማይሆን ባህሪይ በገለጹ ቁጥር እነሱን ልክ ለማስገባት ስትሉ እንደነሱ ከመሆን ተጠበቁ፡፡

3.  ለእናንተ ጨዋ አመለካከትና ስነ-ምግባር የሚመጥኑ ሰዎችን በዙሪያችሁ አድርጉ፡፡
/ከደ/ር ኢዮብ ማሞ አንደበት/
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q