Get Mystery Box with random crypto!

ክፍቱን ተመልገቺ! ባለሽበት ሁኔታ ውስጥ የተዘጋብሽ በር አንድ ቢሆን የኋላ በሩ ክፍት ነው፤ እር | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ክፍቱን ተመልገቺ!

ባለሽበት ሁኔታ ውስጥ የተዘጋብሽ በር አንድ ቢሆን የኋላ በሩ ክፍት ነው፤ እርሱም ቢዘጋ በዙ ክፍት መስኮቶች አሉ። በአንድ ሰው ብትሰበሪ በሌላ ሰው ትጠገኚያለሽ፤ አንዱ ቢገፋሽ አንዱ ያቀርብሻል። ተስፋ የሌላቸው ሁኔታዎች በተስፋ በተሞሉ ብርህ መንገዶች መተካት ይችላሉ። ጨለማ ባለበት ብረሃን የለም፤ ብረሃን ባለበትም ጨለማ አይኖርም። ፍቅርን በመረጥሽበት ቦታ ጥላቻን ማንገስ አትችይም፤ በጥላቻ ተሞልተሽም ስለፍቅር ማሰብ አትችይም። እውነት ድህነትን ከፈለግሽ የይቅርታ ልብ ይኑርሽ፤ የምርም ትክክለኛ አጋር ከፈለግሽ የቀድሞ በደልሽን ተይው፤ በቀልን እርሺው፤ ከስቃዩ ድባብ ውጪ። ስለሄደው አብዘትሽ ከማሰብ በላይ በዙሪያሽ ያለውን ድባብ ተመልከቺ። በአንድ ጉዳይ ለአመታት መጨነቅና መታወክ እንደሌለብሽ አስተውይ። በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የተለየ ምላሽ መጠበቅ እንደማይገባሽ እወቂ።

አዎ! ጀግኒት..! ክፍቱን ተመልከቺ፤ አማራጩን መንገድ ተጠቀሚ፤ የአደጋ ጊዜ መውጫውንም አስተውይው። ሁን ተብሎ ታስቦበት የተዘጋን በር ከመታገል ይልቅ በቀላሉ ሊከፈቱ የሚችሉ ወይም ከነጭራሹ ክፍት የሆኑ በሮችን መጠቀም ለውጤትም ሆነ ለፍጥነት እጅግ ጠቃሚ ነው። አንዳንዴ አንቺ መቀየር የማትችይው ነገር ላይ ተስፋ ቆሮጦ በሌላ መንገድ መሞከር ተገቢ ነው። ለመረጥሽው ሰው ምርጫው ካልሆንሽ በእርሱ ላይ ተስፋ መቁረጡ ብቸኛው መፍትሔሽ ነው፤ ስሜት በማይሰጥሽ ስራ ውስጥ ለአመታት ደስታን ማግኘት ካልቻልሽ ያለሽ አማራጭ ከጎን ሌላ ስሜት ሰጪ ስራ ማንቀሳቀስ መጀመር ነው። ህይወት ባላስፈላጊ ትግል ለማባከን እጅግ በጣም አጭር ነች፤ የተዘጋን በር ለመክፈት ጊዜ ለማባከን እጅግ ውሱን ነችና የተዘጋብሽን ትተሽ በዙሪያሽ ያሉትን ክፍት በሮች ተመልከቺ፤ በእነርሱ ተጠቀሚ።

አዎ! ጀግናዬ..! ውዱ ስጦታህ ጊዜህ እንደሆነ አስተውል፤ እርሱም ባልተገባ ነገር መባከን እንደሌለበት ተረዳ። የትኛውም ትግልህ ከትምህርት ያነሰ ነገር እንዲሰጥህ አትፍቀድ። ብትሳሳት በቶሎ ተምረህ አሰራርህን ወይም መንገድህን ቀይር፤ አንዴ ብትጎዳ ፊትህን ወደሌላ አቅጣጫ በማዞር ዙሪያህን መቃኘት ጀምር፤ ተደጋጋሚው ኪሳራህ ላመንክበት ነገር ብቻ መሆን እንዳለበት ጠንቅቀህ እወቅ። በትግል ውስጥም ብትሆን አይነተኛውን ስሜት ፈልግ። ህይወት ከአንድ በላይ በዙ በሮች፣ ብዙ አማራጮች፣ ብዙ የህይወት አቅጣጫዎች አሏትና በአንዱ አልሆነልኝ፣ አልተሳካልኝም ብለህ ወደኋላ አትመለስ። በሌላ መንገድ ሞክር፤ ሌላ መንገድ ተጠቀም፤ አማራጩን በር ተመልከት። ሃዘንህን በልኩ በማድረግ በሙከራህ ውስጥ ማደግህን ቀጥል።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q