Get Mystery Box with random crypto!

“ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሐፍን ወደ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ቀይሮ ለማቅረብ ኢቢሲ ከሰው መሆን | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

“ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሐፍን ወደ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ቀይሮ ለማቅረብ ኢቢሲ ከሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር የ41,427,600 ብር ውል ተፈራረመ።

ድራማው በአራት ምዕራፍ፣ በ48 ክፍሎች ፕሮዳክሽን ተሰርቶ ይቀርባል። በአማካይ 45 ደቂቃ ርዝማኔ ሲኖረው ለእያንዳንዱ የድራማ ክፍል (Episode) ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 863 ሺህ 75 (ስምንት መቶ ስልሳ ሦስት ሺህ ሰባ አምስት) ብር ለመክፈል ስምምነት ላይ ተደርሷል።

‘ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን’ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የድራማውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማለትም (ከክፍል1-12) የተጠናቀቁ ሥራዎችን እንዲሁም በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ (48 ክፍሎች) አጠናቅቆ ለማስረከብ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል ።