Get Mystery Box with random crypto!

ድጋሜ አታገኘውም! ተሳስተህ የምትማረውን ትምህርት ድጋሜ አትማረውም፤ ያመለጠህን ጊዜ ድጋሜ አታገ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ድጋሜ አታገኘውም!

ተሳስተህ የምትማረውን ትምህርት ድጋሜ አትማረውም፤ ያመለጠህን ጊዜ ድጋሜ አታገኘውም፤ በብዙ ጥረት የምታካብተውን ልምድ እንደገና አታገኘውም። ምድርን መሰናበቻህ ሲቀርብ ከምትነቃ አሁን በጊዜ ንቃ፤ ድጋሜ ለማታገኛቸው ስጦታዎችህ ትኩረት ስጣቸው፤ ውድነታቸውን ውድ ነገር በማድረግ ግለፅላቸው፤ ልብህን ለማሞቅ ቁጭ ብለህ መቆዘም ሳይሆን ተነስተህ የፈለከውን አድርግ። ሽልማት እያሰብክ እራስህን አታድክም፤ ቁስ ባትሸለም ውስጣዊ ሃሴትን የሚሸልምህ፣ የማያልቀውን ደስታ የሚያድልህ ተግባር ውስጥህ አለ። የምትናፍቀው ለውጥ፣ የምትመኘው ከፍታ፣ የምታስበው ስኬት በጥረትህ ልክ የሚመጣ ጉዳይ ነው። ተስፋን በብዙ ተንከባከበው፤ ለእምነትህ ድጋፍ ሁነው፤ የታላቅነት አመለካከትህን አጥብቀህ ያዘው፤ በእራስመተማመንህን ከምንም በላይ ዋጋ ስጠው፤ ዛሬህ ላይ በሚገባ ሰልጥን። ታሪክ ሆኖ በኩራት የምታወራበትን ቅፅበት አሁን መፍጠር ጀምር።

አዎ! ጀግናዬ..! ድጋሜ አታገኘውም፤ እንደገና አይመጣምና እያንዳንዱን የህይወት ስጦታህን፣ ቀንህን፣ ጤናህን፣ ሰላምህን፣ እውቀትህን፣ ጥበብህን፣ ማስተዋለህን፣ ብለሃትህን እንደ ብርቅ፣ አላቂና ውድ ነገር በአግባቡ ተጠቀመው። እንዲሁ እንደ ቀላል የሚባክን፣ ዋጋ የሌለው፣ ተስፋህን የማያጎላ፣ ለምኞትህ የማያቀርብህ ስጦታ እንደማይሰጥህ አስብ። በብረሃናማው ጊዜህ በሚገባ መኖር ከቻልክ ፀሃይህ መጥለቅ ስትጀምር፣ የድካም ዘመንህ ሲመጣ፣ ተፈጥሮ ስትሰለጥንብህ አንዳች የሚያስቆጭህ ነገር አይኖርም። የአሁኗን ቅፅበት ድጋሜ የመኖር እድል እንደማታገኝ መረዳትህ ብቻ በሙሉ ስስት እንድትጠቀማት ሊያደርግህ ይገባል።

አዎ! አስቸኳይ ሃላፊነት፣ ጊዜ የማይሰጥህ ተጠያቂነት፣ ድጋሜ የማይፈፀም ግዴታ እንዳለብህ አስታውስ። ህይወትን በሙላት የመኖር ሃላፊነት፣ መኖርህን ትርፋማ የማድረግ ግዴታ፣ ለእያንዳንዱ ቅፅበቶችህ፣ ለእያንዳንዱ ስጦታዎችህ ዋጋ የመስጠት፣ ትርጉም የመፈለግ ተጠያቂነት አለብህ። የሚጠይቅህም ሌላ ማንም ሳይሆን የእራስህ እውነተኛ ማንነት፣ ውስጥህን በሃሴት ለመሙላት፣ ከፍታህን ለማምጣት የሚታገለው ድንቁ ማንነትህ ነው። ቀላል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በየትኛውም መንገድ ሊደረግ ይገባል። መጨረሻህ ቁጪት፣ ስቃይና የልብ ስብራት እንዲሆን ካልፈለክ አሁን ነቃ በል፤ ህይወትህን ሙሉ አድርጋት፤ በእያንዳንዱ ቀናት ውስጥ በመኖርህ፣ የእራስ ፍለጋ ጉዞ ውስጥ በመሆንህ፣ እራስህን ለማሳደግ በመጣርህ በእርግጥም ኩራት ይሰማህ፤ በምርጫህና በውሳኔህ ሃሴት አድርግ፤ በማንነትህ ሁሌም ደስ ይበልህ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q