Get Mystery Box with random crypto!

የአምላክህ ልጅ ነህ! በእራስህ እንደምታፍር ይሰማሃል? ቀና ማለት ትልቅ ሸክም ሆኖብሃል? ውስጥህ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የአምላክህ ልጅ ነህ!

በእራስህ እንደምታፍር ይሰማሃል? ቀና ማለት ትልቅ ሸክም ሆኖብሃል? ውስጥህ ተረብሿል? ብርታት አጥተሃል? ዋጋህን ለመጨመር ተቸግረሃል? እራስህ ላይ ለመሰልጠን፣ እራስህን ለመግዛት አቅም አንሶሃል? እንግዲያውስ ይህን ንግግር ከልብህ አንስተህ በቃልህ ደጋግመህ ለእራስህ ንገረው፦ "ልበ ብርቱ መንፈሰ ጠንካራ፣ ለአለም ፈተና የማልበገር በእግዚአብሔር የምታመን፣ በአምላኬ መፅናትን የተማርኩኝ፣ በሙላት መፈጠሬ የማያጠራጥረኝ፣ በአሁን ስቃዬ እራሴን የማልለካ፣ አቅሜን የማልገድብ፣ መማር፣ ማወቅን፣ መንቃትን የማላቆም፣ ከእራሴ የሚልቅ፣ ከከባቢዬ የገዘፈ ለሀገር፣ ለአህጉርና ለአለም የሚበቃ ብሩህ ተስፋ ያለኝ፣ እምነቴን ዋና ስንቄ፣ የአምላኬን መንፈስ ጋሻዬ አድርጌ የምጓዝ፣ ስብራቴን ለማከም ማንንም የማልጠብቅ፣ በአምላካዊ ፍቅር በታደለኝ ጥበብ እራሴን የማድን እኔ ብርቱ የአምላኬ ልጅ ነኝ።" ብለህ ለእራስህ ደጋግመህ ተናገር።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ የአምላክህ ልጅ ነህ! የደጉ አባትህ፣ ፍቅር የሆነው፣ በፍቅር የሚያኖርህ፣ ፍቅሩን በየቀኑ የሚገልፅልህ፣ ውሎህን የሚያሳምርልህ፣ መንገድህን የሚጠርግልህ፣ መዓትህን የሚያርቅልህ አዎ! የእርሱ የህያው አምላክህ ልጅ ነህ። አለምን አትፍራ፣ ህይወትህን ከልክ በላይ አታግዝፋት፤ በምድራዊ ዱብዳ፣ በጊዜያዊ ችግር፣ በጊዜያዊ እጦት አትሸማቀቅ። በተለዋዋጭ አለም ፍፁም የማይለዋወጥ በፊትም፣ ዛሬም፣ ነገም ያው ፍቅር የሆነ አምላክ እንዳለህ አስታውስ። በእርግጥ አለም ውስጥ ብዙ አይንን የሚስቡ፣ ለጆሮ የሚጥሙ፣ ስሜትን የሚገዙ፣ ለማድረግ፣ ለመስራት ብሎም የእራስ ለማድረግ የሚያስጎመዡ አያሌ ነገሮች ይኖራሉ። ነገር ግን እንደሚጠበቁት ጥምን አይቆርጡም፤ አምሮትን አያወጡም፤ ስሜትን አያረኩም፤ ውስጣዊ ሰላምን አይሰጡም።

አዎ! ከድካምህ ለማረፍ መንፈስህን ጠግን፣ ከሩጫህ ፋታ ለመውሰድ በእግዚአብሔር መንገድ ተመላለስ፤ ህይወትህን እንደ አዲስ ለማነፅ የአምላክህን ድንቅ ስራ፣ የፈጣሪህን የስነ-ፍጥረት ጥበብ አስተውል። ጨለማን እንዲሁ በዝምታ በአርምሞ ፈጠረ ጨለማም ሆነ፤ ብረሃንንም በቃሉ በነቢበ ብረሃን ይሁን አለ ብረሃንም ሆነ። በዝምታ ረቂቁን ጨለማ የፈጠረ፣ በቃሉ ብቻ አስደናቂውን ብረሃን ወደ ምድር ያመጣ አምላክ ላንተ ህይወት ብረሃን መስጠት፣ ጨለማህን መግፈፍ ምንያክል ቀለሉ እንደሆነ አስብ። ነገር ግን በእርሱ ላይ ያለህን እምነት ይፈልጋል፤ ፅናትህን፣ ፍፁም እርሱን ማስቀደምህን፣ ከውስኗ ሰውኛ አቅምህ በተሻለ ስልጣኑን ለእርሱ እንድትሰጥ ይፈልጋል። አምላክህን አስቀድም ህይወትህንም አንተ ቅደም፣ አንተ አሸንፋት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q