Get Mystery Box with random crypto!

እራስህን ተመልከት! የትኛውም ግንኙነት ውስጥ ከመግባትህ በፊት እራስህን ተመልከት ፤ ወዴትም በጭ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

እራስህን ተመልከት!

የትኛውም ግንኙነት ውስጥ ከመግባትህ በፊት እራስህን ተመልከት ፤ ወዴትም በጭፍን ከመጓዝህ አስቀድሞ እራስህን መዝን ። እራሱን የማይወድ ሰው ሁሌም ፍቅርን ከሰው እየጠበቀ የሚሰቃይ ሰው እንደሆነ አስታውስ ። ግንኙነት ድርሰቶች ላይ እንዳለው ፍፁም እንከን አልባ አይደለም ፤ የተለያዩ የፍቅር ፊልም ላይ እንደሚገለፀው ሙሉ ማንነትህን የሚቀማህም አይደለም ። ድርሰት ከእውነታው ይልቅ የሰውን ትኩረት ለመሳብ የሚደረግ ነገር ይበዛዋል ። ደራሲው በፈለገው መልኩ ሊማርክህ ይችላል ፣ ተዋንያኖቹም እንዲሁ ያደርጋሉ ። ትክክለኛው ያንተ ህይወት እውነታ ግን ከዚህ የወጣ ነው ። እራስህን ሳትመለከት ፣ ደረጃህን ሳትረዳ ፣ ማንነትህን ሳታውቅ ፣ መስጠት የምትችለውን ሳትገነዘብ ፣ የምትቀበለውን ብቻ እያሰብክ በጭፍን የምትገባበት የትኛውም ግንኙነት አንደኛው የውድቀትህ ምክንያት ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን ተመልከት! እራስህን በጥልቀት ጠይቀው። ሌላ ተጨማሪ ሰው ወደ ህይወትህ ከማስገባትህ በፊት ለእራስህ ያለህን ቦታ ገምግም ፤ ከሌላ ሰው ጋር ከመወዳጀትህ በፊት ከእራስህ ጋር ያለህ ወዳጅነት ምን እንደሚመስል እወቅ ። ለእራሳችን የማንሰጠውን ክብር ፣ ቦታና እንክብካቤ በተወሰነ ጊዜያት ለምናውቀው ሰው እየሰጠን መጨረሻችን ህመምና ስቃይ ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ ጥቂት አይደለም ። አንተ ጨክነህ እራስህን አሳልፈህ ከሰጠህ ቦሃል ማንም አንተን የማዳን ግዴታ የለበትም ። እውነተኛ ግንኙነትና የድርሰቱ አለም በብዙ መልኩ እንደሚለያይ ካልተረዳህ እራስህን ከፉ ወጥመድ ውስጥ እያስገባህ ነው ። ከማንም ከምንም በፊት ቀዳሚው ለእራስህ የምትሰጠው ፍቅር ፣ ክብርና ቦታ ነው ። ሌላው የማጋራት ደረጃው ላይ ብቻ ስትደርስ የምታደርገው ነገር ነው ።

አዎ! ጀግኒት..! አንቺ ያልወደድሽውንና ያልተቀበልሽውን ማንነትሽን ሌላው እንዲወደውና እንዲቀበለው አትታገይ ። እራስሽን መጠገን ፣ ተፈላጊ ሰው መሆንሽን ማስመስከር ፣ ለምትፈልጊው ነገር ብቁ እንደሆንሽ ማረጋገጥ የእራስሽ ድርሻ ነው ። እራስሽን ደካማ የሚመጣውን ጠንካራ ፣ እራስሽን ተረጂ የሚመጣውን ሰው ረጂና ደጋፊ አድርጎ መሳል አቁሚ ። እራስሽን ካላጠነከርሽ ማንም ቢመጣ ሊያጠነክርሽ አይችልም ፤ እራስሽን ካልረዳሽ ማንም እስከመጨረሻው የሚረዳሽ የለም ። ለእራስሽ መወገን ካልቻልሽ ወገን እንደሌለሽ ቁጠሪው ፤ ምክንያቱም አንድ ቀን ብቻሽን መቅረትሽ አይቀርምና ነው ። ህይወትን ልክ እንደ ድርሰት ሳይሆን እንድ እራሱ እንደ ትክክለኛ ህይወት መኖር ጀምሪ ። ያየሽውን ሁሉ ለማድረግ ሳይሆን የሚገባሽንና የሚጠቅምሽን ለማድረግ እራስሽን አዘጋጂ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q