Get Mystery Box with random crypto!

እብድ ተባል! እብድ አትሁን ነገር ግን በሚያዩህ እብድ ተባል ፤ የለየለት አለሌ አትሁን ነገር ግ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

እብድ ተባል!

እብድ አትሁን ነገር ግን በሚያዩህ እብድ ተባል ፤ የለየለት አለሌ አትሁን ነገር ግን ለሚከታተሉህ አለሌ ሁን ፤ ብቸኛ አትሁን ነገር ግን ለሰዎች ብቸኛ ሰው አልባ ሁን ። ትክክለኛው ማንነትህ አንተ ለእራስህ የሆነከው እንጂ ለሰዎች ሆነህ የምትታየው አይደለም ። የእብደት መለኪያ ብዙ ቢኖርም የተለየ መንገድ ስለመረጥክና እራስህን እንደ ጀግና ስለተመለከትክ እንደ እብድ ብትቆጠር ለእራስህ ትክክለኛው መንገድ ላይ እስከሆንክ ድረስ ግድ አይስጥህ ፣ ብዙ አትጨነቅ ። በማይመለከትህ ጉዳይ ከሰዎች ባለማውራትህ ፣ ወሬያቸውን ባለማዳመቅህ ፣ ከማይመጥንህ ስፍራ በመራቅህ ፣ የብቻኝነት ደሴትህን በመውደድህ ዝምተኛ ፣ ብቸኛና ሰው እንደማትወድ ልትቆጠር ትችላለህ ፤ ነገር ግን ከእራስህና ከአምላክህ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እስካለህ ድረስ ብቸኛ ልትሆን አትችልም ።

አዎ! ጀግናዬ..! የተባልከውን አይደለህምና እብድ ተባል ፤ የሆንከውን ነህና የማይሆን ስም ይውጣልህ ፤ እራስህን ታውቃለህና ትቺት ይቅረብብህ ፤ በፍፁም አትጨነቅ ። ባለን አጭር የመኖር ጊዜ ስለምንባለው ፣ ስለሚወራብን ጉዳይ ተጨንቀን ህይወታችንን ይባስ ልናሳጥራት አይገባም ። እራስህን ስታውቅ በኩራት መኖር ትጀምራለህ ፤ የት መድረስ እንደምትችል ፣ ደረጃህ ምን እንደሆነ ስታውቅ የልብህ ሙላት የአሰናካዮችህን አይን ያርቅልሃል ። ቀላልም ይሁን ከባድ እራስህን ሆነህ ለእራስህ መታገል የግድ ነው ። አሉታዊ ንግግርን መዝራት የለመደች ምላስ ለማንም አትመለስምና አስቀድሞ መንፈስን ማጠንከር ፣ እራስህን ማበርታት ያስፈልጋል ።

አዎ! ምንም ስታደርግ የማይጥማቸው ሰዎች ካሉ ፣ አንድ ነገር በከወንክ ቁጥር ለተቃውሞ የሚንደረደሩ ሰዎች ካጋጠሙህ ፣ ቀላሉን "በርታ" ማለት ከብዷቸው ከባዱን "አትችልም ይቅርብህ" ለማለት የሚሯሯጡ ሰዎች ወደ ህይወትህ ቢመጡ ማዳመጥ ሳይሆን ለአፍታም ጊዜ መስጠት አያስፈልግህም ። የሚለጠፍብህ ስም ፣ የሚወራብህ ወሬ ፣ የሚነገርብህ ጉዳይ አንተን እንደማይገልፅህ በተግባር አሳይ ። "እሱ እብድ ነው ፤ የሚያደርገውን አያውቅም ፤ የሚመክረው ሰው የለውም ፤ ዝም ብሎ ይለፋል ።" መባል የእንቅስቃሴህ ማሳያ ነው ። ምክንያቱም የተለየ ተግባር ላይ ያልተሰማራ ፣ ባልተለመደ አቅጣጫ የማይጓዝ ፣ በመደበኛው መንገድ የሚመላለስ ሰው እንዴትም እብድ ሊባል አይችልምና ነው ። የምትባለውን ተወት አድርገህ ፈልገህ የሆንከው ላይ አተኩር ፤ ከተሰጠህ ስም በላይ ያለህበት ስፍራ ያሳስብህ ፤ በእራስህ መንገድ መዳረሻህን እራስህ ወስን ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q