Get Mystery Box with random crypto!

መነቃቃትህን እርሳው! አዎ! መነቃቃትህን እርሳው ለእራስህ የገባሀው ቃል ላይ አተኩር ፤ ለስሜትህ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

መነቃቃትህን እርሳው!

አዎ! መነቃቃትህን እርሳው ለእራስህ የገባሀው ቃል ላይ አተኩር ፤ ለስሜትህ መገዛት አቁም ማድረግ የሚገባህን በጊዜው አድርግ ፤ በምታየው ፣ በምትሰማው መማረክህን አቁም ፣ አይንና ጆሮህ ግብህ ላይ ይሁን ። መነቃቃት ጊዜያዊ ነውና እርሱን መጠበቅ ከጀመርክ ተግባርህም ጊዜያዊ እንደሚሆን አትጠራጠር ፤ እንድ ዲም ላይት (dem light) ስትነቃቃ የምታደርገው ሲደብርህ የምታቆመው ተግባር የት ሊያደርስህ ይችላል ? ወዴትስ ይወስድሃል? ወዴትም ። በድግግሞሽ ስሜት ፣ በተደጋገመ ውጤት ያደክምሃል ፤ የጠበከውን ሳይሆን የሆንከውን ያሳይሃል ፤ የምትፈልገውን ሳይሆን ያደረከውን ፍሬ ያመላክትሃል ። ከሁሉም በላይ ዲሲፕሊን (discipline) ፣ እራስን መግዛት ፣ እራስን መገሰፅ ፣ ላወጣሃቸው የእራስ ደረጃዎች መታምን ፣ ማንም ባያየንም ፣ ማንም ቃላችንን ባይሰማም ለእራሳችን ለገባነው ቃል መታመን ይኖርብናል ።

አዎ! ጀግናዬ...! መነቃቃትህን እርሳው! ዲሲፕሊንን አስቀድም ፤ ከስሜት በላይ መሆንን ተላመድ ፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ ትርጉም ማግኘትን አዳብር ። ሲመችህ ብቻ በምትሰራው እንቅስቃሴ የሰውነት አቋምህ አይቀየርም ፤ ሲደላህ ብቻ በምታስበው ሃሳብ እራስህን አታሻሽልም ፤ የፈለከው ሁሉ ተሟልቶ በምታደርገው ተግባር ብቻ ወደፊት መጓዝ አትችልም ። አንዳንድ ሁኔታዎች ልፋት እንጂ ቶሎ ውጤት አይኖራቸውም ፤ ያደክሙሃል እንጂ የሚታይ ነገር አትመለከትባቸውም ፤ እለት እለት ስትደክም ትመለከታለህ እንጂ በፍፁም ጠብ የሚል ነገር አታገኝባቸውም ። የአሁን ድካምህን ሳይሆን የወደፊት ውጤትህን አስበህ ትታገላለህ ፤ የአሁን መረበሽህን ረስተህ የመጪው መረጋጋትህ ላይ ታተኩራለህ ። ቢዘገይም የምትናፍቃትን ብረሃን ትመለከታለህ ፤ ቢቆይም ተስፋ ያደረከው ደረጃ ላይ እራስህን ታገኘዋለህ ፤ ቢያደክምህም የለፋህበት ዋጋ ይገፈልሃል ።

አዎ! ዲሲፕሊን ቀላል አይደለም ፤ ዋጋ መክፈል ፣ ወዶ መሰቃየት ፣ ውጤት ሳይኖር መድከም ፣ በማይታይ ትግል መጠመድ ፣ እለት እለት ከእራስ ጋር መሟገት ፣ ውጪ የምታየው ሌላ ውስጥህ የምታየው ሌላ ሲሆን የስሜትህን መቀያየር መቆጣጠር ከባድ ነው ። በዚህ ሁሉ ውጣውረድ ውስጥ ለእራስህ መታመን ካልቻልክ ይባስ ነገሮችን ታከብዳቸዋለህ ። የሚሰራ ሰው ፣ ለምን የሚሰራውን ስራ ከብዙዎች መርጦ እንደሚሰራው ካላወቀ በስሜቱና በጉልበቱ እየተጫወተ ነው ። ገንዘብ ለማግኘት ፣ ህይወትን ለማሸነፍ ፣ ሌሎችን ለመርዳት ፣ ህልሙን ለመኖር ሊሆን ይችላል ። ምክንያቱን በማነቃቂያው ቦታ የሚያስቀምጥ ከሆነ ዲሲፕሊንን የማያዳብርበት ፣ እራሱ ላይ የማያተኩርበት ፣ በምክንያቱ የማይገዛበትን አጋጣሚ አይኖረውም ። ለተግባርህ ጠንካራ ምክንያት ይኑርህ ፣ ለምታደርገው ነገር ዋጋ የሚያስከፍል ፅኑ ፍላጎት ይኑርህ ፤ በመነቃቃት ሳይሆን በምክንያትህ ተመራ ፤ ለምክንያትህ ብለህ እራስህን ግዛ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q