Get Mystery Box with random crypto!

ዋጋህን ጨምር! ያመለጡህን እድሎች እርሳቸው ፤ የሳትከውን ታርጌት እርሳው ፤ ያመለጠህን አጋጣሚ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ዋጋህን ጨምር!

ያመለጡህን እድሎች እርሳቸው ፤ የሳትከውን ታርጌት እርሳው ፤ ያመለጠህን አጋጣሚ ደጋግመህ ማሰብ አቁም ። አንድ የገባህ ነገር ካለ እርሱን ይዘህ እስከመጨረሻ መጓዝ ተለማመድ ። በየመሃሉ የሚያጋጥሙህን እንቅፋቶች ብዙ ትኩረት አትስጣቸው ፤ ውስጥህ ከተሳለው ትልቅ ነገር የአንድ ቀን አሉታዊ ንግግር ወይም ያልተገባ ተቃውሞ አንዲረብሽህ አትፍቀድ ። ማናችንም ስለ ውሎአችን ማሰብ ካልቻልን ፣ ለአካባቢያችን ካልተጠነቀቅን ፣ የምንሰማውን ካልመረጥን ፣ ለምናየው ካልተጠነቀቅን ስብራታችን ማብቂያ አይኖረውም ፤ ዘወትር ጀምሮ ማቆማችን ይቀጥላል ፤ በየመሃሉ በሚመጣው ድካም ዋጋ መክፈላችን አይቀርም ። አቅደህ በምትኖረው ህይወት ፣ ግብህን ባስቀመጥክለት ፣ እራስህን በሰጠህለት ፣ በጥንቃቄ ለምትመራው ህይወት አጋጣሚ የተባለ ነገር እቅድህን እንዲያበላሽና መንገድህን እንዲያስትህ መፍቀድ አይኖርብህም ።

አዎ! ጀግናዬ..! በአስተሳሰብህ ፣ በእይታህ ፣ በተግባርህና በዉሎህ ዋጋህን ጨምር ፤ እሴት ያለው ህይወት መኖር ጀምር ። ሰዎችን መጥቀም ስትፈልግ በልበሙሉነት አድርገው ፤ ውስጥህ ለመልካም ነገር ሲጓጓ ሄደህ ከውነው ፤ ሰላም እንደሚሰጥህ የተሰማህ ነገር ካለ አጥብቀህ ግፋበት። ንቃትህ ለጊዜው ቢሆንምከ ፍላጎትህ ግን ሁሌም እንዲገፋህና እንዲያበረታህ አድርግ ። በቅድሚያ ያንተን ምርጫ ምታከብረው አንተ እንጂ ሌላው አይደለም ፤ ማንም የሚበጅህን የሚያውቅልህ አካል የለም ። ለእራስህ እራስህ እንደምታውቅ ፣ ለእራስህም ብቁ እንደሆንክ ማሳየቱ ያንተ ድርሻ ነው ። በተወሳሰበ ስብዕና ፣ ባልተገለጠ ማንነት ፣ በተሸፈነ አስተሳሰብ ሳይሆን ቀላል ፣ ግልፅና ብርቱ በሆነ ማንነት እራስህን አሳይ ።

አዎ! እራሱን ያወቀ ዋጋውን ያውቃል ፤ የሚገባው ስፍራ የት እንደሆነ በሚገባ ይረዳል ። ዋጋህን ስትጨምር ውሎህ ይቀየራል ፤ እሳቤህ ፣ እርምጃዎችህና ንግግርህ ሁሉ የተለየ ይሆናል ። ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አላስፈላጊ ጊዜህን አታባክን ፤ በሚወረወሩብህ ጥቃቅን ጠጠሮች ማንነትህን አትገምት ፤ በሚሰጡህ አሉታዊ ስያሜዎች ስሜትህን አትረብሽ ። ማንም ያንተን መንገድ መሔድ እንደማይችል አስታውስ ። ይብዛም ይነስም በልክህ ብዙ ውጣውረድ አልፈሃል ፤ ተፈትነሃል ፤ ዋጋም ከፍለሃል። ይህን በማድረግህም በየጊዜው ዋጋህን እየጨመርክ ትመጣለህና በእራስህ ለመኩራት ምንም አይነት ውጫዊ ማረጋገጫ አትፈልግም ። በእራስህ ምርጫ ማደግህን ቀጥል ፤ ዋጋህንም በየእለቱ ጨምር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q