Get Mystery Box with random crypto!

ፍቃድ አትጠብቅ! ምርጡ ፣ ወሳኚ ፣ ምቹውና ትክክለኛው ጊዜ መቼ ነው? ህይወት ቀያሪው ፣ ከፍታን | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ፍቃድ አትጠብቅ!

ምርጡ ፣ ወሳኚ ፣ ምቹውና ትክክለኛው ጊዜ መቼ ነው? ህይወት ቀያሪው ፣ ከፍታን ፈጣሪው ፣ ስኬትን አቅራቢው ፣ ልዕልናውን የሚያፈጥነው ትክክለኛ ጊዜ መቼ ነው ? ትናንት? ዛሬ? ነገ ወይስ አሁን ? ትክክለኛው ጊዜ ነገም ፣ ዛሬም ፣ ትናንትም አይደለም ። እናም አሁንና አሁን ብቻ ነው ። ትክክለኛና እንከን አልባ ነገር ለመስራት ለአመታት ልትጠብቅ ትችላለህ ፣ እስክትማር ፣ እስክትአውቅ ፣ ብቁ ነኝ ብለህ እስክታስብ፣ ሰዎች ትችላለህ ጀምር እስኪሉህ ልትጠብቅ ትችላለህ ። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ከዚህ ሁሉ ጥበቃ ቦሃላ እንኳን ስህተት መስራትህ አይቀርም ፤ ማጥፋትህ አይቀርም ፤ ውድቀትህም እንደዛው ። ቦሃላም መለስ ብለህ እራስህን ትጠይቃለህ "ይህን ሁሉ ጊዜ የጠበኩት ለመሳሳት ነውን ? ይህን ሁሉ ጊዜ እራሴን የገደብኩት ፣ በፍረሃቴ የተሸነፍኩት ፣ ፍላጎቴን ያዳፈንኩት ውድቀቴ ለማይቀር ነገር ነውን ?" ትላለህ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ፍቃድ አትጠብቅ! የሆነ ሰው ወደ ህይወትህ መጥቶ መሆን የምትፈልገውን ሰው እንድትሆን እንዲፈቅድልህ አትጠብቅ ፤ መንግስት "ላንተ የሚመችህ ይህ ነው ፤ ይህን አድርግ ፣ እንደዚህ ስራ" እስኪልህ አትጠብቅ ፤ የፈለከው ገንዘብ መጥቶ ፣ የተመኘው እቃ ተሟልቶ አንተ ስራውን እንድትጀመር የምትጠራበትን ጊዜ አትጠብቅ ። መጀመሩ ብቻ ሳይሆን እስከ ጅማሬህ የሚወስድህን የፅናት ፣ የትእግስትና የድፍረት ጉዞም መጓዝ ያለብህ አንተው እራስህ ነህ ። ፍራትህን በማስታመም ስህተትህን አታጠፋም ፤ ስጋትህን በመጠየፍ ከውድቀት አታመልጥም ፤ ፍፁምነትን እየተመኘህ እንከን አልባ ስራ አትሰራም ። ስህተትህን አትጠብቅ ፤ መሳሳት ካለብህ አሁን አድርገህ ተሳሳት ።

አዎ! የመጠው ቢመጣም ፣ ስህተቱ ቢፈጠርም ፣ ውድቀቱ ቢከሰትም ፣ ትቺቱ ቢያጋጥምህም አሁን ጀምረህ ተሳሳት ፤ አሁን ጀምረህ ውደቅ ፤ አሁን ተነስተህ ተተች። ቦሃላ ፣ ነገ ፣ የሚቀጥለው አመት ማለት የህልምህ ጠላት እንደሆነ እወቅ ። ጊዜውን ከማዘግየቱም በላይ ፣ በሂደት በስንፍና ሃይል ከህልምህ ይለይሃል ፤ ከራዕይህ ይነጥልሃል ፤ መኖር ከሚገባህ ህይወት ያስቀርሃል ። ማንም ያልተሳሳተ ፣ ማንም ያልወደቀ ፣ ማንም ትቺት ያልቀረበበት፣ ሰው መጥፎ አስተያየት ያልሰጠው ሰው ቢኖር ያልጀመረና ባለበት የቆመ ሰው ብቻ ነው ። ስህተትህ ጅማሬህን ያመላክትሃል ፤ ውድቀትህ ጥረትህን ይገልፃል ፤ የሰው አይን ውስጥ መግባትህ ጉዞ መጀመርህን ያሳያል ። በፍረሃት የምትሸረሽረው ፣ በፍፁምነት እሳቤ የምትቀናንሰው ረጅም ጊዜ ያለህ እንዳይመስልህ ። ጉልበትህ ውሱን ነው ፤ ንቃትህ የተገደበ ነው ፤ ሁሉም በጊዜው ልክ እየሔደና እየወረደ ይመጣል ። ብርታትህን በፍጥነት ተጠቀም ፤ ንቃትህን በጊዜ ስራ ላይ አውለው ፤ ጥንካሬህን በጠዋቱ ለፍሬ አብቃው ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q