Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርን በሙላት ኑሪ! አዎ! ፍቅርን በሙላት ኑሪ ፣ ህይወትሽን ስሜት ስጪው ፤ ውብ አስደሳች ማራ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ፍቅርን በሙላት ኑሪ!

አዎ! ፍቅርን በሙላት ኑሪ ፣ ህይወትሽን ስሜት ስጪው ፤ ውብ አስደሳች ማራኪ አድርጊው ። ጊዜ እንደሌለሽ አስቢ ፤ የሚወዱሽን እንደ ውዶችሽ ተመለከቺ ፤ ለሚያስቡልሽ ጊዜ ስጪ ፤ ለሚያዝኑልሽ ማዘን ጀምሪ ፤ ለሚንከባከቡሽ እንክካቤን ለግሺ ። ህይወት አጭር ነች በተስፋሽ አስረዝሚያት ፤ ህይወት ጉድለት አይጠፋትም በፅናትሽ ሙሉ አድርጊያት ፤ ህይወት እንቅፋቶች ይኖሯታል በብርታትሽ ተሻገሪያቸው ። ስለእራስሽ ብቻ ማሰብ አቁሚ ፤ ባንቺ መኖር የሚያተርፍ ፣ ባንቺ ከጎኑ መቆም የሚደሰት ሰው እንዳለ አስቢ ። ሰው የለኝም ከማለትሽ በፊት ሰው ለሌላቸው ሰው ሆኖ መገኘትን ተለማመጂ ፤ በእርግጥም ከልብሽ ሰዎች እንዲሆኑልሽ የምትፈልጊውን ሰው ለሰዎች ለመሆን ሞክሪ ። ውስጥሽ የሌለ ማንነት ስለፈለግሽው ብቻ እንደማይመጣ አስታውሺ ።

አዎ! ጀግኒት..! የሆንሽውን ከጎንሽ ታገኚዋለሽና ፤ ውስጥሸ ያለው ወዳንቺ ይመጣልና ፍቅርን በሙላት ኑሪ ፤ ለምኞትሽ ሁሉ ልባዊ ጥሩ ስሜት ይኑርሽ ። አንዳንዴ ፍላጎታችን ሌላ ፣ እኛ የሆነው ሰው ሌላ ሆኖ ይገኛል ። መልካም ሰው ወደ ህይወቱ እንዲገባ የሚፈልግና የሚጠብቅ ሰው ፣ ከጥበቃው በፊት የእርሱን መልካምነት ፣ የእርሱን ለዛ ለሚመጣ ሰው ተገቢ መሆን በሚገባ ማረጋገጥ ይኖርበታል ። ከእራስሽ ጋር በፍቅር ከወደቅሽ አንቺን የሚያፈቅርና የሚያከብር አይጠፋም ። ህይወትን መኖር በስስት ነው ፤ ዛሬን ማሳለፍ በሙላት ነው ። ምክንያቱም ከአንድ ጀምበር ኋላ የምትመጣው ከቀድሞው የተለየችና አዲስ ቀን ፣ አዲስ ህይወት ነችና ነው ። በህይወት እያለሽ ማሳካት የምትፈልጊውን ነገር በጥልቀት መርምሪው ፤ መመስረት የምትመኚውን የቤተሰብ ሁኔታ ፣ እንዲኖርሽ የምትፈልጊውን ስፍራ ፣ መርዳት የምትመኚውን ሰው ደጋግመሽ አስቢ። ዛሬ ያለሽበትን ስፍራ ተመልከቺ ፣ ጉዞሽን አስተውይ ፣ ምንያክል ለምኞትና ፍላጎቶችሽ ብቁ እንደሆንሽ እራስሽን ጠይቂ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ማምጣት የምትፈልገውን ተዓምር የምታመጣው በውስጥህ ፈጥረሀው ከጨረስክ ቦሃላ ነው ። ያንተ እንደሆነ ያመንከው ነገር ያንተ ነው ፤ ያንተ በመሆኑ የሚሰማህን ስሜት ማጣጣም ስትጀምር በእውን ያላችሁ ርቀት እየጠበበ ይመጣል ። በምኞት አለም ለመኖር ጊዜ እንደሌለህ አስብ ፤ ዘወትር የምትፈልገውን እያሰብክ ለመዝለቅ ሁኔታዎች እንደማይፈቀዱ አስተውል ። የልብህ መሻት እውን ይሆን ዘንድ የፍቅርን ሃይል በሚገባ ልትጠቀመው ይገባል ። ደስታን የሚሰጥህን ነገር ለመውደድ ገደብ አታስቀምጥ ፤ በሚያረጋጋህ ነገር ለመረጋጋት እራስህን አታቅብ ፤ ውስጥህ ሃሴት የሚፈጥርልህን ነገር ከማጣጣም ወደኋላ አትበል ። በዙሪያህ በጣም ብዙ ህይወት ኖሯቸው ህይወት የሚዘሩብህ ፣ ምሉዕ የሚያደርጉህ ነገሮች አሉ ። ፍቅርን ከልብህ መኖር ስትጀምር ፣ ለተፈጥሮ ያለህ ስሜት ከውስጥህ ሲወጣ ፣ በከባቢህ ስትማረክ ካሰብከው በላይ የህይወት ምርጫና ፍላጎት በአንድ አቅጣጫ ሲዋሃዱ ትመለከታለህ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q