Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርን በሙላት ኑሪ! አዎ! ፍቅርን በሙላት ኑሪ፣ ህይወትሽን ስሜት ስጪው፤ ውብ አስደሳች ማራኪ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ፍቅርን በሙላት ኑሪ!

አዎ! ፍቅርን በሙላት ኑሪ፣ ህይወትሽን ስሜት ስጪው፤ ውብ አስደሳች ማራኪ አድርጊው። ጊዜ እንደሌለሽ አስቢ፤ የሚወዱሽን እንደ ውዶችሽ ተመለከቺ፤ ለሚያስቡልሽ ጊዜ ስጪ፤ ለሚያዝኑልሽ ማዘን ጀምሪ፤ ለሚንከባከቡሽ እንክካቤን ለግሺ። ህይወት አጭር ነች በተስፋሽ አስረዝሚያት፤ ህይወት ጉድለት አይጠፋትም በፅናትሽ ሙሉ አድርጊያት፤ ህይወት እንቅፋቶች ይኖሯታል በብርታትሽ ተሻገሪያቸው። ስለእራስሽ ብቻ ማሰብ አቁሚ፤ ባንቺ መኖር የሚያተርፍ፣ ባንቺ ከጎኑ መቆም የሚደሰት ሰው እንዳለ አስቢ። ሰው የለኝም ከማለትሽ በፊት ሰው ለሌላቸው ሰው ሆኖ መገኘትን ተለማመጂ፤ በእርግጥም ከልብሽ ሰዎች እንዲሆኑልሽ የምትፈልጊውን ሰው ለሰዎች ለመሆን ሞክሪ። ውስጥሽ የሌለ ማንነት ስለፈለግሽው ብቻ እንደማይመጣ አስታውሺ።

አዎ! ጀግኒት..! የሆንሽውን ከጎንሽ ታገኚዋለሽና፤ ውስጥሸ ያለው ወዳንቺ ይመጣልና ፍቅርን በሙላት ኑሪ፤ ለምኞትሽ ሁሉ ልባዊ ጥሩ ስሜት ይኑርሽ። አንዳንዴ ፍላጎታችን ሌላ፣ እኛ የሆነው ሰው ሌላ ሆኖ ይገኛል። መልካም ሰው ወደ ህይወቱ እንዲገባ የሚፈልግና የሚጠብቅ ሰው፣ ከጥበቃው በፊት የእርሱን መልካምነት፣ የእርሱን ለዛ ለሚመጣ ሰው ተገቢ መሆን በሚገባ ማረጋገጥ ይኖርበታል። ከእራስሽ ጋር በፍቅር ከወደቅሽ አንቺን የሚያፈቅርና የሚያከብር አይጠፋም። ህይወትን መኖር በስስት ነው፤ ዛሬን ማሳለፍ በሙላት ነው። ምክንያቱም ከአንድ ጀምበር ኋላ የምትመጣው ከቀድሞው የተለየችና አዲስ ቀን፣ አዲስ ህይወት ነችና ነው። በህይወት እያለሽ ማሳካት የምትፈልጊውን ነገር በጥልቀት መርምሪው፤ መመስረት የምትመኚውን የቤተሰብ ሁኔታ፣ እንዲኖርሽ የምትፈልጊውን ስፍራ፣ መርዳት የምትመኚውን ሰው ደጋግመሽ አስቢ። ዛሬ ያለሽበትን ስፍራ ተመልከቺ፣ ጉዞሽን አስተውይ፣ ምንያክል ለምኞትና ፍላጎቶችሽ ብቁ እንደሆንሽ እራስሽን ጠይቂ።

አዎ! ጀግናዬ..! ማምጣት የምትፈልገውን ተዓምር የምታመጣው በውስጥህ ፈጥረሀው ከጨረስክ ቦሃላ ነው ። ያንተ እንደሆነ ያመንከው ነገር ያንተ ነው ፤ ያንተ በመሆኑ የሚሰማህን ስሜት ማጣጣም ስትጀምር በእውን ያላችሁ ርቀት እየጠበበ ይመጣል ። በምኞት አለም ለመኖር ጊዜ እንደሌለህ አስብ ፤ ዘወትር የምትፈልገውን እያሰብክ ለመዝለቅ ሁኔታዎች እንደማይፈቀዱ አስተውል ። የልብህ መሻት እውን ይሆን ዘንድ የፍቅርን ሃይል በሚገባ ልትጠቀመው ይገባል ። ደስታን የሚሰጥህን ነገር ለመውደድ ገደብ አታስቀምጥ ፤ በሚያረጋጋህ ነገር ለመረጋጋት እራስህን አታቅብ ፤ ውስጥህ ሃሴት የሚፈጥርልህን ነገር ከማጣጣም ወደኋላ አትበል ። በዙሪያህ በጣም ብዙ ህይወት ኖሯቸው ህይወት የሚዘሩብህ ፣ ምሉዕ የሚያደርጉህ ነገሮች አሉ። ፍቅርን ከልብህ መኖር ስትጀምር ፣ ለተፈጥሮ ያለህ ስሜት ከውስጥህ ሲወጣ ፣ በከባቢህ ስትማረክ ካሰብከው በላይ የህይወት ምርጫና ፍላጎት በአንድ አቅጣጫ ሲዋሃዱ ትመለከታለህ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q