Get Mystery Box with random crypto!

ምንድነው የምትሰጠው? እንደ አንድ ጥሩ ሰው ፣ እንደ አንድ ብርቱ ለሰው አዛኝ ሰው ፣ እንደ አን | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ምንድነው የምትሰጠው?

እንደ አንድ ጥሩ ሰው ፣ እንደ አንድ ብርቱ ለሰው አዛኝ ሰው ፣ እንደ አንድ ቅንና የዋህ ሰው ይበልጥ የሚያስጨንቅህ ነገር ምንድነው ? የምትሰጠው ወይስ የምትቀበለው ? የምታደርገው ወይስ የሚደረግልህ ? የምታስገኘው ወይስ የምታገኘው ? የምታስጨምረው ወይስ የሚጨመርልህ ? ለየትኛው ይበልጥ ትኩረት ትሰጣለህ ? ልብህ ለየትኛው ያደላል ። መቀበል የለመደ ሰው ደስታው ሁሌም የሚሰጠውን ነገር በማሰብ የሚያገኘው ነው ። መስጠትን የለመደ ደግሞ ሲሰጥ ብቻ የሚያገኘውን ደስታ በሚገባ ያውቀዋል ። አዲስ ነገር ሲደረግልህ እንደምትደሰተው ሁሉ አዲስ ነገር ለሰዎች ማድረግም ደስታን ሊሰጥህ ይገባል ። የጠበከው ነገር ሲከናወንልህ ልብህ ሃሴት ያደርጋል ፤ ብዙዎች የሚጠብቁትም ባንተ በኩል ሲደረግላቸው ያንተን ስሜት አዳምጥ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ምንድነው የምትሰጠው ? እንደ ማንኛውም ሰው "ምን አለኝና" አትበል ። ምንም ባይኖርህ መስጠት እንደምትችል መለማመድ ይኖርብሃል ። ነገር ግን ማንም ምንም ሳይኖረው ፣ ምንም ሳይሰጠው ፣ ምንም የሚያካፍለው ሳይታደለው የተፈጠረ ሰው የለም ። ትኩረታችን ሁሉ ሰዎች ላይ ሆኖ ያለንን ነገር ግን ማስተዋል ያልቻልን ብዙዎች ነን ። ባለው ነገር የሚመካ ፣ በተሰጠው ነገር ደረቱን የሚነፋ ሰው ቢኖር አለኝ የሚለው ነገር ሲጠፋ ተሽመድምዶ እንደሚቀመጥ ምንም ጥርጥር የለውም ። ኩራትህ በተሰጠህ ፣ ባገኘሀው ወይም በታደልከው ሳይሆን በምትሰጠው ፣ በምታጋራውና በምታካፍለው ይሁን። የሚያኮራህ ነገር አንተ ጋር ያለ ነገር ሳይሆን ካንተ የሚወጣ ነገር ይሁን ።

አዎ! ሌላው ባይኖርህ ተስፋ አለህ ፣ ብርታት አለህ ፣ ቅንነት አለህ ፣ ደግነት ፣ መልካምነት ፣ የዋህነት አለህ ። ሰዎችን ከዚህ በላይ ለረጅም ጊዜ የሚጠቅማቸው ነገር የለም ። የምትሰጣቸው ገንዘበ ለጊዜው ችግራቸውን ይፈታል ፤ የምታጋረቸው ንብረት ለተወሰነ ጊዜ የተሻለ ህይወት ያሳያቸዋል ፤ በየጊዜው የምትመግባቸው የተስፋ ቃል ፣ እንደ ቀላል ጆሮ ሰተህ የምታዳምጣቸው ፣ ሲፈልጉህ አለሁላችሁ የምትላቸው ፣ ብርታትን የምታካፍላቸው ነገር ግን ከምታስበው በላይ ዋጋህን ይጨምራል ። ሁሌም ቢሆን ከምትቀበለው የምትሰጠውን አስበልጥ ፤ ከሚደረግልህ ለሰዎች የምታደርገውና የምታካፍለው ነገር ላይ አተኩር ፤ መስጠትን ፣ ማጋራትን ልመድ ፤ ውስጥህንም በመትረፍረፍ ሙላው ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q