Get Mystery Box with random crypto!

ለዛሬ ተቆጠቡ! ለዛሬ ተቆጠቡ እራሳችሁን ቆጥቡ ፤ ነገሮች ላይ ጠንቃቃ ለመሆን ሞክሩ ፤ ከተለመደ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ለዛሬ ተቆጠቡ!

ለዛሬ ተቆጠቡ እራሳችሁን ቆጥቡ ፤ ነገሮች ላይ ጠንቃቃ ለመሆን ሞክሩ ፤ ከተለመደው አድካሚ ውሎ ፋታ ውሰዱ ፤ ከሚያሳስበችሁ ብሎም ከሚያስጨንቃችሁ ጉዳይ ገለል በሉ ፤ እራሳችሁን ያዝ ፣ ጠበቅ ፣ ቆንጠጥ አድርጉት ። የሁልጊዜ ሩጫችሁ ውጫዊ እይታን ለማግኘት ከሆነ ወደ እራሳችሁ ተመለሱ ፤ የዘወትር ፀሎታችሁ ከሰው በታች ላለመሆን ከሆነ ከዛ በላይ ብቁ መሆን ፣ ትርፋማ መሆን ፣ እሴት መጨመር ላይ አተኩሩ ። በምርጫችሁ ጎዳና ላይ በተለየ ብርታት ስለሚያስቀምጣችሁ ፤ አዲስ ልዩ ብሩህ ውሎን ስለሚያድላችሁ ፤ እድገታችሁን እንድትመለከቱ ስለሚያደርጋችሁ ፣ ዋጋችሁን እንድትጨምሩና እንድታድጉ ስለሚያስችላችሁ በየጊዜው በፍቅር ለሚታደሏችሁ ቀናት ደስ ይበላችሁ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ለዛሬ ተቆጠብ! ለዘመናት አይተህ ፣ ለረጅም ጊዜ ተከትለህ ፣ ለጊዜያት አስበሀው ካልቀየረህ ፣ እሴት ካልጨመረልህ ፣ ዋጋህን ከፍ ካላደረገልህ ሰውና ጉዳይ እራስን ቆጥብ ። ቁጠባ ጨርሶ እንደመተው አይደለም ። እንደ ቀድሞ ሙሉ በሙሉ ማይጠቅሙ ነገሮች ውስጥ ተዘፍቆ ማስተዋልን ከማጣት ይልቅ በቅርብ ርቀት ሆኖ ነገሩን በአንክሮ መመልከት ፣ በጥልቀት ማጥናትና በተለየ መንገድ መረዳት ነው ። ቁጥብነት ያስከብራል ፤ ቁጥብነት ጥንቃቄን ያላብሳል ፤ ስሜታዊነትን ያስታግሳል ፤ በሰዎች ዘንድ የተለየ ስፍራን ያሰጣል ፤ ዋጋን ይጨምራል ፤ ለመመርመር እድል ይሰጣል ። እራስን መግዛት ፣ እራስ ላይ መሰልጠን በጭፍን ከመነዳት ፣ በጭፍን ከመፍረድ ፣ በጭፍን ከመኮነን ይታደጋል ።

አዎ! ዛሬ ለፍላጎትህ የምትቆምበት ፣ ለውስጣዊ እርካታህ ቅድሚያ የምትሰጥበት ፣ በማንም በጭፍን ከመነዳት የምትወዳውንና የሚያስፈልግህን የምትመርጥበት ቀን ነው ። ጨከን ማለትን ተለማመድ ፤ ከባዱን መንገድ ለመምረጥ እራስህን አዘጋጅ ፤ አውቀህ ለመፈተን ፣ በተለየ አቅጣጫ ለመጓዝ ፤ እራስህ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እራስህን አደፋፍር ። ጥራት ያለው ፣ የተረጋጋ ፣ በአንድ አቅጣጫ የሚጓዝ ፣ ትርፋማና አስደሳች ህይወትን ስለመምራት ማሰብ ጀምር ። የእስካሁኑ ሩጫህ ካልቀየረህ ፣ የእስካሁኑ ድካምና ልፋትህ ስሜት ካልሰጠህ ቆም ብለህ እራስህን ጠይቅ ፤ ምን እንደጎደለህ እወቅ ፤ ለምን እንደሆነ ተረዳ ። የምትለወጠውና የምታድገው ያለማቋረጥ ስለሮጥክ ፣ ጠንክረህ ስለሰራህ ፣ ያለእረፍት ስለደከምክ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ጠንክረህ ስላሰብክ ፣ አስተውለህ ስለምትራመድና በየጊዜው እራስህን ስለምትመዝን እንደሆነ ተረዳ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q