Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.43K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-02 05:10:14 ... አንተም አትኖርም!

ሰዎች ከታሪካቸው ይቀዳሉና ታሪክህ ባይኖር አንተም አትኖርም፤ ያሳለፍከው መጥፎም ሆነ ጥሩ ነገር ባይኖር የዛሬው አንተም ባልነበርክ ነበር። ብዙዎች ብዙ የሚያልፍ የማይመስል ስቃይን አሳልፈዋል፤ ዛሬ በዛው አስከፊ ህመም ውስጥም ያሉ ሰዎች ይኖራሉ። ነገር ግን የሁኔታው ክብደትና ፋታ መንሳት ከማለፍ አይከለክለውም። ሁሉም በጊዜው ይታለፋል፤ ታሪክ ይሆናል። ትናትህን ባታልፍ ዛሬህን ባለየህ ነበር፣ ዛሬንም ካላለፍክ ነገን ልታየው አትችልም። ዛሬ ምንም ሊገጥምህ ይችላል፣ አሁን በየትኛውም አስከፊና አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ልትሆን ትችላለህ። አንድ ነገር ግን አስታውስ:- ከዚህ ከባድ ጊዜና ሁኔታ በተሻለ ሊሰራህና ብቁ ሊያደርግህ የሚችል አጋጣሚ የለም። መከዳትን፣ መገፋትን፣ መጠላትን የሚወድ የለም፤ ባይወደውም ግን ሊያልፍበት ግድ ነው። በመንገዱም መሰራቱ የግድ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! መሆን የሚገባህን ሰው እስክትሆን መሰራት ያለበት ስራ ይሰራል። አንቺን የምትመጥንሽ ሴት እስክትፈጠር ስቃዩ ይቀጥላ፤ ለቅሶሽ አያበቃም፤ ህመምሽ አይድንም። መልቀቅ ሲገባሽ አጥብቀሽ የያዝሽው እሾህ እስክትለቂው ድረስ እጅሽን መውጋቱንና ማድማቱን አያቆምም። እሾሁን ይዘሽ ለህመምሽ ሌላ ተወቃሽ አትፈልጊ። ድህነትሽ በእጅሽ እንደሆነ አስተውይ። ነገር ግን እርሱም ቢሆን በበቂ ሁኔታ ካላስተማረሽና ብቁ ካላደረገሽ በፍፁም አይተውሽም። ተዓምር የሚመስል ታሪክ አሳልፈሽ ተራ ህይወት አትኖሪም፤ ከባዱን ትናንት አልፈሽ መደበኛ ህይወት አትኖሪም። የጣለሽ መሰናክል የውድቀትን ህመምና ዳግም የመነሳትን ክብደት በሚገባ ያስተምርሻል፤ መከዳትሽ፣ በሌላ መተካትሽ የሰዎችን ለስሜታቸው መገዛትን ያስገነዝብሻል። ታሪክሽም ሆነ አሁንሽ አስተማሪ ነውና የተሻለችውን አንቺ ፍጠሪበት።

አዎ! ትናንትህ፣ የቀደመ ታሪክህ፣ ያለፈ ስቃይና ብሶትህ ባይኖሩ አንተም አትኖርም። አንተ ማነህ? የሚጨበጥ የሚዳሰሰው፣ አይን አፍንጫ አፍ እግር እጅ ያለው አካልህ አይደለህም። አንተ መንፈስህን ነህ፤ ስሜትህን ነህ፤ ማንነትህን ነህ፤ ስብዕናህን ነው። አካልህ ቢገድብ አስተሳሰብህ አይገደብም፤ ሰውነትህ ቢታሰር አዕምሮህ አይታሰርም፤ እጅ እግርህ ቢጎዳ ማመዛዘን አታቆምም። ይህን ገደብ አልባው ማንነት ደግሞ አንተ ነህ። በታሪኮችህ ተሰርተሃል፤ በውጣውረዶችህ ተገንብተሃል፤ በከፈልከው ዋጋ ለዚህ በቅተሃል። አሁን ከሁለት አንዱ ሰው መሆንህ አይቀርም። አንድ ታሪክህ የሰራህ፣ ሁለት ታሪክ እየተሰራብህ ያለህ። ሁለቱም በጊዜያቸው እጅጉን በጣም አስተማሪና የሚያንፁ ናቸው። ታሪክህ ቢሰራህ ዳግም የቀድሞ ስህተትና ስቃይ ውስጥ የመግባት እድልህ ይቀንሳል፤ ታሪክ ቢሰራብህ አዲስ ማንነት እየተሰራ እንደሆነ አስበህ ሁኔታዎቹን አምነህ መቀበልና ከእነርሱ መማር ይኖርብሃል።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
5.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 05:09:33 በጥልቀት ቆፍር!

"አሸናፊዎች እስኬት ይጓዛሉ?" ብለህ ብትጠይቅ "እስከ አሸናፊነታቸው" ትባላለህ፤ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መዳረሻቸው የት ነው?" ብትል "በገነቡት ማንነት ተፅዕኖ መፍጠር የጀመሩበት ቦታ" ትባላለህ፤ "መሪዎች መጨረሻቸው የት ነው?" ብትል "የሚመሩትን አካል መርተው የሚያደርሱበት ከፍታ" ትባላለህ፤ "ጠንካራ ተማሪዎች እስኬት ይማራሉ?" ብለህ ብትጠይቅ "የሚያኮራቸው የእውቀት ደረጃ እስኪደርሱ" ትባላለህ። ያንተስ ጉዞ እስኬት ነው? ለምን ጀመርክ? ለምንስ በዚህ ልክ ትፋለማለህ? ለምን በዚህ ልክ ዋጋ ትከፍላለህ? ውስጥህ እንዳታቆም እየገፋህ፣ ደጋግሞ እየታገለህ፣ እንቅልፍ እየነሳህ፣ ዋጋ እያስከፈለህ ከሆነ በእርግጥም ብርቱ የማይበገር ሃይል አግኝተሃል፤ ፅኑ የማይናወፅ ድጋፍ ተሰጥቶሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ውስጣዊ ድጋፍ ካለህ፣ ስሜት የሚሰጥህን ተግባር ከጀመርክ፣ የምታገኘው ገቢ ካላሳሰበህ፣ ተቀባይነት ማግኘትህ ካላስጨነቀህ ያለምን ፍረሃት፣ ያለምንም መሳቀቅና ድካም በጥልቀት አርቀህ ቆፍር፤ እስከጥግ ተፋለም፤ እስከመጨረሻው ታገል። ተስፋ መቁረጥ፣ ወደኋላ መመልከት፣ በታሪክ መታሰር፣ በቀድሞ ማንነት መታቀብ የሚባሉ ነገሮችን እርሳቸው። ድሮ በዚህ ማንነት ላትታወቅ ትችላለህ፣ አሁን ግን መታወቅ ትጀምራለህ፤ ቀድሞ ለፍረሃት እንደ ምሳሌ ልትታይ ትችላለህ፣ ዛሬ ግን በድፍረትህ እስከመወደስ ትደርሳለህ፤ በፊት በተጠራህበት ቦታ ሁሉ ትገኝ ይሆናል፣ አሁን ግን ውድነትህ ለብዙዎች እየገባቸው ይመጣል። ዋጋ መክፈል ካለብህ ከላይ ከላይ፣ ለነገሩ፣ እንዳይቀር የሚባል ነገር የለም። በጅማሬህ ከተማመንክ ጉዞህ እስከ ፍፃሜው ነው፤ በሃሳብህ ትልቅነት ጥርጣሬ ከሌለህ ተግባርህ ጥም ቆራጭ፣ አንጀት አርስ መሆን ይኖርበታል።

አዎ! ትልቅ ህልም ኖሮት የሚተኛ ሰው የለም፤ ከእራሱ በላይ ለሰዎች መኖርን ግቡ አድርጎ በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጥ አይኖርም፤ የተፈጠረለት አላማ ኖሮ መሞት ብቻ እንዳልሆነ የተገነዘበ ሰው በፍፁም አላማውን ሳይኖር ማለፍ አይችልም። እውቀቱ ወደ ተግባር ይገፋዋል፤ ተነሳሽነቱ ለአላማው ያቀርበዋል፤ እያንዳንዱን ቀኑን በሙላት እንዲኖር ያደርገዋል። የውልደትህ ምክንያት ታላቅነት እንደሆነ አስታውስ፤ ወደ ምድር የመጣሀው ለእራስህ ብቻ ኖረህ ለማለፍ እንዳልሆነ አስታውስ፤ በህይወት መኖርህ ሸክም ሳይሆን በረከት እንደሆነ እወቅ። እግዚአብሔር ዋጋ ያለው የተለየ ድንቅ የሰው ልጅ አድርጎ ፈጥሮሃል፤ አምላክህ በሚያምር ማንነት፣ በሚገርም ክብር፣ እጅግ በሚወደድ ጥበብ አበጅቶሃል። ክብርህን ማስጠበቅ፤ ለላቀ ደረጃ መብቃት ያንተ ድርሻ ነው። በጥልቀት መቆፈርህን እንዳታቆም፤ እራስህን ከመፈለግ እንዳትገታ፤ በምክንያት ተፈጥረሃልና ለምክንያትህ፣ ለህይወት አላማህ እስከመጨረሻው ተፋለም።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 05:23:29 አይንህን ግለጥ!

ወደኋላ ዞረህ እራስህን ስትመለከት ምን ይታይሃል? ብዙ ርቀት ወደፊት ተጉዘሃል ወይስ እዛው አካባቢ በቅርብ ርቀት ነህ? ሃሳቦችህን በሚገባ አሳክተሃል ወይስ ከነጭራሹ ትተሃቸዋል? አምስት አመታትን ወደኋላ ስትቆጥር የነበሩ ችግሮችህ ዛሬም አሉ ይሆን? ያኔ ሲያስጨንቁህ የነበሩ ጉዳዮችስ ከምን ደረሱ? በጊዜ ፍጥነት ነገሮች በቶሉ ይቀያየራሉ። የሆነ ጊዜ እራስን ማወቅ፤ እራስ ላይ መስራት፣ እራስን ማዳን፤ ከእራስ በላይ ለሰዎች መኖር የሚባለውን ነገር አናውቀውም ነበር። ዛሬ ግን ህይወት በእራሷ በተግባር እያስተማረችን ነው። ዝም ብሎ በዘፈቀድ መኖር፣ ያለምንም እቅድና አላማ ምድር ላይ መመላለስ ህይወትን የባሰ ከባድና ውስብስብ እንደሚያደረግው እራሷ ህይወት በሚገባ አስረድታናለች።

አዎ! ጀግናዬ..! አይንህን ግለጥ፤ በአፅንዖት መመልከት ጀምር፤ እራስህን በሚገባ መርምር። ከአመታት በፊት የነበርክበት ስፍራ ነህ ወይስ እየተጓዝክ ነው? ዛሬም ባለፉት አመታት ችግሮችህ ተከበሃል ወይስ ከእንቅስቃሴህ ጋር ከተቀየሩ አዳዲስ ችግሮችህ ጋር ነህ? የት ነበርክ? የትስ አለህ? ምን ይዘሃል? ከምንስ ደርሰሃል? እድሜ እስከጨመረ ድረስ የፊት ገፅታ፣ የሰውነት አቋምና ድምፅ መቀየሩ አይቀርም። ዋናው ቁብነገር ግን እርሱ አይደለም። በግል ስብዕና፣ በአመለካከት፣ በአስተሳሰብ ልኬት፣ በማስተዋል ችሎታ እራስህ ላይ የተመለከትከው ለውጥና እድገት ምንድነው? ምናልባት በቻልከው መጠን ትጥር ይሆናል፤ ብዙ ስራ እየሰራህ፣ ብዙ ወዳጆችህን አፍርተህም ይሆናል። ሂደቱ ካልሰራህ ግን እራስህ ቆም ብለህ ማሰብ ይጠበቅብሃል።

አዎ! ምንም ቢሆን አንተን የማይቀይር፣ እሴት የማይጨምርብህ፣ ዋጋህን ከፍ የማያደርግ፣ ካለህበት ቦታ ፈቀቅ የማያደርግህ ጥረት ምንም ትርጉም የለውም። ከፍጥነቷ የተነሳ ህይወትን ትናንት ብለን ዛሬ ለማለት ጊዜ ልናጣ እንችላለን፤ ያለምንም ቁብነገርና አለማ የሚደረግ ሩጫ ደግሞ ጠዓም እያሳጣት በብዙ እጥፍ ያሳጥራታል። የመኖርህን ትርጉም ለመረዳት ጊዜ አታጥፋ፤ አይንህን በቶሎ ግለጥ፤ እርሱን ለማወቅ ማድረግ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ። በዚህ ጉዳይ ቀጠሮ ሰጠህ ማለት ህይወትህን ሙሉ፣ ትርፋማ፣ አስደሳችና በእግዚአብሔር የተወደደ ለማድረግ እያቅማማህ እንደሆነ እወቅ። ህይወትህን መቀየር እንደምትችል፣ የተሻለ ስፍራ ማድረስ እንደምትችል ማወቅህ ብቻ በቂ አይደለምና ውስጥህ የሚመላለሰውን ግሩም ሃሳብ በመተግበር በመግለፅ እውቀትህን ተግባራዊ አድርገው።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
5.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 05:22:55 ያልተሰጠህን ለእራስህ ስጥ!

ብቻህን ትጓዛለህ ቢሆንም አትፈራም፤ ብቻህን ትለፋለህ ቢሆንም አትጨነቅም፤ ብቻህን ትኖራለህ ቢሆንም በእራስህ መቆም አይከብድህም፤ በችግሮችህ መዋል ማለፍ ትችላለህ፤ ብዙዎች ባያምኑብህ በእራስህ ትተማመናለህ፤ ማንም ባይደግፍህ እራስህን ትደግፋለህ፤ ማንም የተሻለ ቦታ ባይሰጥህ ለእራስህ ግሩም ቦታ ትሰጣለህ። ያጣሀውን ለእራስህ አድርግ፤ ያልተሰጠህን ለእራስህ ስጥ። ብቻህን ነበርክ ዛሬም ዳግም ብቻህን መቅረትህ ሊደንቅህ አይገባም። ሰዎች ይመጣሉ በፊት እንደነበርከውም ብቻህን ጥለውህ ይሔዳሉ። ብቸኝነትን ተለማመድ፤ ከሌሎች ስታገኘው የነበረውን ነገር ከእራስህ ለማግኘት ሞክር። በእርግጥ ሰው የሚሰጥህን በሙሉ ከእራስህ ላታገኝ ትችላለህ ከልቡ አምኖበት፣ ፈልጎና ወዶ የሚሰጥህ እስኪመጣ ግን ለእራስህ በፍፁም አንሰህ እንዳትገኝ። ለእራሱ፣ በእራሱ ደስተኛ፣ ጠንካራ ብርቱ የሆነ ሰው ከውድቀቱ እንዴት ማገገም እንዳለበት፣ በምንያክል ፍጥነት ዳግም መነሳት እንዳለበት፣ እንዴት እራሱን ዳግም ማግኘት እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ያልተሰጠህን ለእራስህ ስጥ! ከሌሎች ጠብቀህ ያጣሀውን፣ ስትናፍቀው ያስቀሩብህን፣ እያስፈለገህ የተነፈከውን ነገር ለእራስህ በእራስህ ለመስጠት ቆርጠህ ተነስ። በሰዎች ችግር ምክንያት፣ በሰዎች ፍላጎት ማጣት፣ በሰዎች ፊታቸውን ማዞር ማላዘንህን አቁም፤ እራስህን መውቀስ አቁም፤ እራስህን ተጠያቂ ማድረግ አቁም። ይህ ጊዜ ብቸኝነትህን በሚገባ የምታከብርበት፣ ማየት ለሚገባቸው፣ ማየት ለሚፈልጉ ትክክለኛውን ማንነትህን የምታሳይበት ጊዜ እንደሆነ እወቅ። ብቻውን የፈለገውን ነገር ማድረግ የሚችልን ሰው የትኛውም ጫና ሊያስቆመው አይችልም፤ የትኛውም አይነት በደል ወደኋላ ሊያስቀረው አይችልም። ብቻህን ስትሆን ፍፁም የተለየህ ሰው ትሆናለህ፤ ፍፁም ከዚህ በፊት የማትታወቅ ላንተም ለሌላውም አዲስ ሰው ትሆናለህ።

አዎ! ድጋፍ ማጣትህ ያጠነክርሃል፤ የሚያምንብህ አለመኖሩ በእራስህ እንድታምን ያነሳሳሃል፤ በሰዎች መገፋትህ እግዚአብሔር አምላክህን እንድትጠጋ ያደርግሃል፤ ተቀባይነት ማጣትህ እራስህን ከነድክመቱ እንድትቀበለው ይጠቁምሃል። ብቻህን ስትጓዝ አብሮህ ያለው አምላክህ ነውና መከዳት የለም፤ መገፋት አይኖርም፤ ድራማ የለም፤ በሰዎች ስሜት ምክንያት ዋጋ መክፈል አይኖርም። ብቻህን እራስህ ላይ ትሰራለህ፤ ብቻህን እራስህን ታጠነክራለህ፤ ብቻህን ማን እንደሆንክ፣ ምን ማድረግ እንደምትችል ታሳያለህ። በስተመጨረሻም የእውቁ ደራሲ የዋይኒ ዳየርን ንግግር አስታውስ፡ "ብቻህን ስትሆን አብረሀው የምትሆነውን ሰው ከወደድከው በፍፁም ብቸኛ ልትሆን አትችልም።" ያንን ሰውም አንተ ሁን፤ በህይወትህ በጣም የምትፈልገውን ሰው እራስህ ሁን፤ እራስህ ላይ በመስራትህ የሚያኮራህን አይነት ሰው ሆነህ ተገኝ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 05:22:15 ፍላጎትህን አቃና!

ቀላል ህይወት እንዲኖርህ ከፈለክ፣ ቀላል የህይወት መርህ ያስፈልግሃል። አንደኛውም መርህ ከሰዎች የምትጠብቀውን ነገር ይዳስሳል። ማንም መወደድን የሚጠላ፣ ተቀባይነትን የሚጠየፍ፣ መከበርን የሚገፋ ሰው የለም። ነገር ግን ፍላጎቱ ስህተት መሆን የሚጀምረው ያየው ሰው ሁሉ እንዲወደው፣ ስራውን የተመለከተው ሰው ሁሉ እንዲያደንቀው፣ የሰማው ሁሉ እንዲከተለው መፈለግ የጀመረ እለት ነው። ይህን መርህ ይዘህ ከህመም በቀር ምንም ልታተርፍ አትችልም። ምክንያቱም አንተ እራስህ የማትተገብረውን ነገር ከሰዎች እየጠበክ ነውና ነው። ማንም ብትሆን የእራስህ ስሜትና ፍላጎት አለህና ሁሉንም ሰው ልትወድ፣ ሁሉም ሰው የሚናገረውን ልታዳምጥ፣ የሁሉም ሰው አድናቂና ተከታይ ልትሆን አትችልም። የምትወደው ሰው እንደመኖሩ የማይመችህና ምርጫህ ያልሆነ ሰው አለ። ይህም በሰውነቱ ሳይሆን በተግባሩ ነው።  ስለዚህ ከፍላጎትህ ጋር የሚሄደውን፣ ለአላማህ የሚጠቅምህን፣ ንግግሩ ፍሬ ነገር የሚሰጥህን ሰው ትሰማለህ፣ ትወዳለህ፣ ትቀበላለህ ሌላውን ትተዋለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ፍላጎትህን አቃና! ምኞትህን ፈር አስይዝ፤ የህይወት መመሪያህን ከአቋምህ ጋር አስኪድ፤ ከተግባርህ ጋር አጣጥም። አንተ የማትፈፅመውን ተግባር ሌሎች እንዲፈፅሙልህ አትጠብቅ፤ እራስህ የማትሆንላቸውን ገፀባህሪ እነርሱ እንዲሆኑ አታስገድዳቸው። አንተ ስትፈልግ ቀላልና መደረግ ያለበት ግዴታ፣ ሌሎች ሲፈልጉ ደግሞ በፍላጎትህ ልክ በምርጫ የምታልፈው ነገር የለም። ከሌሎች የምትጠብቀውን ነገር ሌሎች ካንተ እንደሚጠብቁ ብታውቅ ምንያክል ልታደርግላቸው ዝግጁ እንደሆንክ እራስህን ጠይቅ። እራስህ ባስቀመጥከው ሚዛናዊ ያልሆነ መርህ አትሸነፍ፤ መልሶ አንተኑ በሚያጠቃህ አቋም እራስህ አትገድብ።

አዎ! ለደስታህ ሲባል መርሆችህ በሙሉ ደጋፊህና ከገሃዱ አለም እውነታ ጋር የሚሔዱ ሊሆኑ ይገባል። ሰዎች እንደማያደርጉልህ እያወክ ስለምን ደጋግመህ እነርሱን እየጠበክ እራስህን ትሰብራለህ? በፍላጎቶችህ ከደብ ማጣት ስለምን ለጭንቀትና ብሶት እራስህን ታጋልጣለህ? ከውጭ የምትፈልገው ነገር ቢኖር ቅድሚያ ውጥህ እንደሌለና ለእራስህ እንዳላደረክ እርግጠኛ ሁን። እግዚአብሔር ከሚሰጥህ፣ አምላክ ከሚያድልህ ነገር በቀር አንዱም ከሰዎች የሚመጣ ነገር አብሮህ አይቀርም። ውጫዊ መሻትህን ገድብ፤ ከእራስህ የምትጠብቀው ነገር ላይ አተኩር፤ መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ እውነታ አንፃር ህይወትህን ቀለል አድርገህ ኑር።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.2K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 05:21:47 ህመምህን እቀፈው!

እራስን የመግዛትን ህመም፣ እራስን የማሰቃየትን ህመም፣ ጨክኖ ለአላማ የመታገልን፣ እስከ ጥግ የመፋለምን፣ እንቅልፍ የማጣትን፣ ዋጋ የመክፈልን፣ ህይወትን በመርህ የመምራትን፣ እራስ ላይ ለመሰልጠን የመታገልን ብርቱ ህመም እቀፈው። ማንበብ አልተመቸኝም ብለህ አዋቂ ልትሆን አትችልም፤ ማጥናት አልፈልግም እያልክ ለውጤት አትበቃም፤ ምቾቴ ይሻለኛል እያልክ ስኬትን አታገኝም፤ በሁሉም መወደድን እየፈለክ ለእራስህ መሆን አትችልም። እያንዳንዱ ትልቅነትን አስበህ፣ ስኬትን ተመኝተህ እራስህን የምትሰጥለት፣ ማንነትህን የምትሰዋለት ተግባርህ ብርቱ ህመም አለው፤ ያሰቃይሃል፤ ያደክምሃል። ከስቃዩ ጀርባ ግን እውነተኛውን አንተ ታገኘዋለህ፤ ከህመምህ ኋላ ነፃነትህን ታውጃለህ፤ ከድካምህ ስታልፍ ስኬትህን በእጅህ ታስገባዋለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ህመምህን እቀፈው! የምትሰራበት፣ የምታድግበት፣ የምትታነፅበት ከሆነ ከህመምህ ለመወዳጀት፣ ስቃይህን ለማቅረብ፣ ከማንነትህ ለማዋሃድ ጊዜ አትፍጅ። ፍጠን! ከህመምህ ተላመድ፤ ፍጠን! በእርሱ መደሰት ጀምር፤ ፍጠን እራስህን ገንባበት። እያደክ መሆንህን ለህመምህ የምትሰጠውን ምላሽ እየተመለከትክ ታውቀዋለህ። በእርግጥም ልዩ የሚያደርግህ፣ ልዩነት ፈጣሪ የሚያደርግህ ከዲሲፕሊን ስቃይ ጋር ያለህ የጠበቀ ግንኙነት ነው፤ ከአላማህ ጋር ያለህ ፅኑ ትስስር ነው፤ በጊዜያዊ ፍላጎቶችህ አለመሸወድህ ነው፤ ለውጫዊ ጫጫታ እጅ አለመስጠትህ ነው፤ ባለህ መጀመርህ፣ በሂደቱ መማረክህ፣ በእራስመተማመንህ ነው። መኖርን ብቻ አልመረጥክም፤ ምርጫህ ደስተኛ ህይወት ነው፤ ምርጫህ ትርፍ ያለው፣ ለብዙዎች የሚያበቃህ ተዓምረኛና ስኬታማ ህይወት ነው።

አዎ! በምክንያት ትሰቃያለህ፤ በምክንያት ትደማለህ፤ በምክንያት ትገፋለህ፤ ትጠላለህ፤ በምክንያት ትመታለህ። የምክንያትህ ግዝፈትም ህመምህን እንድትቋቋም ያደርግሃል፤ ቁስልህን እንድትችለው፣ ስቃይህን እንድታልፈው ያደርግሃል። ብትወድቅ መነሳት እንደምትችል ታውቃለህ፤ በብዙዎች ፊት ዋጋ ብታጣ ለእራስህ የማይተካ ስፍራን ትሰጣለህ፤ መሰናክሎችህ ቢበዙ በፍፁም እጅ አትሰጥም። በማጣት መሃል ቀና ማለቱን ትችልበታለህ፤ በሽንፈትህ ላይ ለድል መብቃቱን ታውቅበታለህ፤ በህመመ ውስጥ ፈክቶ መውጣቱን ትችልበታለህ፤ በጨለማ መሃል ብረሃንህን መግለጥህን ታውቅበታለህ። የሚያቆመኝ የለም ባልክበት ቅፅበት የሚያቆምህ ይጠፋል፤ ብቻህን መጓዝህ አያሳስብህም። ብቻህን ትጋፈጣለህ፤ ብቻህን ታሸንፋለህ፤ የድልህን ፅዋም በኩራት ትጎነጫለህ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 05:21:15 በይቅርታ ቋጨው!

መረጋጋት ትፈልጋለህ? ውስጥህ ሰላም እንዲሰማው፣ እረፍት እንዲኖረው ትመኛለህ? በትክክለኛ አቅሙ እንዲገለጥ፣ የሚመኘውን ህይወት እንዲፈጥር ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ምንም ከመጀመርህ በፊት፣ ወዴትም ከመጓዝህ አስቀድሞ እራስህን ይቅር በል፤ ለእራስህ ሃዘኔታ ይኑርህ፤ ከእራስህ ጋር ታረቅ፤ ከልብህ ወግንለት፤ በሚገባ ደግፈው። ምን በድዬው? ምን ነስቼው? ምንስ አሳጥቼው? ልትል ትችላለህ። ነገር ግን እራስህን በጥሞና ስትመለከት ዛሬ ላለህበት አስጨናቂና ፀፀት የተሞላበት ደረጃ ላይ ለመገኘትህ ካንተ በላይ ተጠያቂ ሰው የለም። ለእራስህ ውድቀት ማንን ትጠይቃለህ? እራስህ ላይ በመጨከንህ? ጊዜያዊ ደስታህን በማሳደድህ ማን ማንን ጎዳው? ማንስ በዳይ ማን ተበዳይ ሆነ?

አዎ! ጀግናዬ..! ከእራስህ ታረቅ፤ ጉዳዩን በይቅርታ ቋጨው! ሁለት ሆነህ እየኖርክ፣ አንዱ በዳይ አንዱ ተበዳይ፣ አንዱ አጥፊ ሌላኛው ጠፊ፣ አንዱ ከሳሽ ቀሪው ተከሳሽ ሆኖ እየቀረበ ህልምህን ልታሳካ፣ አላማህን ልትኖር፣ ለሰዎች መትረፍ አትችልም። በየሰዓቱ በሚቀያየር ሃሳብ፣ በየጊዜው በሚምታት አቋም፤ ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ በሚሆን ውሳኔ በፍፁም ወደፊት ልትጓዝ አትችልም። ለእራስ የሚደረግ ይቅርታ እስከመርሳትም ሊደርስ ይችላል። የሆነ ጊዜ ባጠፋሀው ጥፋት ለረጅም ጊዜ እራስህን እየወቀስክና በእራስህ እየተናደድክ በቀጠልክ ቁጥር ሃይልህን ታጣለህ፤ ትኩረትህ ይበተናል፤ ውሳኔና ተግባርህ ይጋጫል።

አዎ! ሁኔታህን የምታከብደውም ሆነ የምታቀለውም አንተው እራስህ ነህ። እራስህ ላይ ቂም ይዘህ የትም አትደርስም። እንኳን ለእራስህ ይቅርና ለስንተ ሰው ይቅርታ አድርገሃል፤ እራስህን በማስቀደም ከጫወታው በሰላም ወጥተሃል። ካባድ ሊሆን ይችላል፤ አዲስ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ምንም ዋጋ ቢያስከፍልህ ለምታገኘው ውስጣዊ ሰላምና እርካታ ብለህ ከእራስህ ጋር ታረቅ፤ ዘወትር ደጋግመህ የምትከሰውን ጥፋተኛ ማንነትህን ይቅር በለው፤ ወደ እራስህ አስጠጋው፤ የበደለኝነት ክሱን አንሳለት። ለእራስህ ማዘን ሳትችል "ለሰዎች አዝናለሁ" ብትል ውሸት ነው። እራስህን ጥለህ፣ ብቸኝነትህን እየተጠየፍክ፣ ታሪክህን እየኖርክ ለሰው ቀርቶ ለእራስህ ለመትረፍ አትበቃም። የትም ከመሔድህ በፊት የቤትስራህን እራስህ ጋር ጨርስ፤ የእራስህን ጉዳይ እልባት ስጠው፤ በይቅርታ ቋጨው
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 05:19:25 በተግባርህ አሸንፍ!

ምርጫህ የማይመቸው፣ ውሳኔዎችህ የማያስደስተው፣ ተግባርህ የማያረካው መሃበረሰብ ውስጥ ካለህ ብዙ ምርጫ የለህም። ደጋፊ በማጣትህ ውሳኔህን ትጥላለህ ወይም ብቻህን ተጋፍጠህ ታልፈዋለህ። ተቃውሞህን ለማሸነፍ፣ ተቃርኖህን ጥሎ ለማለፍ ብዙ ተዓምር መስራት፣ ያልሆንከውን መሆን፣ ከአቅምህ በላይ መንጠራራተት፣ ለማሳመን መጣጣር አይጠበቅብህም። ተግባርህ ከበቂ በላይ ነው፤ ተጨባጩ ስራህ ሁሉንም ያስተካክላል፤ እራስህን ለእርሱ አሳልፈህ መስጠትህ ከባዱን ሁኔታ ያሻግርሃል። ማድረግ እንደማውራት ቀላል እንደማይሆን ታውቀዋለህ። ለማድረግ ስትነሳ እንደምትጨርሰው ውስጥህ ማመን ይኖርበታል፤ መሰናክሎችህን እንደምትሻገር ማመን ይጠበቅብሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! በተግባርህ አሸንፍ! አዲስ ተግባር፣ አዲስ ማንነት፣ የተለየ አካሔድ፣ የተለየ ስራ እጅግ በጣም ብዙ ፈተና ይኖረዋል። ቤተሰብ አይረዳህም፤ መሃበረሰቡ ቶሎ አይቀበልህም፤ ውጤቱን ቶሎ አትመለከትም፤ ተቃዋሚህ ይበዛል፤ የሚተችህ እልፍ ነው፤ ችግርህን የሚቆጥርልህ ከዙሪያህ አይጠፋም፤ ውስጥህ ቢታገልም ውጪ በሚመለከተው ነገር ብዙ ይፈተናል። ከዚህ ሁሉ ተቃሞና ፈተና በስተጀርባ በእራስመተማመን የተባለውን ወሳኝ ነገር ያታግልሃል። እንደምትችለው ብታውቅም የሚወራብህን እየሰማህ፣ የሚሰጥህን አስተያየት እየተቀበልክ፣ የጠቆረብህን ፊት እየተመለከትክ፣ የሚያሽሟጥጡብህ ላይ እያተኮርክ ለመውደቅ ትንገዳገዳለህ፤ ለማቆም ታማትራለህ፤ ተስፋ ለመቁረጥ ትሰናዳለህ። ከውስጣዊ መሻትህ በላይ ውጫዊው ምላሽና ገፅታህ እራስህን እንድትጠራጠር ያደርጉሃል።

አዎ! ተግባርህ ግን ለሁሉም ምላሽ አለው፤ ስራህ ግን ለሁሉም መልስ ይጠሳል፤ የማያቋርጠው ጥረትህ የተቃዋሚህን አፍ ያዘጋል፤ ውጤትህ ውጫዊ ተቃርኖህን ያርቀዋል። ጠንክረህ የምትሰራው አንድም ህልምህን እውን ለማድረግ ሲሆን ሌላም ተቃውሞህን ለማስታገስ ነው። ማንም በተቃራኒህ ቢቆም፣ ማንም መንገድህን ቢዘጋብህ ከእርሱ ጋር ሰጣ ገባ ውስጥ መግባት አይጠበቅብህም፤ እርሱን ለማሳመን ላይ ታች ማለት አይኖርብህም። በጀመርከው መንገድ መቀጠል፣ ለህልምህ መታገል፣ ለአላማህ መወገን፣ ራዕይህን ማስኬድ፣ ወደፊት ብቻ መመልከት፣ አሰናካዮችህን ማስወገድ ብቻ በቂ ነው። "አትችልም" ብትባል ቆመህ መቻልህን በቃላት ስብጥር፣ በአርፍተ ነገሮች ህብረት አታስረዳም። ችሎታህን የሚያሳየው ሁነኛው መንገድህ ተግባርህና ተግባርህ ብቻ ነው። በተግባርህ አሸንፍ፤ ተቃውሞህን በውጤትህ ቀልብስ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 05:17:51 ለእራስሽ ድረሺላት!

ለሚያይሽ ሁሉ የደላሽ፣ የተመቸሽ፣ ህይወት አልጋ በአልጋ የሆነልሽ ትመስያለሽ፤ ነገር ግን ውስጥሽን አንቺ ታውቂያለሽ፤ ህመምሽን፣ የልብ ስብራትሽን፣ ቁስልሽን አንቺ ትረጂዋለሽ። ፊትሽ ፈክቶ፣ ጥርስሽ ስቆ፣ ገፅሽ አብርቶ ህመምሽን ባያክም፣ ቁስልሽን ባያደርቅ፣ ብሶትሽን ባያስተነፍስ ምን ዋጋ አለው። ሰው ባየሽ ሊያውቅሽ ይሞክራል ነገር ግን በፍፁም ሊያውቅሽ አይችልም፤ በንግግርሽ ሊገልፅሽ ይጥራል ነገር ግን በፍፁም ንግግርሽ ውስጥሽን አይወክልም። አንዳንዴ ድብብቆሽም ይደክማል። ለማን ብለሽ፣ ምን እንዳይመጣ ብለሽ በውስጥ እያረርሽ በውጭ እንደምትስቂ አታውቂውም። በብዙ ሰዎች ተከበሻል ነገር ግን ማንም ህመምሽን ሊረዳሽ አልሞከረም፤ ጊዜ ሰጥቶ አላዳመጠሽም፤ ትኩረት ሰጥቶ አልተከታተለሽም። እንዲሁ እንደሚያይሽ የደላሽ ትመስይዋለሽ፤ የሰው ልጅ ከበላ ከጠጣና ለብሶ ካማረበት ማንም ችግር አለበት እርዳታ ያስፈልገዋል ብሎ አያስብም።

አዎ! ጀግኒት..! ለእራስሽ ድረሺላት፤ እራስሽን አድኚ። ሁለት ሰው ሆነሽ፣ ሁለት ገፅ ኖሮሽ ከእራስሽ በቀር ማንም እንደማያድንሽ እወቂ። ሰዎች ሃሳብ ሊሰጡሽ ይችላሉ፤ ሊመክሩሽ ይችላሉ ነገር ግን በፍፁም ህመምሽን አይታመሙልሽም፤ ስቃይሽን አይሰቃዩልሽም። ብቻሽን እንደሆንሽ እያሰብሽ እራስሽ ላይ አትጨከኚ፤ በገዛ ፍቃድሽ እራስሽ ላይ የህይወትን ክብደት አትጨምሪ። ከአምላክሽ ቀጥሎ ለእራስሽ ያለሽው አንቺ እንደሆንሽ እወቂ። ዘወትር ብቻዋን ስትሆን ቁስሏ የሚቀሰቀስባት፣ ህመሟ የሚያገረሽባት፣ በማስመሰል አለም የምትሰቃየዋ ምስኪን ሴት አታሳዝንሽም? እርሷስ ብትሆን ካንቺ በቀር ማን አላት? ማን ደርሶ ከስቃይዋ እንዲገላግላት ትጠብቂያለሽ? ጊዜ አትፍጂ፣ የህመም፣ የስቃይ ወቅትሽን አታስረዝሚ። እራስሽ ላይ በመጨከን፣ ህይወትሽን ይበልጥ በማወሳሰብ ምንም አታገኚም። ለእራስሽ ብለሽ ህመምሽን ተንፍሺ፣ ለእራስሽ ብለሽ ፍረሃትሽን ተጋፈጪው፤ ለእራስሽ ብለሽ ከአስጨናቂ ሃሳቦችሽ ፋታ ውሰጂ።

አዎ! ጀግናዬ..! ብዙ ሸክም አለብህ፤ ቀላል የሚመስሉ ነገሮች ፋታ ነስተውሃል፤ የህይወት ፈተና ተወሳስቦ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶሃል። ገፅህና ውስጥህ እጅጉን ተራርቀዋል። የቤተሰብ ጉዳይ፣ የትምህርት፣ የግንኙነት፣ የስራ፣ የገንዘብ ችግር ተደራርበው ስለእራስህ እንኳን እንዳታስብ አድርገውሃል። አንደ ነገር ግን አስታውስ ሁሉም አሳሳቢና አስጨናቂ ነገር የሚመጣው ካንተ ቦሃላ ነው፤ ያንተ ህልውና ከምንም ነገር በላይ ነው፤ ቀዳሚም ነው። እራስህን ተደብቀህ አትችለውም፤ ለእራስህ እያስመሰልክ አታመልጠውም። ለውስጥ ህመምህ እረፍት ካልሰጠህ፣ ቁስልህን ካላከምከው የህይወትህ ጨለማነት እንዲሁ እንደቀጠለ ነው። ብዙ ሰዎች ያሉበት ሁኔታ ውስጥ ነህና አትረበሽ፤ የገጠመህ ጉዳይ መፍተሔ አለውና በእራስህ ተስፋ አትቁረጥ፤ የሃዘንህ መቋጫ ቅርብ ነውና ቀና በል። ያንተን ጉዳይ ጉዳዬ ብለው ሊያነሱህ የሚመጡ ባይኖሩም አንተ ለእራስህ ድረስለት፤ ካቀረቀረበት አንገቱን ቀና አድርገው፤ ሲፈራው የነበረውን ነገር ተጋፈጥለት፤ የውስጥ ብሶቱን አውጣለት፤ ተንፍስለት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.9K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 07:48:07
ሳይበረታ ድረስ
አየኸው ዝናቡን አንተን ሲያስታውሰኝ
ካለፈው ትዝታህ ወስዶ ሲመልሰኝ
ተመለከትክልኝ የብርዱንስ ብርታት
አንተን እያስመኘ ሲናፍቅ ቀን ከሌት
አስተውለኸዋል የበረዶውን ዶፍ
ወደነዛ ቀናት የዃሊት ሲያከንፍ
አየህልኝ ውዴ ክረምቱ በረታ
ልቤም አንተን አለኝ ፍቅርህ ልቤን ረታ

#_ታድያልህ_አለሜ
ናፍቆትህ በርትቶ ካልጋ እንዳላድር
በትዝታህ ባህር ሰምጬብህ ሳልቀር
ዝናቡ ሳይጠና ብርዱም ሳይጠነክር
ሳይበረታ ድረስ ህመሜም እንዲሽር።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
7.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ