2023-05-11 20:46:19
መቼ ነበር?መቼ ነበር ለእራስህ ትልቅ ነገር ያደረከው? መቼ ነበር የሚያኮራህን ተግባር የፈፀምከው? መቼ ነበር ከልብ የሚያስደስትህን ስራ ያከናወንከው? መቼ ነበር በእራስህ ምክንያት ሙሉና ደንቅ ሰው እንደሆንክ የተሰማህ? መቼ ነበር በእራስህ የኮራሀው? ምንስ ስላደረክ በእራስህ ኮራህ? ምን ስለጀመርከ ወይም ምን ስላቆምክ ደስ አለህ? እርሱን ነገር አስታውስና አሁንም አድርገው፤ የቀድሞ ስሜትህን መልሰው፤ በእራስህ ሜዳ ላይ አሸናፊነትህን መልሰህ አግኘው። ያንተ መሆን የሚገባውን፣ ቀድሞ የምታውቀውን ማንነት ዳግም መፍጠር ጀምር። ቀድሞ በሚያስደስቱህ ነገሮች መደሰት የማይቻል፣ ያለፈበት ነገር ሊመስልህ ይችላል፣ ነገር ግን ዳግም እራስን ፈልጎ በማግኘት ዙሪያ ምንም ነገር ሊረፍድና ሊዘገይ አይችልም፤ ቀድሞ እንደነበረ መሆን ባይችልም በተለየ መንገድ ስሜቱን ማምጣት ይቻላል። የጎላ ጥረትህን ቢፈልግም ዳግምም መመለሱና እንደ ቀድሞ ይባሱንም ከዛም በላይ መሆኑ አይቀርም።
አዎ! ጀግናዬ..! ትልቁን የህይወት ደስታ ያጣጣምክበት፣ ለመኖርህ ትርጉም ያገኘህበት፣ በእራስህ ላይ እሴት መጨመር የቻልክበት፣ እራስህን ያወክበት ጊዜ
መቼ ነበር? ጊዜውን ማስታወስህ ስሜቱን ሙሉ ባያመጣውም በወቅቱ የተሰማህን ስሜት ግን ያስታውስሃል፤ ወደኋላ ተመልስህ እንድትታደስ ያደርግሃል፤ አሁንም ዳግም በእዛው መንገድ እራስህን ማግኘት፣ ማስተደሰት እንደምትችል ያስገነዝብሃል። ትልቁ ሃላፊነትህ እራስህን በምትፈልገው መንገድ መምራት መቻል እንደሆነ አስታውስ። የሆነ ጊዜ ትክክለኛው መንገድ ላይ ነበርክ፣ በአንድ ወይም በለተያየ አጋጣሚ ግን ከዛ መንገድ ልትወጣ ትችላለህ። ነገር ግን መንገድህን እንደሳትክ፣ በማይመጥንህ ስፍራ እንደተገኘህ፣ እራስህን እየገፋህ መቀጠል ካልፈለክ ወደ ትክክለኛው የጉዞ አቅጣጫህ መግባት የማትችልበት ምንም ምክንያት አይኖርም።
አዎ! ከባድ ነው፤ ነገር ግን የማይቻልና ከአቅምህ በላይ አይደለም። በእርግጥም ያንን የጥንካሬ ዘመንህን፣ አስደሳቹን ጊዜህን፣ የሚያኮራህን ተግባር ከልብህ ከፈለከው ካንተ በቀር እንዳታደርገው ሊከለክልህ የሚችል አካል አይኖርም። በትናንት ትዝታ መደሰት አንድ ነገር ነው፤ ነገ ጥሩ ትዝታ፣ አስደሳች ትውስታ መሆን የሚችልን ነገር ዛሬ ላይ መፍጠሩ ደግሞ እጅግ የላቀውና አመርቂው ተግባር ነው። በእራስህ ላይ ተስፋ አትቁረጥ፤ ምንም እንኳን በብዙ ውጣውረድ ውስጥ ብታልፍም ትናንትም አንተው ነህ፤ ዛሬም ያው አንተ ነህ። አሁን በሆነብህ ነገር አትደናገጥ፤ አሁን በሚሰማህ መጥፎ ስሜት አትሸበር፤ አትታወክ። እንደ አስፈላጊነቱ የቀደመውን አስደሳች ጊዜህን መልሰህ መፍጠር ሞክር፣ በእርሱም ውስጥ እራስህን ፈልገህ አግኝ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited 17:46