2023-05-11 20:50:09
አንተው መልስ ስጥ!ያንተን ጉዳይ ለእራስህ ስጥ፤ ያንተን ጥያቄ እራስህ መልስ፤ መሰናክልህን አንሳ፤ እንቅፋትህን አስወግድ፤ ችግርህን በእራስህ የመቅረፍን ልማድ አዳብር። አዳምጦ የሚስቅ ወይም የሚፈርድ እንጂ ለጉዳይ ቦታ የሚሰጥ ሰው እንደሌለ እወቅ። ችግርህን ችግሬ፣ ብሶትህን ብሶቴ፣ ማጣትህን ማጣቴ ብሎ ዋጋ የከፈለልህ፣ ላንተ ብሎ የተሰቃይ፣ አንተ ያየሀውን አበሳ ለማየት የተፋጠነ ሰው ማነው? ስትወድቅ እንኳን ሊደግፍህ የመጣ፣ ከጎንህ የቆመ ሰው ማነው? ብዙ ጉዳይ አስፈፃሚዎች አሉ፤ ጥቂቶቹም ካንተ በላይ ያስፈፅሙልሃል፤ ጥቂቶቹ ደግሞ አንተ ተጨናንቀህ እንኳን ከምታከናውነው ደረጃ ባነስ ያከናውኑልሃል። የማንንም ብቃት መወሰን ባትችል የምትችለው ነገር አንተ የምትችለውን ማድረግ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ከመናገርህ በፊት፣ ሁሉም ሰው እንዲረዳህ ከመፈለግህ በፊት አንተው እራስህን ተረዳው፤ ለእራስህ ጉዳይ አንተው እወቅበት፤ ችግርህን አንተው ፍታው፤ ለጥያቄህ
አንተው መልስ ስጥ። ያንተን ትግል ማንም አይታገልልህም፤ ያንተን ችግር ማንም አይፈታልህም። ለእራስህ ጉዳይ ብቁ እንደሆንክ የምታስመሰክረው አንተ ነህ። እየዞርን ጆሮ ለማይሰጠን ሁሉ ታሪካችንን፣ ችግራችንን፣ ብሶታችንን መተረክ መሳቂያ መሳለቂያና ማነፃፀሪያ ከመሆን በቀር ምንም አያተርፍልንም። የእራሱን ችግር አሸንፎ ላንተ መፍትሔ የሚያቀርብልህ፣ ሊረዳህ ዝግጁ የሆነ ሰው ብታገኝ እጅግ እድለኛ ነህ። ነገር ግን ማንንም ሰው ብታገኝ ካንተ በተሻለ ሊረዳህ እንደማይችል እወቅ።
አዎ! ሰዎች እንዲረዱት፣ ችግሩን እንዲቀርፉለት፣ ነፃ እንዲያወጡት አብዝቶ ከሚጠባበቅ ሰው በላይ የዋህ ሰው የለም። በእያንዳንዱ ጉዞህ አምላክህ አብሮህ ካለ፣ እርሱን ካስቀደምክ ሰዎችን የምትማፀንበትን ነገር ሁሉ እራስህ የማታደርግበት ምክንያት አይኖርም። ከሰዎች በላይ በአምላክህ ታምናለህ፤ በእርሱም ትታመናለህ። ከተከመረብህ የችግር መዓት፣ አስፎ ከያዘህ አጣብቂኝ ሁነት፣ መፈናፈኛ ካሳጣህ አስጨናቂ ጉዳይ ነፃ ትወጣለህ። ለረጅም ጊዜ ችግርህን እንዲቀርፉልህ ብዙ ሰው ጠይቀሃል፤ ብዙ ሰው እግር ስር ወድቀህ ተማፅነሃል፤ ከልብህ አልቅሰህባቸዋል ነገር ግን የጠበከውን ምላሽ አላገኘህም። አምላክህን ጠይቅ፤ እራስህን ጠይቅ፤ አምላክህን ተማፀን፤ ትክክለኛውን የገዛ ማንነትህን ተማፀን፤ ፈጥኖ ምላሽ የሚሰጥህ፣ ካንተ በላይ የሚያስብልህ አምላክህ ላይ አልቅስ። ከችግሮች በላይ በበረከት፣ ከጭንቀት በላይ በውስጣዊ ሰላም፤ ከሃዘን በላይ በሳቅ ትሞላለህ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited 17:50