2023-05-20 14:48:33
ማናችንም ነገ ምን እንደምንሆን አናውቅም ። ሀብት አያድነንም ፤ ውበት አያድነንም ፤ ጉልበት አያድነንም ፤ ስልጣን አያድነንም ፤ ማንም አያድነንም ።
ሳምራዊት እህታችን ለመኖር አገባች ፤ አግብታም ወለደች ። ትናንት ግን ከወራት ስቃይ በኋላ አረፈች ። " ገንዘብ እንደማያድን አየሁት " ይላሉ እናቷ ለኢዮሀ ሚዲያ እያለቀሱ ። ሀብት አያድንም ፤ ጉልበት አያድንም ፤ ስልጣን አያድንም ፤ ማንም አያድንም ። አምላክ ብቻ ያድናል ። በሳምራዊት መዳን ላይ የአምላክ ፈቃድ አልሆነም ። ቁምነገሩ እሱ አይደለም ። ለልጇ ፣ ለእናቷ ፣ ለባለቤቷና ለቅርብ ሰዎቿ ልብ መሰበር ካልሆነ ሳምራዊት በሞቷ እረፍት እንጂ ያጣችው የለም ።
ሀብት አያድንም ፤ ጉልበት አያድንም ፤ ስልጣን አያድንም ፤ ማንም አያድንም ። እኛ ከዚህ የምንወስደው ምንድነው ። በዚህ ዓለም ላይ የምንኖረው ለራሳችን ይሁን ለሌላ ግልጽ አይደለም ። መኖራችን ጥቅሙ ፣ መሞታችን ጉድለቱ የሚታየው በሌላው ለይ ነው ። ያ የመዳን ጉጉት አልሆነም ። እያንዳንዳችን እንደ ሳምራዊት ያለ ቀን ከፊታችን አለ ። ካንሰር ላይሆን ይችላል ። በተኛንበትም ፣ በእንቅልፋችን ውስጥ ሆነንም ሊሆን ይችላል ። የመሄጃችን ቀን ግን አለ ። ለእናቷም ፣ ለባለቤቷም ፣ ለልጇም ጭምር አለ ። የጊዜ ጉዳይ ነው ። ማንም ከዚያ አያስቀረንም ። ፀሎትም ፣ ጻድቅነትም እንኳ አያስቀረንም ።
ስራችን ይቀር ካልሆነ እኛ አንቀርም ። ከሌሎች ተምረን ራሳችንን የምንገልጽበት ሀሳባችንና ተግባራችን ብቻ በዚህ ዓለም ላይ ቋሚ ሆኖ ይቀራል ። ልጆቻችን ስማችንን የሚያስጠሩበት እድል እንኳን ጠባብና ጥቂት ነው ። እኛን ሰው የሚያደርገን በሰው ልጅ ልብ ውስጥ የተተከልንበት መጠን ነው ። የሚያስጠራን ያለን ሳይሆን ለዓለምና የሰው ልጆች የሰጠነው ነው ። " በምን ያህል መጠን ሰጥተናል ? " የሚለው ነው " በምን ያህል እንታሰባለን ? " የሚለውን የሚወስነው ። ሀብት አያድንም ፤ ጉልበት አያድንም ፤ ስልጣን አያድንም ፤ ማንም አያድንም ።
ውበት በወራትና ጥቂት አመታት ውስጥ እንዲህ ይረግፋል ። ይህቺ ውብ አበባ ምናልባትም በህልፈቷ ወቅት ከዚህ በላይም ከሰውነት ተራ ወጥታ ይሆናል ። በቃ ሰውነት ማለት እንዲህ ነው ። እኛ ማለት እንዲህ ነን ። ዋጋችን እንዲህ ነው ። መልካችን የሚመስለው ይህንን ነው ። ሳምራዊት ስታገባ ይህ ሁሉ መከራ ከፊቷ መምጣቱን አታውቅም ። አግብታ ስትወልድም ከምትወደውና ነሚወዳት ባለቤቷ ጋር ቤታቸው መሞቁንና መዋቡን እንጂ ከውልደቷ ማግስት ጀምሮ ስቃይና መከራን አልጠበቀችም ። እናቷም ፣ ባለቤቷም ሲናገሩ ትልቅ ስቃይ የሆነባቸው በቁም እያለች እሷንና ልጇን መነጠል ነበር ። በመጨረሻ ላይ የምትወደውንና የምትሳሳለትን ልጇን እንኳን ማቀፍ አልቻለችም ። አቅሟ ደክሟል ፤ ጉልበቷ ዝሏል ። በመጨረሻም ላይ ሄደች ። የዚህች ቆንጆ ሰውነት ከአፈር እንደመጣ ወደ አፈር ተመለሰ ። ማናችንም ከዚህ ቀን አናመልጥም ። ሀብት አያድነንም ፤ ውበት አያድነንም ፤ጉልበት አያድነንም ፤ ስልጣን አያድነንም ፤ ማንም አያድነንም ።
3.8K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited 11:48