Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.43K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-11 20:43:51 አቋም ይኑርህ!

በአንድም በሌላም ከሰዎች ጋር እንገናኛለን፤ ከእራሳችን በላይ ለእነርሱ ስሜት እንጨነቃለን፤ የተናገርናቸው ሁሉ የሚያሳዝናቸውና የሚያበሳጫቸው፣ የምናደርገው ሁሉ ግንኙነታችንን የሚያሻክር ይመስለናል። ነገር ግን ቀዳሚው ጉዳይ የንግግሩ አስከፊነት ሳይሆን ትክክለኛነት ነው፤ የድርጊቱ አሳዛኝነት ሳይሆን ልክነቱ ነው። እራስህን በመሆንህ፣ እቋም ስላለህ፣ የእራስህ  የግል አመለካከት ስለገነባህ፣ ያዋጣኛል ባልከው ትክክለኛ መንገድ ስለተጓዝክ፣ የእራስህ ደጋፊ፣ የእራስህ አበርታች በመሆንህ የሚቃወምህ፣ የሚተችህ፣ የሚናደድብህ ሰው ካለ ለእርሱ ስሜት ከመጨነቅ በላይ አንድ ማድረግ የምትችለው የተሻለ ነገር እንደፈለገው እንዲያስብህ፣ ድንበርህን ሳያልፍ እንዲገፋህና የፈለገውን እንዲያወራ መተው ነው። ማንም የእራሱ አቋም አለው፤ ምናልባትም አቋሙ ትክክል ላይሆን ይችላል፣ ጠቃሚም ላይሆን ይችላል ነገር ግን መገለጫው እስከሆነ ድረስ ተቀብለህ ከእርሱ ዞር ማለት ትችላለለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! አቋም ይኑርህ፤ እራስህን ሁን። ለመወደድ ብለህ እንደ እስስት አትቀያየር። አንድ ታዋቂ ማንነትን መገንባት ባለመቻል የሚመጣ ነገር ቢኖር በሁሉም ዘንድ ዝቅ ተደርጎ መታየት ነው። የአቋም ሰው እራሱን የሚያከብር እራሱን የሚያስከብር ሰው ነው፤ በማንነቱ የሚታወቅ ሰው ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ወጥና የተስተካከለ ነው። ስህተቱን የሚያምንና የሚቀበል ሰው ለይቅርታ ጊዜ አያጠፋም፤ ለመታረም ደጋግሞ ማሰብ አይጠበቅበትም። ያንተ ማስረዳት ችግር ካለበት፣ ቃላቶችህ የሚጎዱና የሚያሳምሙ ከሆኑ፣ ባልተገባ መንገድ ሃሳብህን ከገለፅክ ስህተቱ ያንተ ነውና እራስህን ከመውቀስ በላይ እራስህን አሻሽል፣ ስህተትህን አርም። ነገር ግን ባንተ ሳይሆን በሰዎች የመረዳት አቅም፣ የማስተዋል ችሎታ፣ የአስተሳሰብ ክፍተት ምክንያት የሚፈጠር ክፍተት ካለ ያንተ ድርሻ እራስን መውቀስ ሳይሆን በተሻለ ግልፅነት አቋምህን ማሳወቅ ነው።

አዎ! የምንለውን የሚሰሙ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የሚፈልጉትን በፈለጉት መንገድ የሚሰሙ ሰዎችም መኖራቸውን ማስተዋል ተገቢ ነው። አንዳች የሚያስቀይም፣ የሚያሳዝን ነገር ሳትናገር ወይም ሳታደርግ በእነርሱ የአረዳድ ችግር ብቻ ሲቀየሙህና ሲናደዱብህ ልትመለከት ትችላለህ። ለሆንከው ማንነት ዘብ ለመቆም፣ ለእራስህ ለመወገን አትፍራ፤ ተገቢውን የግል አቋምህን ከማንፀባረቅ ወደኋላ አትበል፤ ክብርህ በእጅህ እንደሆነ እወቅ። ባለቤቱ ያከበረውን ማንም ሊንቀውና ሊያወርደው አይችልም። ጠቢብ ጥበቡን እስካልተጠቀመ ጠቢብ አይባልምና አንተም የአቋም ሰው ካልሆንክ አቋመቢስ መባልህ አይቀርምና አቋም ይኑርህ፤ የሚገልፅህና የሚያሳውቅህን ማንነት ገንባ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 15:39:38
ልክ እንደብርጭቆ ሁን ከሰበሩህ ቁረጥቸው
3.9K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 12:37:22
ደም ለማን ይስጡ ፤ ከማንስ ይቀበሉ?

የደም አይነት: A+
※ለ A+, AB+ ይሰጣል።
※ከ A+, A-, O+, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: O+
※ለ O+, A+, B+, AB+ ይሰጣል።
※ከ O+, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: B+
※ለ B+, AB+ ይሰጣል።
※ ከ B+, B-, O+, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: AB+
※ ለ AB+ ብቻ ይሰጣል።
※ ከሁሉም ይቀበላል።

የደም አይነት: A-
※ ለ A+, A-, AB+, AB- ይሰጣል።
※ከ A-, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: O-
※ ለሁሉም ይሰጣል።
※ከ O- ይቀበላል።

የደም አይነት: B-
※ለ B+, B-, AB+, AB- ይሰጣል።
※ከ B-, O- ይቀበላል።

የደም አይነት: AB-
※ ለ AB+, AB- ይሰጣል።
※ ከ AB-, A-, B-, O- ይቀበላል።

አንብባችሁ ሼርርርር
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሸል ሚዲያ ያገኛነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:50:11 የወደድከውን ለምትወደው!

መውደድ ስስት የለውም፤ ፍቅር ዛሬ ነገን አያውቅም። ለምትወዳት፣ ለምትወደው መውደድህን፣ ለምታፈቅራት ፍቅርህን፣ ለምታከብረው አክብሮትህን፣ ለምታደንቀው አድናቆትህን ለመግለፅ ቀጠሮ አታብዛ፤ ጊዜ አትጠብቅ። በአጭሯ ህይወት ውስጥ የደስታችን ምክንያት የሆኑ ውድ ክስተቶችን ማዘግየት አያስፈልግም። ለሃዘናችን ውጫዊው አካል ምክንያት ቢደረድር፣ ለውስጣዊው ደስታና ሰላማችን ግን እራሳችን ዘብ መቆም ይኖርብናል። ህይወትን በጥልቀት ሰትረዳት ምንም ነገር ብታገኝ፣ የትም ብትደረስ፣ ምንም ብታሳካ አንድ ጥልቅ ስሜትህን የምታጋራው ሰው እንደሚያስፈልግህ ትረዳለህ። ከፍ ብትል ከፍታህን ከቤተሰብህ ጋር ታከብራለህ፤ የስኬትን ማማ ብትቆናጠጥ ከልብ ጓደኞችህ ጋር ታጣጥመዋለህ፤ የህይወትን ፈተና ድል ብትነሳ የእኔ ከምትለው ሰው ጋር ሃሴት ታደርጋለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! የወደድከውን ለምትወደው ለማጋራት ጊዜ አታጥፋ፤ የተመቸህን ለሚመችህ ለማካፈል አትሰስት፣ ወደኋላ አትበል። ከሰው ልጅ በላይ የምትወደው ነገር አለመኖሩንም እርግጠኛ ሁን። የሰውየው ማንነት ለውጥ ባያመጣም ደስታህ ደስታው፣ ስኬትህ ስኬቱ፣ ከፍታህ ከፍታው እንዲሆን የምትመኝለት የልብ ወዳጅ ያስፈልግሃል። እናት፣ አባት፣ ወንድም፣ እህት፣ ባል፣ ሚስት፣ የፍቅር ጓደኛ፣ ጓደኛ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን የደስታንም ሆነ የሃዘንን ስሜት ለመጋራት የሰው ልጅ ሰው ይፈልጋል፣ ሰውም ያስፈልገዋል። ይህም ሰው የሚወደው፣ የሚያከብረውና ጥሩ ስሜት እንዲሰማው የሚያደርገው ሰው ቢሆን ይመረጣል። ሮጠህ ብታሸንፍ ደስታህን የምታከብረው ከሰው ጋር ነው፤ ተዓምር ብትሰራ ተዓምሩን የሚካፈልህ የሆነ ሰው ነው።

አዎ! ከልብህ ደስ ሲለህ ቀድሞ በአዕምሮህ የሚመጣው፣ ከሃሳብህ የሚገባው፣ ደስታህን ልታጋራው የምትፈልገው ሰው ማነው? ሲከፋህ፣ ሆድ ሲብስህ፣ ስታዝን ስሜትህን እንዲጋራህ የምትፈልገው ሰው ማነው? በሁለቱም ወሳኝ የህይወት ክስተቶች ሰዓት የሚታወሱህ ሰዎች በልብህ ያኖርካቸው፣ በህይወትህ ትልቅ ስፍራን የሰጠሃቸው እጅግ የተወደዱና የተከበሩ ሰዎች ናቸውና ለማክበር፣ ለማመስገንና ፍቅርህን ለመግለፅ ጊዜ መድብላቸው። አብሮህ ሆኖ ምንም ያላደረክለት፣ አብሮህ ከባባድ ጊዜያትን ያሳለፈ፣ በመጥፎም በጥሩም ከጎንህ የነበረ፣ መቼም እንደማትለያዩ የምታስበው፣ ነገር ግን ነገ ምን እንደሚመጣ የማታውቀው ሰው ሊኖር ይችላል። ለእርሱም ቢሆን ስለምታጣውና ስለምትለየው ሳይሆን ስለአብሮነቱ፣ ስለድጋፉና ስላሳለፋችሁት ጥሩ ጊዜ ሁሉ አመስግነው፤ እንዳለህለት፣ ከጎኑም እንደሆንክ በኩራት ንገረው። አምላክ በሚፈቅደው መንገድ ፍቅርን በማጋራት የተረጋጋና እጅግ ሰላም የሰፈነበት ህይወትንም በሙላት አጣጥም።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.2K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:47:01 አምላክህ ያስፈልግሃል!

ማንንም ከምትፈልገው በላይ ማንም ከሚያስፈልግህ በተሻለ አምላክህ ያስፈልግሃል፤ ፈጣሪህ ያስፈልግሃል፤ አምላክህ ያሻሃል። በእርሱ ትነሳለህና ሰለመውደቅህ አታስብ፤ በእርሱ ትጠገናለህና ስለመጎዳትህ አትጨነቅ፤
በእርሱ ትድናለህና ህመምህ አያሳስብህ። አምላክን የያዘ ማን አፍሮ ያውቃል? ጌታውን የተጠጋ፣ በፈጣሪው የታመነ ምን ይደርስበታል? ምንስ ይድልበታል? ምንም እንዲደረግልህ ብትፈልግ እንዲረዳህ ሳይሆን እንዲያከናውንልህ፣ በመንገድህ እንዲቀድምልህ፣ አቅጣጫውን እንዲጠቁምህ፣ ካንተ እውቀት በላይ የማያልቀውን የእርሱን ጥበብ እንዲያድልህ ተማፀነው። ከአምላክ ጋር ስትሆን የውስጥ ሰላምህ እጅግ የተለየ ነው፤ በፈጣሪ ስትታመን ምድራዊ ፈተና አያሳስብህም፤ አያስደነግጥህም። የምታደርገው ተግባር፣ የምትጀምረው ነገር "በእርግጥ የአምላክ ፍቃድ አለበት? እርሱ ይወደዋልን?" ብለህ እራስህን ጠይቅ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከምታስበው በላይ አምላክህ ያስፈልግሃል፤ ፈጣሪህ አብሮህ ሊሆን ይገባል፤ በመንገድህ፣ በስራህ፣ በህይወትህ ሁሉ እርሱ መቅደም ይኖርበታል። ስለምታምነው ሁሉን እንዲያበጃጅ ትሰጠዋለህ፤ ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ወደ እርሱ ታሸጋግራለህ፤ መፍራት፣ መጨነቅ ታቆማለህ፤ ከህመም፣ ከስቃይ ነፃ ትወጣለህ። እምነት ደጋግሞ ስለፈጣሪ በማውራት ብቻ የሚገለፅ አይደለም፤ በቃል ብቻ "እርሱ አለ" በማለት የሚወከልም አይደለም። ከማንም ከምንም በላይ እንደሚያስፈልግህ ካመንክ በዛው ልክ በተግባር ልትታመንለት ይገባል፤ ለእርሱ መተው ያለብህን ነገር የመተው ብርታት፣ አሳልፈህ መስጠት የሚገባህን አሳልፈህ የመስጠት ድፍረት ያስፈልግሃል።

አዎ! "እግዚያብሔር ያውቃል፤ አምላኬ መልስ ይሰጠኛል፤ በጊዜው ሁሉን ውብ አድርጎ ይሰራዋል" ማለት በቃል ብቻ የሚተው አይደለም። እያለቀስክ፣ እየተበሳጨህ፣ በጉዳዩ እየታመምክ፣ አብዝተህ ስለእርሱ እየተጨነክ ለአምላክህ መታመን አትችልም። በአምላክህ ማዳን፣ በፈጣሪህ ድንቅ አደራጊነት የምታምን ከሆነ ሁሉን ለእርሱ መተው ይኖርብሃል። " የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉ፤ ሸክማችሁ የከበዳችሁ ወደ እኔ ኑ እኔ አሳርፋችኋለሁ። " የተባለውም በምክንያት እንደሆነ አስተውል። ጭንቀት ካለብህ ቢያውቀውም ምንያክል ከእርሱ ነፃ መሆን እንምትፈልግ ለማስገንዘብ ለአምላክህ ንገረው፤ ሸክምህ ከብዶህ መራመድን ቢከለክልህ ወደ ፈጣሪህ ተጠጋ እርሱም ሸክምህን ያቅልልህ፤ የማያልቀው ሰላሙንም ከፍፁም በረከቱ ጋር ያጎናፅፍህ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:46:34 ከፈለከው ተዋህደው!

ሃይሌ ገ/ስላሴ ስለፈለገ ብቻ የአለም ብርቅዬው አትሌት የሆነ ይመስልሃል? ክርስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲ ስለፈለጉ ብቻ የአለም ቁንጮ እግርኳስ ተጫዋቾች የሆኑ ይመስልሃል? ጄይ ሼቲ ስለፈለገና ስለመረጠ ብቻ የአለማችን ቁጥር አንድ አላማን ማግኘት ላይ የሚሰራ ፖድካስተር (On Purpose Podcaster) የሆነ ይመስልሃል? በፍፁም! ፍላጎትህ ሊያስጀምርህ ይችላል ነገር ግን አያስጨርስህም፤ ምርጫህ መንገዱን ሊጠቁምህ ይችላል ነገር ግን ከመዳረሻው አያደርስህም፤ ፍላጎት ሊያነቃቃህ ይችላል ነገር ግን በሒደቱ አያቆይህም፤ ፍላጎትህ ጊዜያዊ ብርታት ሊሆንህ ይችላል ነገር ግን ዲሲፖሊንድ (disciplined)  አያደርግህም። ከፍላጎት የሚልቅ፣ ከምኞት የሚገዝፍ፣ ከመጎምዠት የዘለለ ከሙያው ጋር በጥልቀት መዋሃድ፣ Obsessed መሆን የሚባል ነገር አለ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከፈለከው ተዋህደው! ከመረጥከው ከማንነትህ ጋር አገናኘው፤ ከተመኘሀው በሒደት እንዲሰራህና እንዲያበቃህ አድርግ። ከምትፈልገው ሙያ ጋር ብትዋሃድ የሚነዳህ፣ የሚያሰራህ፣ የሚሰራህ እርሱ ነውና የምትደክምበት ምክንያት አይኖርህም። ተግሉ ይጣፍጥሃል፤ ውጣውረዱ ያበረታሃል፤ ምቾት ማጣቱ ምቾት ይሰጥሃል፤ ድካሙ ብርታት ይሆንሃል። የተዋሃድከውን ነገር ላቁም ብትል እንኳን ማቆም አትችልም። ህይወት ያለእርሱ ትርጉም አይሰጥህም፤ ጠዓም አይኖረውም። ምቾት የሚሰማህ እየከበደህም ስታደርገው፤ እያስጠላህም ስቃዩን ስታየው ነው። በተዋሃደህ ነገር ውስጥ ምቾት ማጣት የሚባል ነገር የለም። ህይወትህ እርሱ ነው፤ አንተም የምትኖረው ለእርሱ ነው። አምላክ የፈጠረህ በዚህ ጉዳይ ቤተሰብህን፣ ወገንህን፣ ሃገርህንና አለምን እንድታገለግል ነው።

አዎ! በአንድ የሙያ ዘርፍ ቁንጮ ለመሆን ፍላጎት ብቻ በቂ እንዳልሆነ ተረዳ፤ ስለመረጥከው ብቻ ውጤታማ እንደማትሆን ተገንዘብ። ውህደት እጅግ አስፈላጊና ወሳኙ ነገር ነው። የምትሰራው ስራ ለምን ጥራት ያጣ ይመስልሃል? ለምን በየጊዜው እየተጀመረ የሚቆም ይመስልሃል? ለምን የማያረካህ ይመስልሃል? ምክንያቱም ስላልተዋሃደህ ነው፤ ምክንያቱም ስሜት ስለማይሰጥህ ነው፤ ምክንያቱም እንደ ግዴታና እንደ ሸክም ስለምትመለከተው ነው። በምትወደው ዘርፍ ስኬታማ መሆን ከፈለክ መታገሉን አቁመህ ከሒደቱ ጋር ተዋሃድ፣ ማንነትህን ለሙያው አስገዛ፣ የደስታህ ምንጭ፣ የሃሴትህ ምክንያት አድርገው። መዋሃድ ስትጀምር የህይወት አላማህም በዛው ልክ ይገለጥልሃል፤ በተራውም አንተን መቅረፅ ይጀምራል።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:45:58 ዛሬን እንደ እርምጃ ቀን!

ዛሬ የተግባር ቀን ብትሆንስ? ዛሬ ሃሳባችንን ወደ ተግባር የምንቀይርባት፣ ይብዛም ይነስም አንድ ወይም ሁለት እርምጃ ወደፊት የምንጓዝባት፣ የረጅም ጊዜ ሃሳባችንን ወደ ምድር የምናወርድባት፣ ውጤት ሳንጠብቅ የወደድነውን ነገር በነፃነት የምናደርግባት የተለየች ታሪካዊ ቀን ብትሆንስ? በተደጋጋሚ ማሰብህ ለውጥ እንዳላመጣ አይተሃል፤ ሁሌም አቅደህ መተውህ ትርጉም እንዳልሰጠህ ተገንዝበሃል። እናም እርምጃ መውሰድ፣ ወደ ተግባር መግባት፣ ስራን መስራት፣ በትንሹም ቢሆን መንቀሳቀስ ይኖርብሃል። ብዙ ነገር ላይጠበቅብህ ይችላል፣ ሃሳቤን ሊደግፍ ይችላል፤ ሊረዳኝ፣ ሊያግዘኝ ይችላል፣ "አብሮ ለመስራት የተሻለው ሰው እርሱ ነው" ለምትለው ሰው ሃሳቡን ማጋራት ትችላለህ፣ እንደ ጀማሪ የሚያስፈልጉህን ግበዓቶች ዋጋ ማጠያየቅ ትችላለህ፤ በዘርፉ ላይ ግንዛቤህን ለመጨመር በተለየ ሁኔታ መማር ትችላለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬን እንደ እርምጃ ቀን፣ ዛሬን እንደ ውጤታማና ትርፋማ ቀን ተጠቀም። ለአመታት የጠበከውን ተነሳሽነት፣ ብርታትና ንቃት የምትጠብቅበት ሳይሆን፣ ለረጅም ጊዜ የጎደሉህን ነገሮች ስትቆጥርባቸው እንደነበሩት ቀናት ሳይሆን፣ ጀምረህ እንደምትተውበት ወቅት ሳይሆን ቢሆንም ባይሆንም፣ ቢሳካም ባይሳካም ከሃሳብ የዘለል፣ እቅድን የተሻገረ፣ እራሱ ብርታትን የሚሰጥ፣ ስለጀመርከው የሚያጠነክርህን ተግባር በትንሹ የምትጀምርበት ቀን አድርገው። እውቀት አንሶህ፣ ከብዶህ፣ ድጋፍ እጥተህ፣ ገንዘብ አጥሮህ እንዳላቆምክ ታውቃለህ። ዋናው ችግርህ ምቾትህ ነው፤ ድፍረት ማጣትህ ነው፤ ሪስክ ለመውሰድ ዝግጁ አለመሆንህ ነው፤ ለእራስህ ደጋግመህ የምትነግረው አሉታዊ ሃሳብ ነው፤ ከበቁና ከነቁ፣ ካደጉና ከበለፀጉ፣ ለአመታት ከለፉና ከደከሙ፣ በዘርፉ አንቱታን ካተረፉ ሰዎች ጋር እራስህን ማነፃፀርህ ነው።

አዎ! ቢያንስ ዘወትር እየደጋገመ የሚመጣብህ ሃሳብ  ይኖርሃል፤ አንድ ነገር ባየህ ወይም በሰማህ ቁጥር የሚታወስህ ህልም ይኖራል፤ ሌላው ቢቀር ስለጉዳዩ የምታውቀው ነገር አለ። የሰነከው ራዕይህ ህይወትህን እንደሚቀይር ታውቃለህ፣ ነገር ግን ሂደቱን አላማንክበትም፤ የህልምህን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ተረድተሃል፣ ነገር ግን በትንሹ የመጀመሩ ሃሳብ አልተዋጠልህም። አሁን በሰበብ አስባቡ ምክንያት እየደረደርክ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ የምታባክንበት ወቅት አይደለምና ዛሬን እንደመነሻህ ተጠቅመህ ተነስ፤ የተግባር ሰው ወደመሆን ተሸጋገርባት፤ በአንድ እርምጃ ወደ ህልምህ እውንነት የምትንቀሳቀስበት ውጤታማና ትርጉም ሰጪ ቀን አድርጋት። ቢያንስ ከራዕይህ ጋር የሚገናኝ አንድ ነገር አድርገህ አሳልፋት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:45:32 ማን አቆመህ?

መሔድ እስከምትችለው እንዳትሔድ፣ መድረስ ያለብህ ስፍራ እንዳትደርስ፣ ማግኘት ያለብህን እንዳታገኝ፣ ማትረፍ ያለብህን እንዳታተረፍ፣ የሚገባህን እንዳይኖርህ ማን አገደህ? ማንስ አቆመህ? ጀምሮ በመተው ልማድ ታስረህ፣ ሞክሮ በማቆም አዙሪት ውስጥ ገብተህ፣ ሁሉን የመነካካት እንጂ የመጨረስን መልካም ተግባር ወደኋላ ብለህ ከመንገድህ ለመሰናከልህ ሰዎችን፣ ሁኔታዎችን፣ አሰራርን፣ መንግስትን ብትወቅስ ምንም ዋጋ የለውም። ምክንያት የማትደረድር ከሆነ እውነታውን ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ። ስለራስህ ጀብደኝነት ለማውራት እንደምትጣደፈው ድክመትህንም ለእራስህ ከማስረዳት ወደኋላ አትበል። የምታውቀው ማንነትህ ወዳጅህ እንጂ ባዳህ አይደለም፤ የሚረዳህ እንጂ የሚገፋህ አይደለም፤ የሚያውቅህ እንጂ ያልተገለጥክለት አይደለህም።

አዎ! ጀግናዬ..! ማን አቆመህ? ማን እንደነበርክ፣ በነበርክበት አስቀረህ? ማን ለውጥን እንደማትፈልግ፣ እንድገትን እንደምትጠየፍ፣ ከፍታን እንደምትጠላ ሊያሳምንህ ሞከረ? በአለም ዙሪያ የሚናፈሰው ተስፋቢስ ዜና ነውን? ሀገርን የወረረው አሉታዊ ትርክት ነውን? በየጊዜው የሚቀያየረው ጊዜያው ጉዳይ ነውን? አወኩት ባልከው ማግስት የሚለወጥብህ ሰው ነውን? ካንተ የማያልፈው ጊዜያዊ ምቾትህ ነውን? ባለህበት ለመቆምህ፣ በአንድ ቦታ፣ በተመሳሳይ አዙሪት ለመዋጥህ ብዙ ምክንያቶች ልትጠቅስ ትችላለህ። ነገር ግን አሁንም እዛው ባለህበት ቆመህ መቅረትን ካልፈለክ ዋንኛው ምክንያትህ አንተ እራስህ እንደሆንክ ማመን ይኖርብሃል። ለሰው ሲሆን ብዙ ምክንያት ልትደረድር ትችላለህ ለእራስህ ግን የምታውቀውን አንተው ታውቀዋለህ።

አዎ! አንዳንዴ በሆድ የሚያዙ፣ ከእራስ የማይወጡ፣ ለእራስ ብቻ እንደ ሚስጥር የሚያዙ እውነታዎች ይኖራሉ። አውጥተህ ብትናገራቸው መጠቋቆሚያ ያደርጉሃል፤ የሚሰጥህን ግምት ያሳንሱታል፤ ለትቺትና ዘለፋ ያጋልጡሃል። ስለዚህ ስለእራስህ የምታውቀው እውነታ ቢኖርም የሆድህን በሆድህ ይዘህ ሰዎች የሚታያቸውን ምክንያት ትደረድርላቸዋለህ። የምታውቀውን እውነት ተቀበል፤ ስለእራስህ የሚሰማህን ስሜት አዳምጥ፤ ባለህበት ለመክረምህ፣ በቀድሞው ስፍራ ለመሰንበትህ ከእራስህ በላይ ተጠያቂ እንደሌለ እመን። የውጪውን እንቅስቃሴ ተውና እራስህ ላይ መስራት ጀምር፤ አንድ እርምጃም ቢሆን ፈቀቅ በል፤ ለአዲስ ከባቢ፣ ለተለየ ምህዳር እራስህን አዘጋጅ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:45:10 ከባጣ-ቆየኝ ተጠበቅ!

ባጣ-ቆየኝ የተባሉ ሰዎች ሲኖርህ ወዳጆችህ ናቸው፤ ስታጣ፣ አንዳች ነገር ሲጎድልህ ደግሞ ምንም የሌለህ፣ ምንም የማትጠቅማቸው ከንቱ ሰው ነህ። እያንዳንዱ ተግባርህ እነርሱን ከመጥቀም ጋር መገናኘት አለበት። ምንም ካላገኙብህ፣ ምንም ካልጠቀምካቸው አንተ ለእነርሱ ምንም ነህ። በተዓምር ትዝም አትላቸውም። ሩጫቸው የእራሳቸውን ሆድ ለመሙላትና ጠግቦ ለማደር እንጂ ያንተ መራብና በችግር መሰቃየት ምናቸውም አይደለም። የእነርሱ ሙቀት ማግኘት እንጂ ያንተ በብርድ መጠበስ ጉዳያቸው አይደለም። ስታገኝ እንድታካፍላቸው ሲያገኙ ደግሞ እንድትርቃቸው ይፈልጋሉ። ከሌላው ሰው በጣም የተለዩ እንደሆኑ ስለሚያስቡ ካንተ እኩል እራሳቸውን መመልከትን እንደ ውርደት ይመለከቱታል። ተጠቃሚ እስከሆኑ ድረስ አብረውህ ናቸው ካልጠቀምካቸው ግን በነጋታው ጥለውህ ለመሔድ በፍፁም አያንገራግሩም። የቀድሞ ውለታህ፣ ያደረክላቸው መልካም ነገር፣ በጎነትህ ዛሬ እስካልሆነ ድረስ ከመሔድ ልታስቆማቸው አትችልም።

አዎ! ጀግናዬ..! ከባጣ-ቆየኝ ተጠበቅ! እንደ አማራጭ ከሚመለከቱህ፣ እንደማያዛልቁህ ከተረዳሃቸው፣ የዘወትር ፍላጎታቸው እራሳቸውን ብቻ መጥቀም ከሆነ፣ ከእራስ ወዳድነት ባህሪ የገዘፈ የእራስ አምላኪነት አባዜ ካላቸው፣ ሁሌ ስህተት እንደማይሰሩ፣ ጥፋታቸው ሁሉ ቅዱስ እንደሚያደርጋቸው ከሚያስቡ፣ ህይወታቸውን በሙሉ ስለእራሳቸው ምቾትና መደላደል ብቻ ሲጨነቁ ከሚኖሩ ሰዎች እራስህን ጠብቅ። እነርሱ ጋር የሰውነትህ ልኬት በምታደርግላቸው ተግባር እንጂ በማንነትህ አይደለም። አብረሃቸው ብትሖን መሔጃ እንዳጣህና ያለህ አማራጭ ከእነርሱ መጠጋት ብቻ እንደሆነ ስለሚያስቡ እንደፈለጉ ሊያደርጉህና ሊጫወቱብህ ይሞክራሉ። ከእራስ አምላኪዎች ጋር ስትሆን አንተ መጠቀሚያ እቃ እንጂ ሰው አትመስላቸውም፤ ነገ አውጥተው እንደማይጥሉህ እርግጠኛ መሆን አትችልም።

አዎ! ከእራሳቸውን አምላኪዎች (Narcissist) ሰዎች እራስህን ልትጠብቅ የምትችልበት አዋጭ መንገድ ሳትቀደም በመቅደም ብቻ ነው። እንደ ሸንኮራ አኝከው፣ ጠዓምህን ጨርሰው ከመትፋታቸው በፊት አንተ ቀድመህ ከህይወትህ ውስጥ ትፋቸው፤ ከህይወትህ ጠራርገህ አስወጣቸው። ከእነርሱ ለመለየት ከበቂ በላይ ምክንያት እንዳለህ አስታውስ። እነርሱ ባሉበት የበታችነት እየተሰማህ፣ እየተሳቀክ፣ ሁሌም ስህተት የምትሰራው አንተ እንደሆንክ እያሰብክ፣ ካንተ በላይ ባንተ የሚደረገው ጥቅም ዋጋ እንዳለው እየተመለከትክ፣ አብሮ ከመኖር ይልቅ በአኗኗሪነት መቆጠር የእነዚህን ሰዎች ቅርንጫፍ ከእራስህ ግንድ ላይ ቆርጦ ለመጣል እጅግ በጣም በቂ ምክንያቶች ናቸው። የሰውነት ዋጋህን ከፍ ለማድረግ እራስ አምላኪ (Narcissist) መሆን ሳይሆን እራስ አምላኪዎችን፣ ባጣ-ቆየኞችን ከህይወትህ ማስወጣት በቂ እንደሆነ አስተውል።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:44:45 እርግጠኝነት ይቅደም!

ሳይገባህ ለውሳኔ አትቸኩል፤ ሳትረዳ ለፍርድ አትፋጠን፤ ጉዳዩን ሳታጣራ እርምጃ አትውሰድ። ህይወት የውሳኔዎችህ ነፀብራቅ ከመሆኗ አንፃር በተቻለህ መጠን ከየትኛውም ውሳኔና እርምጃህ በፊት እግጠኝነትን አስቀድም። ይብዛም ይነስም በትንሹ እርግጠኛ የሆንክበት ነገር ዝግጁነትህን ይጨምራል፤ አቅጣጫህን ያስተካክላል፤ መንገድ ይጠቁምሃል። የፍቅር ህይወትህን በመለያየት ለመቋጨት ከመጣደፍህ በፊት ማወቅ የሚገባህን መርምረህ እወቀው፤ ብሎም ከመለያየት ቦሃላ ለሚመጣው የተለየ የህይወት ዘይቤ ዝግጁ መሆንህን እርግጠኛ ሁን። ስራህን ከማቆምህ በፊት ስለምትጀምረው አዲስ ስራ በቂ መረጃ ይኑርህ። ከቤትህ ሳትወጣ የት እንደምትሔድ ማወቅ እንዳለብህ ሁሉ አንድን ነገር ስታቆም በቀጣይ ምን እንደምትጀምር እወቅ።

አዎ! ጀግናዬ..! እርግጠኝነት ይቅደም! ቢሳካም ባይሳካም አየር ላይ መቅረት እንደሌለብህ ታውቃለህ፤ ያሰብከው ቢሆንም ባይሆንም መጨነቅና መጎዳት እንደሌለብህ እርግጥ ነው። ምንም ነገር ከማድረግህ በፊት በልበሙሉነት፣ በእርግጠኝነትና በእምነት ማድረግህ ከብዙ አደጋ ይታደግሃል። በእርምጃው እርግጠኛ የሆነ፣ የጉዞውን አቅጣጫ የሚያውቅ፣ እንቅስቃሴውን የተረዳ ሰው ሃላፊነት ከመውሰድ ወደኋላ አይልም። ወዴትም ልትሔድ ትችላለህ፣ ምንም ልታደርግ ትችላለህ፣ እንዴትም ልታደርገው ትችላለህ ነገር ግን አንድ ነገር ስታደርግ አንዱን መተውህ፣ አንዱን ስትጨብጥም አንዱን መልቀቅህ የማይቀር ነው። ለማያዋጣ ግንኙነት ተብሎ የተረጋጋውንና ሰላማዊውን ግንኙነት ማፍረስ ከማስተዋልና በጉዳዩ ላይ እርግጠኛ ካለመሆን የሚመጣ ነው።

አዎ! ቅድሚያ ማግኘት ያለበት ነገር ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። እርሱም የጠለቀ እውቀት ነው፤ እርሱም የመጪው ክስተት ግልፅነት ነው፤ እርሱም እርግጠኝነት ነው። የትኛውም ውሳኔህ በደመነፍስ ሳይሆን በሰከነ መንፈስ፣ በስሜታዊነት ሳይሆን በተረጋጋ አዕምሮና በማስተዋል የሚወሰን ነው። አደጋ እንዳለው ብታውቅም የአደጋውን ምንነት ልትረዳው ይገባል፤ ከውሳኔህ ቦሃላ የሚገጥምህን ክስተት መገመት ባይከብድህም በእርሱ ዙሪያ የምትሰጠውን ምላሽ ላይ በሰፊው መዘጋጀት ይኖርብሃል። ስለምታገኘው ነገር እርግጠኛ ሳትሆን ያለህን አትጣል፤ የሚመጣው ነገር እንደሚጠቅምህ እርግጠኛ ሳትሆን እጅህ ላይ ያለውን አሳልፈህ አትስጥ። ለመቅደም ሲጣደፉ መቀደምም እንዳለ አስታውስ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ