2023-05-14 07:08:42
ይሄው ነው!እውነት ነው፤ ያለምንም ጥርጥር ከቆይታ ቦሃላ የተሻልክ ሰው ትሆናለህ፤ መጀመር ስለምታስበው ነገር ብዙ ትማራለህ፤ ብዙ ታውቃለህ፤ በተሻለ ደረጃም ትገኛለህ። አንተ ባትፈልግም የህይወት ግፊት፣ የሰዎች ጫና፣ የሁኔታዎች ከባድ መሆን በትንሹም ቢሆን ይበልጥ እንድትሰራና ለተሻለ ስፍራ እንድትበቃ ያደርግሃል። ነገር ግን በዚህ መንገድ ከመደበኛው ለውጥ የተለየ ነገር አታደርግም። ምኞትህ ልባዊ ሆኖ ተግባር ባይኖረው እንደማንኛውም ሃሳብና ምኞት እንዳለው ሰው ከመደበኛው የህይወት መዓቀፍ አትወጣም። ልዩ ነው የምትለው መርህ በውስጥህ ቢመላለስና ለመተግበር ድፍረቱ ባይኖርህ ዛሬም በነበርክበት ትቀጥላለህ። ዞሮ ዞሮ እዛው መገኘት ምንም የተለየ ጠዓም አይኖረውም።
አዎ! ጀግናዬ..! ከተግባር በቀር አትለወጥም፤
ካላደረከው ምንም አታመጣም፤ ካልጀመርክ አንዳች ነገር አትመለከትም። የትም ብትሔድ ፍረሃት አለ፤ ምንም አዲስ ነገር ለማድረግ ብታስብ መስጋትህ አይቀርም። ምክንያቱም ከለመድከው የሃሳብ እርከን ትወጣለህና፤ ምክንያቱም አድርገህ የማታውቀውን ነገር ለማድረግ ተዘጋጅተሃልና። በህይወትህ ተጨባጭ ለውጥ ማየት ከፈለክ የለውጥ ሃሳብህን አድርጎ መገኘት ምርጫ የሌለው አማራጭ ነው። ያስቀመጥካቸው ቅደመሁኔታዎች እስኪሟሉ ጊዜ ቆሞ አይጠብቅህም። የአለምን የለውጥ ፍጥነት ተመልከት፤ አንተ ግን ዛሬም በይሉኝታ ታስረህ ትጨነቃለህ። ሃሳብህ ምንም ይሁን አዎንታዊ ከሆነና ካንተ ጀምሮ የሰዎችን ህይወት የተሻለ የሚያደርግ ከሆነ ማንም ምንም ቢል ጉዳይህ ሊሆን አይገባም። ሃሳብህ መስረቅ አይደለም፤ ሃሳብህ ወንጀል መስራት አይደለም፤ ምኞትህ ሰዎችን መጉዳት አይደለም። ስለዚህ መጀመሩን ለምን ፈራሀው? ለምንስ በሰዎች አሉታዊ ቃላት ተሸበብክ?
አዎ! እርሱ ሳይመጣ አንተ ሂድለት፤ ሳያስገድድህ በውዴታ ጀምረው። ኑሮ ከብዷል፤ ሰው ክፉ ሆኗል፤ ፈተና ተደራርቧል፤ ችግር ላይ የወደቀ ሰው በዝቷል። ከዚህ በላይ ሃሳብህን መሬታ ላይ እንድታወርድ የሚያደርግህ ሁኔታ ምን ሊሆን ይችላል? አንዳንዴ የነገሮች ዋጋቸው መናር አይቀሬ ቢሆንም የእኛ በነበርንበት ስፍራ መሰንበት ደግሞ ንረቱን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል። የዛሬ አምት አመት በሚከፈልህ ደሞዝ እንዴት የዛሬውን ኑሮህን በሚገባ ተቋቁመህ ማለፍን ታስባለህ? የነገሮች ዋጋ ሲጨምር ያንተም ዋጋ በትንሹም ቢሆን መጨመር ይኖርበታል። ጊዜው ትልቅ ሃሳብ ታቅፎ ለሚያባብል ሰው አይሆንም፤ ጊዜው ምኞትን እየተመገበ ለሚኖር ሰው አይሆንም። ሁሌም ቢሆን እራስን አዘጋጅቶ መጀመር፣ ወደ ተግባር መግባት መስራት፣ መስራት ብቻ። አትፍራ፤ ለሚያድገው ህልምህ ዛሬ መሰረቱን ጣል፣ በየጊዜው በሙሉ አቅምህ ስራበት፤ በዚህ ሁኔታ በፍፁም ያለማደግ ምርጫ ሊኖረው አይችልም።
ይሄው ነው፤ በርታ!
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited 04:08