Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት ሰዓት ይበቃሃል! ብዙ ሰዓት መስራት አይጠበቅብህም፤ ረጅሙን ጊዜህን እርሱ ላይ ማጥፋት አይ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ሁለት ሰዓት ይበቃሃል!

ብዙ ሰዓት መስራት አይጠበቅብህም፤ ረጅሙን ጊዜህን እርሱ ላይ ማጥፋት አይኖርብህም። በቀን ስምንት የስራ ሰዓት አለህ፣ ሌላው ስምንት ሰዓት የእንቅልፍ ነው፤ ቀሪው ስድስት ሰዓት ለምግብ፣ ለመጠጥና ለመዝናናት ሊውል ይችላል ሁለቱ ቀሪ ሰዓት ግን ህልምህን የምትኖርበት ነው፤ ራዕይህን አቅጣጫ የምታሲዝበት ነው፤ የህይወት ትርጉምህን የምታገኝበት ነው። ህይወት ከፈተናዋና ከችግሯ ብዛት ህልምን ለመኖር ጊዜ ላትሰጥህ ትችላለች፤ በፈለከው መንገድ እንድትኖራት ላትፈቅድልህ ትችላለች። የሆነ ሰዓት የገባህበት ስራ መፈናፈኛ ያሳጣሃል፤ ሳታስበው የጀመርከው ትምህርት እረፍት ይነሳሃል፤ በአጋጣሚ የተዋወከው ጓደኛህ አጉል ልማድ ውስጥ ይከትሃል። ህልምህ ግን ሳይታሰብ የሚደረግ፣ ያለእቅድ የምትከውነው፣ በአጋጣሚ የሚሆን ነገር አይደለም። ከዘፈቀደው አኳሃን በተለየ በሚያስበው የአዕምሮ ክፍል ተመዝኖ ቦታና ጊዜ የሚመደብለት ብርቱ ጉዳይ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁለት ሰዓት (2:00) ይበቃሃል፤ ህልሜ የምትለውን ነገር ለማሳካት፣ ህይወትህን አቅጣጫ ለማስያዝ፣ ደስተኛና የተረጋጋ ህይወት ለመኖር ገንዘብ አያስፈልግህም፤ የሰው እርዳታ አያስፈልግህም፤ የመንግስት ድጎማ አስፈልግህም። አንድ በዋናነት ሊያስፈልግህ የሚችለው ነገር ካለህ ሃያ አራት ሰዓት ውስጥ  ሁለቱን ሰዓት ብቻ ለህልምህ መስጠት ነው። ምናልባት ከህልምህ ጋር የሚገናኙ መፅሃፍትን ማንበብ ሊሆን ይችላል፤ ምናልባት በራዕይህ ዘርፍ ሰዎችን ማገልገል ይሆናል፤ ምናልባት ከህልምህ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ሁን ብሎ ማግኘትም ሊሆን ይችላል። ስለ ህልምህ ስታወራ እህ.. ብሎ የሚሰማህን ሰው ከገኘህ እራሱ እርሱ በጣም ትልቅ ነገር ነው። ከሰማህ ቦሃላ ማረጋገጫ ባይሰጥህ እንኳን ህልምህን በቃላት ሰድረህ መግለፅ መቻልህ በእራሱ ግልፅነቱን እንድትረዳው ያደርግሃል።

አዎ! ወጥነት ያላቸው፣ በየቀኑ የማይቋረጡ የሁለት ሰዓት ድርጊቶች አሁን ሙሉ ህይወትህን እንድትመራበት ካስቻለህ የስምንት ሰዓት ስራ ነፃ እንደሚያወጣህ አትጠራጠር። የምትኖረው ህይወት ነው። መኖር ውስጥም ጠዓም አለ። ጠዓሙም የሚጎላው በምትወደውና በምትፈልገው ነገር ውስጥ ነው። የምትወደው ነገር ደግሞ ሙሉ በሙሉ ህልምህ ውስጥ አለ፤ ራዕይህ ውስጥ አለ፤ አላማህ ውስጥ አለ። ህልምህን መኖር ለመጀመር አሁን ከምትማረው ትምህርት ጋር መጋጨት አያስፈልግህም፤ ስራህን ማቆም አይጠበቅብህም፤ ሰዎች እንዲያምኑብህ መጣር አይጠበቅብህም፤ እርዳታ ከየአቅጣጫው መጉረፍ አይኖርበትም። ህልሜ ለምትለው ነገር ተገቢውን ጊዜ ስጠው፤ በየቀኑ ሁለት ሰዓት ብቻ ስራበት፣ በእርሱ ዙሪያ ግንኙነትህን አስፋ፤ እንደ ትግል ሳይሆን እንደ አስደሳች ሁነት ተመልከተው፤ በውስጡ እራስህን አድስ። በስተመጨረሻም ከምታስበው በላይ ዋጋህን እንደሚከፍልህ እመን።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q