Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.43K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-17 18:25:46
ከፍቶኛል ስልህ እንደናፈከኝ
ሳኮርፍህ እያሰብኩህ እንደሆነ
ሳቅፍህ እንደምሳሳልህ
ስስምህ እንደማፈቅርህ
አይኖቼ ሲያዮህ አለሜ እንደሆንክ
ስታስቀኝ የደስታዬ ምንጭ እንደሆንክ
ስምህን ጠርቼ ስምል ያንተ ብቻ መሆኔን፡፡
እጅህን ስይዝህ እንደማምንህ እወቅ
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 10:14:49
ደሜ ውስጥ ፍቅርሽ አለ
አይምሮዬ ውስጥ ትዝታሽ አለ
እንቅልፌ ውስጥ ህልምሽ አለ
ህይወቴ ውስጥ ደሞ አንቺ አለሽ::

https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 10:01:41 ሸክምህን ቀንስ!

እለት እለት ከሚያደቡበህ፣ ውድቀትህን አጥብቀው ከሚሹ፣ ኪሳራህን ከሚጠባበቁ፣ በወጣህ በገባህ ቁጥር ጥፋትህን ከሚቆጥሩ፣ እንዲሁ በባዶ ቀልባቸው ከማይወድህ፣ ያለምክንያት ሊርቁህ ከሚፈልጉ ሰዎች ምን ህብረት አለህ? የምትፈልገውን እየሰጡህ ነውን? ወደምትፈልገው ስፍራ እየመሩህ ነውን? አንዳች ከእነርሱ ያተረፍከው፣ ለህልምህ እውንነት ያበረከቱት አስተዋፅዖ ምንድነው? የምትበርበትን ከፍታ ለመጨመር ግዴታ የያዝከውን ሸክም መጣል ይኖርብሃል፤ ከሸክሞችህ ዋንኞቹ ደግሞ በሃሳብ፣ በምኞት፣ በተግባር የሚጠሉህ ሰዎች ናቸው። የሚጠየፉህን፣ ወደኋላ የሚጎትቱህን፣ ክፉ የሚመኙልህን ሰዎች ተሸክመህ እስኬት መጓዝ የምትችል ይመስልሃል? ምንያክል ርቀት የምትሔድ ይመስልሃል? ከመጥፎ ልማዶችህ መለየት እንዳለብህ ሁሉ የሚጠሉህን ሰዎች የመለየት ግዴታ አለብህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሩቅ ለመሔድ ሸክምህን ቀንስ፤ የሚጠሉህን ችላ በል፤ ከህይወትህ ዞር አድርጋቸው፤ አስወግዳቸው። መልካም የማያስቡልህን አርቅ፤ በብርታት ቦታ እንቅፋት የሚሆኑህን ሰዎች ከዙሪያህ አስወግድ። ጠላትህን ውደድ፣ የሚረግምህንም መርቅ የሚለውን የአምላክ ቃል ለመፈፀም መልካም እያደረክላቸው፣ እያሰብክላቸው፣ በፍቅርህ እየማረካቸው መቆየት ትችላለህ ነገር ግን በእነርሱ አሰናካይ ሃሳብ፣ በእነርሱ የምቀኝነት ደባ፣ በእነርሱ ቅስም ሰባሪ ንግግር የመጎዳትና የመሰበር ግዴታ የለብህም። ብትወዳቸውም ከህይወትህ ታስወጣቸዋለህ፤ ብታስብላቸውም አስተያየታቸውን አትቀበልም፤ ብታከብራቸውም ንግግራቸውን አትሰማም። ክፋት አስበህ፣ ተናደህባቸው ወይም አዝነህባቸው አይደለም። እራስህን ለማዳን፣ ጠንካራ ጎንህን ለማጎልበት፣ በብርታት ወደፊት ለመጓዝ፣ ፍጥነትህን ለመጨመር፣ እራስህን ነፃ ለማውጣት ያለህ ብቸኛ አማራጭ እርሱ ስለሆነ ነው።

አዎ! እስከ መቼ ከህይወት ሸክምህ ቅንጣት ከማይቀንሱልህና ከማይካፈሉህ ሰዎች ጋር ትደክማለህ? እስከ መቼ ውድቀትህን አጥብቀው ከሚመኙ ሰዎች ጋር ትቀጥላለህ? እስከመቼ ከመንገድህ ከሚያስቀሩህ፣ ሃሳብህን ከሚቃረኑ፣ እቅድህን ከሚያምታቱ፣ ህልምህን ከሚያጨናግፉ ሰዎች ጋር ትጓዛለህ? የሚደግፉህ ከሆነ ይደግፉሃል፤ የሚያግዙህ ከሆነ ያግዙሃል፤ የሚረዱህ ከሆነ ይረዱሃል ካልሆነ ግን ውድ ጊዜህን እያባከኑብህ፣ አቅምህን እያሳነሱብህ፣ ተነሳሽነትህን እየቀበሩት፣ መነቃቃትህን ውሃ እየደፉበት ልትመርጣቸውና አብረሃቸው ልትሰራ አትችልም። እራስህን ለማዳን አትችልም ለሚሉህ መልስ መፈለግ አይጠበቅብህም፤ አሉታዊ ንግግርን የሚያቀርቡልህን መጥላት አይኖርብህም። እራስህ ላይ ማተኮር፣ ከእነርሱ ዞር ማለት፤ ፊትህን ማዞር፣ ቀስበቀስ ከህይወትህ ማስወጣት፤ በምትኩ የልብ ወዳጆችህንና ደጋፊዎችህን ማስገባት እጅግ በጣም በቂ ነው።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 02:38:56
Friend,Boyfriend,Girlfriend ልበ በሉ በ ነው የሚያበቁት ያ ማለት ደግሞ ያበቃሉ ማለት ነው ። FAMILY ግን በ"ILY" ነው ሚጨርሰው "ILY" ማለት ደግሞ I LOVE YOU ማለት ነው ። ፍቅር ደግሞ አያልቅም አያበቃም ። ምን ለማለት ፈልጌ ነው መጨረሻ የሌለውንና የማያበቃውን Family ምረጡም መስርቱም እላችኋለሁ ። ምርጫቹ ማስተዋል የተሞላበት ይሁን ።
3.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  23:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 02:17:30
መደሠትን ጠላሁ መከፋት ተጫነኝ
የያዝኩት ተነነ ያቀፍኩትም ገፋኝ
የልቤን እረመጥ በእንባዬ ሳጠፋ
ሀዘን ብሶቴን በትካዜ ስጋፋ
በመደሰቴ ላይ ሠው አብሮኝ ቢኖርም
የሆድ ውስጥ እሳት ግን ጎረቤት አይፈጅም
ለምን ሆነ አትበሉኝ አጠይቁኝ ይቅር
ሁሉን ብነግራችሁ ላይገባችሁ ነገር
እንዴት አትበሉኝ ለማወቅ ጓጉታችሁ
ነገሩን ላታውቁት ምንም ላይጠቅማችሁ
ብቻዬን ብኖርም ከሰው ተሸሽጌ
ሀዘን ሰቆቃዬን ብሶት ቻል አድርጌ
ድጋ እንደታቀፈ ባህር እንደለበሰ አልጌ
እንደተዳፈነ እሳት እንደለበሰ አመድ
ከአፍ ለወጣ ቃል ላይያዝ በገመድ
የየብስ ላይ አሳ የውቅያኖስ አይጥ
ጅብን በመጫኛ አንበሳውን በልጥ
ውዬ አድሬ ድብርት አልቻልኩኝም ማምለጥ
አታድሙት ቁስሌን በእሾህ ወጋግታችሁ
የማያባራ እንባ ጉድ እንዳይሠራችሁ
አላድክም እራሴን አንዱም ላይገባችሁ
በቃ አትጠይቁኝ የለኝም መልሳችሁ
mesfin
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  23:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 22:47:05 ሩቅ ነው!

የምትፈልገው፣ የምትመኘው፣ የምትናፍቀው ትልቅ ነገር ከምቾት ቀጠናህ እጅግ በጣም ሩቅ ነው፤ ዘወትር በልብህ የሚመላለሰው፣ በተደጋጋሚ የምትመለከተው፣ ከአዕምሮህ አልጠፋ ያለው ህልምህ ያለው ከምቾትህ በተቃራኒ አቅጣጫ ነው። ችግር ስለተደራረበ፣ ስቃይ ስለተፈራረቀ፣ ማጣት ስላጎሳቆለህ፣ መገፋት ስላሰቃየህ አታልቅስ፤ አትጨነቅ፤ ፈጣሪህንም አታማር። ጠንከር በል፣ የማያልፍ ነገር የለም፤ ሁሉም ያልፋል። ማለፉ ግን በዋዛ እንዳይሆን ብቻ ተጠንቀቅ። ሲያልፍ ቀይሮህ፣ አሳድጎህና ባርኮህ መሆን እንዳለበት ተረዳ። እያለቀስክ ሳይሆን እየተማርክ ወደፊት ተጓዝ፤ እያማረርክ ሳይሆን እያመሰገንክ መንገድህን ቀጥል፤ እያነስክ፣ እየሰነፍክ ሳይሆን ከፍ እያልክ፣ እየበረታህ መጪውን ጊዜ በተስፋ ተመልከት። በፈተናህ መሃል ዋጋህን ጨምር።

አዎ! ጀግናዬ..! ሩቅ ነው! ተመችቶኝ እቀየራለሁ፤ ከችግር ነፃ ሆኜ አድጋለሁ፤ በነፃነት እለወጣለሁ ብለህ የምታስብ ከሆነ አሁንም ስኬትህ በጣም ሩቅ ነው፤ ደስታህ ገና ነው፤ እውነተኛው ውስጣዊ ሰላምህ አልመጣም፤ ፈጣሪህን ከልብህ አላገኘሀውም። ምቾት ውስጥ እንደሆንክ ሲሰማህ መቅለጥ ትጀምራለህ፤ ወደ ኋላ መጓዝ፣ አቅምህን ማሳነስ፣ ለውጥን መሸሽ፣ በአንድ ነገር መወሰን ትጀምራለህ። ችግር ቢመጣ ካልገደለህ ሌላ ምን ልትሆን ትችላለህ? ግፋ ቢል አለኝ የምትለውን ነገር ቢያሳጣህ ነው፤ የሰዎች መዘባበቻና መጠቋቆሚያ ቢያደርግህ ነው፤ ግፋ ቢል ጭንቀት ውስጥ ቢከትህ፣ በሃሳብ ቢወጥርህ ነው። ነገር ግን ከዚያ በላይ ማየት ከቻልክ የለውጥህን ቁልፍ፣ የእድገትህን በረከት በእርሱ ውስጥ ታገኘዋለህ። "የማልወጣው አዘቅት ውስጥ ገብቼያለሁና ዋጋ የለኝም" ብለህ ከማሰብህ በፊት አዘቅት ያልከው ችግርህ ምን ይዞ እንደመጣ በጥሞና ተመልከት።

አዎ! ከዚም ከዛም ይንፈስ፣ ከላይም ከታችም ያስጨንቅህ፣ ገንዘብ ይጠርህ፣ የምትረዳው ነገር እጣ፣ ኑሮው ይወደድብህ ያኔ ለውጥ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነ ትረዳለህ፤ ያኔ እድገት ለደርድር የሚቀርብ ነገር እንዳልሆነ ትገነዘባለህ፤ ያኔ በጨለማ ውስጥ ብረሃንን ማሳደድ ትጀምራለህ። እንደፈለከው እየኖርክ፣ ሁሉን እያገኘህ፣ በሁሉ ተደግፈህ አዲስ ነገር አያለው፣ ትክክለኛው ማንነቴን እረዳለሁ፣ እራሴን አውቃለህ፣ ወደፊት እጓዛለሁ ብለህ እንዳታስብ። ከማጣት ቦሃላ የሚመጣ ማግኘት ብዙ ያስተምራል፤ ብዙ ከመገፋት ቦሃላ የሚገኝ ፍቅር ብዙ ዋጋን ይጨምራል። ባለህበት የተደላደለ ህይወት አትታለል፤ ዞር ዞር ብለህ እራስህን ፈትሽ፣ በችግርህ ውስጥ ማንነትህን አጉልተህ አሳይ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 22:46:30 የምትኖረውን ስራ!

አዎ! ስራህን ኑረው ወይም የምትኖረውን ስራ። እያማረርክና እየተናደድክ የምትጨርሰው ረጅም ጊዜ ያለህ እንዳይመስልህ። እያንዳንዱ ሰዓትህ ተመላሽ አይደለም፤ እያንዳንዱ ጊዜህ በምንም ቢያልፍ ውድና አይተኬ ነው። እንዳለመታደል ሆኖ የምትሰራውን ላትወደው ትችላለህ ነገር ግን ወደድክም ጠላህም እየኖርክ ያለሀው እርሱን እየሰራህ ነው። "ኑሮ እንዴት ነው?" ብትባል ቀድሞ የሚመጣልህ አሁን የምትሰራው ስራ ነው። ስራህን እንደ መዝናኛ መመልከት ብትችል ህይወትህን ማቅለል ትችላለህ፤ ከስራህ ጋር ብትዋሃድና ከልብህ ብትሰራው ማንም ባያይህም በብዙ እጥፍ ጥራትና ውጤትን ትጨምራለህ። መስራትህ ካልቀረ ከልበህ ስራው። እስከ መቼ እራስህንም ስራውንም እየበደልክ ትኖራለህ? የያዝከው ህይወት እንጂ ነገ የምትደግመው ጫወታ አይደለም። አንድ ስራህን እያማረርክ ህይወትህን ደስታ ቢስ ታደርገዋለህ፤ ሁለት ካንተ በማይጠበቅ ሁኔታ ስራውን ትበድላለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከሁለት አንዱን ካላደረክ ምንም አትቀይርም። የተሰጠህን አጭር እድሜ ጠዓም ለመስጠት አንድም ስራህን ኑረው ወይም የምትኖረውን ስራ። ስራህን ስትኖረው ከማንነትህ ጋር ይዋሃዳል፤ ስራ ሳይሆን ጫወታ ወይም መዝናኛ ይሆንሃል፤ ሁሌም ስታደርገው ደስተኛነትህ በእጥፍ ይጨምራል፤ ጊዜህን ቢወስድ፣ ቢፈትንህና ቢያደክምህ ላንተ ምንም አይደለም። የምትኖረውን ስትሰራም እንዲሁ መርጠሀው፣ ወደሀው፣ ፈልገሀው ትጀምረዋለህና ስሜቱ የተለየ ነው፤ ያለማንም ግፊት፣ ያለምንም ጫና በእራስህ ስለጀመርከው ብቻ ውስጥህ በሃሴት ይሞላል፤ ህይወትህ በእርሱ ትርጉም ያገኛል፤ በእርሱ ታርፋለህ፤ በእርሱ ትታደሳለህ፤ በእርሱ ትረጋጋለህ። ህይወታችንን በምንም ብናሳልፍ ማለፉ አይቀርም። ተደሰትን አዘንን፣ ተቆጨን አመሰገንን፣ አማረርን በስራችን ረካን ጊዜው ይሔዳል፤ ወቅቱ ይቀየራል፤ ነገሮች ይለዋወጣሉ።

አዎ! ምርጫ እንደሌለህ ካሰብክ ምንም ቢሆን ምርጫህ ተረጋግቶ፣ ተደስቶና ሰላም አግኝቶ ህይወትን ማጣጣም ነው። ለዚህም ሁነኛው መንገድ ስራህን መኖር፣ በውስጡ ህይወትን ማግኘት፣ ደስታን መፍጠር። ካልሆነም የምትኖረውን፣ የሚያኖርህን፣ እለት እለት የምትታደስበትን፣ ላንተ ትርጉም የሚሰጥህን እያደረጉ መኖር ነው። ምኑንም እንደነገሩ ሰርተሃል፣ ይህንንም ያንንም እየጀመርክ ትተሃል፣ ማንንም ስትከተል ከርመሃል ነገር ግን ዛሬም እዛው ነህ፤ ህይወትህ ለውጥ የለውም፤ በእራስህ ላይ ምንም አልጨመርክም። ጉዳዩ የገንዘብ፣ የንብረት ወይም የስምና የእውቅና ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ የእሴት (Value) ጉዳይ ነው። በህይወትህ ትርጉም የምታገኘው እሴት መጨመር ስትችል ነው። በምሬትና በለቅሶ፣ በሰበብና በቁጪት ደግሞ እንኳን እሴት መረጋጋትም ሊመጣ አይችልም። ህይወት ነገ እንደማትኖር እያሰብክ በሚገባ ኑራት፤ መቼ እንደምትቀማ አታውቅምና ባለህ አመስግንባት፤ እንዲኖርህ ለምትፈልገውም እንዳለህ አድርገህ አመስግን። በህይወት መሰንበትህ ውዷ ስጦታህ ናትና በስራህ ሙሉና አስደሳች አድርጋት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 22:46:07 ስብራትሽ ያበቃል!

ለእራስሽ ማሰብ ስትጀምሪ፣ ጨከን ስትዪ፣ እራስሽን ስትደግፊ፣ ዙሪያሽን ስትመለከቺ፣ አማራጮችን ስትቃኚ ሲያስጨንቅሽ የነበረው ነገር ሁሉ ተኖ ይጠፋል። ማንም የለሽም ብለው ችላ ቢሉሽ ተያቸው፤ ዋጋ የለሽም ብለው ቢርቁሽ ተያቸው፤ አታስፈልጊንም ብለው ቢያገሉሽ ተያቸው። ዳግም እንዲጎዱሽ አትፍቀጂ። ለእራስሽ ዋጋ ሲኖርሽ በሰዎችም ፊት ዋጋ ይኖርሻል። በወሬ ቢተቹሽ በስራ ብለጪያቸው፤ ስም በማጥፋት ሊጥሉሽ ቢሞክሩ እራስሽ ላይ በመስራት ተሽለሽ ተገኚ። ወደ ፊት ወደ ኋላ ማለት አያስፈልግም። አንዴ ሲገፉሽ የነበሩ ሁሉ ሊወዳጁሽ ቢጥሩ አትደነቂ። እራስሽን ስትጠብቂ፣ እራስሽን ስትወጂ፣ እራስሽን ስትንከባከቢ የማይመለከትሽ ሰው አይኖርም። ነገር ግን ለእራስሽ ተገን የምትሆኚው፣ ዋጋ የምትሰጪው በሰዎች ተቀባይነት እንድታገኚ፣ ሰዎች እንዲወዱሽ አይደለም። ለእራስ መወገን፣ እራስን መጠበቅ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነ ስለምታውቂ ነው።

አዎ! ጀግኒት.! እራስሽን ስታውቂ፤ ማንነትሽ ሲገባሽ፣ አንቺነትሽን ስትረጂ፣ ዋጋሽ ሲገለጥልሽ፣ ደረጃሽን ስትለዪ ስብራትሽ ያበቃል፤ እንባሽ ይታበሳል፤ ሃዘንሽ ይቆማል። ነገሮች በምክንያት እንደሚሆኑ ስታምኚ ያለ ጥፋትሽ ለበደለሽ፣ ክዶሽ ጥሎሽ ለሔደ ማዘን ትጀምሪያለሽ፤ በእርሱም ምክንያት ወደ እራስሽ በመምጣትሽ ታመሰግኚዋለሽ። "አንቺ እራስሽን ካልረዳሽ ማንም አይረዳሽም" የሚለው ንግግር ንግግር ብቻ አይደለም። ሁሉም ችግሮችሽ መፍትሔ የሚያገኙት ከማንም በላይ አንቺ እራስሽን ስትረጂና እራስሽን ስትረጂ ብቻ ነው። ጠንካራ ሴት መሆን ምርጫ ሳይሆን ግዴታሽ ነው። በጣም ብዙ ሃላፊነቶች እንደሚጠብቁሽ አስቢ፤ ከጊዜያዊ ችግሮችሽ በላይ የሙሉ ህይወትሽ ቁልፍ በእጅሽ እንደሆነ ተገንዘቢ። ከእንድ ሰው ጫወታ ሜዳ ብትወጪ የእራስሽ የግል መጫወቻ ሜዳ እንዳለሽ አስታውሺ። ከምንም በፊት እራስሽን ጠግኚ፤ እራስሽን አበርቺ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሰው (High Value Man) ስትሆን ውድና ተፈላጊ ሰው ትሆናለህ። እንደ በፊቱ የፈለገህ ሁሉ አያገኝህም፤ ያልተፈለክበት ቦታም አትገኝም፤ እንደ ቀድሞው ሲጠሩህ አቤት ሲልኩህ ወዴት አትልም። ዛሬ ትጠይቃላህ፣ ታመዛዝናለህ፤ የምትላክበት ስፍራ ካንተ አላማ ጋር መሔዱን ታገናዝባለህ። የመሸወድ፣ የመታለል፣ የመበላት ጊዜ አብቅቷል። ጥለውህ ስለሔዱ፣ ስለካዱህና የማይሆን ስም ስለሰጡህ ጥግ ይዘህ የምታለቅስ ወይም የማይሆን ሱስ ውስጥ የምትገባ አይደለህም። ዋጋህን ከፍ በማድረግ፤ ጥራትህን በመጨመር፤ ደረጃህን በማስተካከል ማንነትህን ታሳያለህ። ሲጫወቱበት ነበሩት ሰው ሁሌም መጫወቻ ሆኖ አይቀጥልም፤ ሲቀለድበት የነበረ ሰው ሁሌም መቀለጃ ሆኖ አይቀርም። ማንም ደጋግሞ ቢጥልህ ደጋግመህ እራስህን የማንሳት ግዴታ አለብህ። ለእራስህ ማድላትን፣ ለእራስህ መወገንን ምርጫ አታድርገው። ካንተ ቦሃላ የሚመጡትን ነገሮች አቆያቸው፤ አስቀድመህ እራስህን ታደግ፤ እራስህን አጠንክር።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 19:10:22
የወሎ ልጅ አፍቅሬ የገጠምኳት ግጥም

የሙሐባ ችግኝ የፍቅር አዝመራ፣
ደሴ ላይ ተዘርቶ ሐይቅ ላይ አፈራ።
ውጫሌና እሮቢት ሊብሶን ይዞ ሐብሩ፣
ውብ ይወጣበታል ጋራው ሸንተረሩ።
ጊራና ወርጌሳ ሐራና ወልዴያ፣
የማይጠገበው የቆንጆ መብቀያ።
መርሳ ራያ ቆቦ የጀግኖቹ መንደር
በክፉ ለመጡ የማይደራደር።

ኧረ ወሎ ወሎ ምድሩ ገደላማ፣
ያበቅላል ከስሩ አንገተ መለሎ አይነ ኮለምላማ።
ኮምቦልቻና ባቲ ደጋንና ገታ፣
ደግነት ልምዳቸው ሳቅና ፈገግታ።

ሐርቡና ከሚሴ ሚጢቆሎ አንቻሮ፣
ፍቅር በጅምላ ነው የለም በችርቻሮ።
ተንታና መቅደላ ከላላ ወግዴ፤
ልቤ ናፍቆብኛል አልቀረም መሄዴ።
አቃስታ ገነቴ ለሚና ቀይመብራት፣
ትዝታው ከመጣ አያስበላም እራት።

ወረኢሉ ካቤ ጃማና ልጓማ፣
ያፈራል ሸበላ ቆንጆ ውብ አይናማ።
መካነሰላምን የሸሆቹን አገር፤
አይቼው በመጣሁ ሂጄ በወፍ በረር።
አጅባርና ማሻ ተንታና ደጎሎ፣
ልጆቹ ሸንቃጦች አንገተ መለሎ።

ጉጉፍቱና ጊንባ አየረ ቀዝቃዛ፣
የሚታፈስበት ፍቅር እንደዋዛ።
ዋድላና ደላንታ መገን ወገልጤና
ሐገሩ እህል አብቃይ ሰው መልከቀና።
ወረባቦን ብየ ልዝለቅ በቢስቲማ:
ገደራ ነው ምንጩ ፍቅር ለተጠማ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 18:17:55 ድጋሜ ሞክረው!

ምንም ያክል ዋጋ ያስከፍልህ ድጋሜ ሞክረው፤ ያስወጣህን ያስወጣህ አሁንም ደግመህ አድርገው። እስኪያኮራህ፣ አንገትህን ቀና እስኪያደርግ፣ ልብህን እስኪያስደነድን በፍፁም ከማድረግ እንዳትቦዝን። ሙከራህ ዋጋ አለው፤ የማይቋረጥ ጥረትህ ይቆጠራል፤ በስተመጨረሻም ይከፍልሃል። ከምትባለው በላይ ነህ፤ ከሚወራብህ ትናንሽ ነገር ትበልጣለህ። ሀ ብለህ ስትጀምር ሃላፊነት መውሰድ እንዳለብህ ታውቃለህ፤ መርጠህ፣ ፈልገህ፣ ወስነህ መጀመርህ ደግሞ ሃላፊነት እንዲሰማህና ይበልጥ እንድትጠነክር ያደርግሃል። የምትችለው ወድቆ መቅረት አይደለም፤ የሚመጥንህ በመሃል ማቋረጥ አይደለም፤ የሚገልፅህ የጅምሮች ብዛት አይደለም። የጀመርከውን የመፈፀም ሃላፊነት አለብህ፤ ምቾት ማጣትን መላመድ አለብህ፤ ትቺትና ጫናውን መቻል ይኖርብሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ድጋሜ ሞክረው! ተስፋ መቁረጥ፣ ወደኋላ መመልከት፣ መሰናክሎችን መቁጠር፣ ችግሮችን ማጋነን፣ ሁኔታዎችን ማወሳሰብ አቁም። ካልደጋገምክ የትም እንደማትደርስ እወቀው። አንዴ ሞክሮ በማቆምና ደጋግሞ እስኪሰለችህ መሞከር መሃል ጥልቅ ፍላጎት የተሰኘው ልዩነት ፈጣሪ ነገር አለ። ካልፈለከው አትገደድም፤ ከፈለከው ግን የምታቆመው ስታሳካው ብቻ ነው። አንተ ቢደክምህ ውስጥህ አይደክመውም፤ አንተ ብትሰበር ውስጥህ አይሰበርም፤ አንተ ብትሰለች ውስጥህ አይሰለችም። እችላለሁ ከምትለው በላይ እንደምትችል የሚያረጋግጥልህ ማንም ሳይሆን የማያቋርጠው ጥረትህ ነው፤ እልህ አስጨራሹ ትጋትህ ነው። የትም ብትሔድ ድጋሜ እንድትሞክር የሚገፋህ ሃይል ውስጥህ አለ፤ ከየትኞቹም ብርታትና አነቃቂዎች በተሻለ እርሱ ያበረታሃል፤ እርሱ ያነቃቃሃል።

አዎ! በጫና፣ በግፊት፣ በሰዎች አበረታችነት አንዴ ልትሞክር ትችላለህ፤ ለእራስህ፣ በእራስህ ፈልገህ መርጠህና ወደህ ከጀመርክ ግን የመደጋገሙ ጥያቄ አያሳስብህም። ከጅማሬህ ማግስት ረጅም ርቀት እንዳለ ልብህ ያውቀዋል፤ በአጭሩ የትም እንዳማትደርስ ውስጥህ ያውቃል። በሙከራህ ሂደት እዚህ ደርሰሃል። ወደኋላ ብትመለከት፣ ለአፍታ እራስህን ብትቃኝ ከዛሬው ማንነትህ ፍፁም የተለየውን አንተን ትመለከታለህ። በሙከራህ ውስጥ አድገሃል፤ በጥረትህ ትክክለኛውን ማንነትህን ተገንዝበሃል፤ ያንተ የሆነውን የሚያስደስትህንና የሚገልፅህን አውቀሃል። መቼ ታቁም አታቁም ባታውቅም መቀጠል እንዳለብህ ግን ውስጥህ ይነግርሃል። ለመጀመር ረጅም ጊዜ ወስደሃል፤ ለማቆምም ይህንኑ ታደርጋለህ። ያንተ ያልሆነን ነገር መደጋገም ላይጠበቅብህ ይችላል፤ ያንተ የሆነውን ግን መተው አትችልም። በጫና ውስጥ ብትሆንም ሙከራህን ቀጥል፤ ብዙ ያልተመቸህ ነገር ቢኖርም ለውስጥ ፍላጎትህ፣ ለልብ መሻትህና ለማያቋርጠው ፅኑ ምኞትህ ብለህ ጥረትህን ቀጥል፤ ህይወትህን አሸንፍ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.8K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ