Get Mystery Box with random crypto!

ስብራትሽ ያበቃል! ለእራስሽ ማሰብ ስትጀምሪ፣ ጨከን ስትዪ፣ እራስሽን ስትደግፊ፣ ዙሪያሽን ስትመለ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ስብራትሽ ያበቃል!

ለእራስሽ ማሰብ ስትጀምሪ፣ ጨከን ስትዪ፣ እራስሽን ስትደግፊ፣ ዙሪያሽን ስትመለከቺ፣ አማራጮችን ስትቃኚ ሲያስጨንቅሽ የነበረው ነገር ሁሉ ተኖ ይጠፋል። ማንም የለሽም ብለው ችላ ቢሉሽ ተያቸው፤ ዋጋ የለሽም ብለው ቢርቁሽ ተያቸው፤ አታስፈልጊንም ብለው ቢያገሉሽ ተያቸው። ዳግም እንዲጎዱሽ አትፍቀጂ። ለእራስሽ ዋጋ ሲኖርሽ በሰዎችም ፊት ዋጋ ይኖርሻል። በወሬ ቢተቹሽ በስራ ብለጪያቸው፤ ስም በማጥፋት ሊጥሉሽ ቢሞክሩ እራስሽ ላይ በመስራት ተሽለሽ ተገኚ። ወደ ፊት ወደ ኋላ ማለት አያስፈልግም። አንዴ ሲገፉሽ የነበሩ ሁሉ ሊወዳጁሽ ቢጥሩ አትደነቂ። እራስሽን ስትጠብቂ፣ እራስሽን ስትወጂ፣ እራስሽን ስትንከባከቢ የማይመለከትሽ ሰው አይኖርም። ነገር ግን ለእራስሽ ተገን የምትሆኚው፣ ዋጋ የምትሰጪው በሰዎች ተቀባይነት እንድታገኚ፣ ሰዎች እንዲወዱሽ አይደለም። ለእራስ መወገን፣ እራስን መጠበቅ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነ ስለምታውቂ ነው።

አዎ! ጀግኒት.! እራስሽን ስታውቂ፤ ማንነትሽ ሲገባሽ፣ አንቺነትሽን ስትረጂ፣ ዋጋሽ ሲገለጥልሽ፣ ደረጃሽን ስትለዪ ስብራትሽ ያበቃል፤ እንባሽ ይታበሳል፤ ሃዘንሽ ይቆማል። ነገሮች በምክንያት እንደሚሆኑ ስታምኚ ያለ ጥፋትሽ ለበደለሽ፣ ክዶሽ ጥሎሽ ለሔደ ማዘን ትጀምሪያለሽ፤ በእርሱም ምክንያት ወደ እራስሽ በመምጣትሽ ታመሰግኚዋለሽ። "አንቺ እራስሽን ካልረዳሽ ማንም አይረዳሽም" የሚለው ንግግር ንግግር ብቻ አይደለም። ሁሉም ችግሮችሽ መፍትሔ የሚያገኙት ከማንም በላይ አንቺ እራስሽን ስትረጂና እራስሽን ስትረጂ ብቻ ነው። ጠንካራ ሴት መሆን ምርጫ ሳይሆን ግዴታሽ ነው። በጣም ብዙ ሃላፊነቶች እንደሚጠብቁሽ አስቢ፤ ከጊዜያዊ ችግሮችሽ በላይ የሙሉ ህይወትሽ ቁልፍ በእጅሽ እንደሆነ ተገንዘቢ። ከእንድ ሰው ጫወታ ሜዳ ብትወጪ የእራስሽ የግል መጫወቻ ሜዳ እንዳለሽ አስታውሺ። ከምንም በፊት እራስሽን ጠግኚ፤ እራስሽን አበርቺ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሰው (High Value Man) ስትሆን ውድና ተፈላጊ ሰው ትሆናለህ። እንደ በፊቱ የፈለገህ ሁሉ አያገኝህም፤ ያልተፈለክበት ቦታም አትገኝም፤ እንደ ቀድሞው ሲጠሩህ አቤት ሲልኩህ ወዴት አትልም። ዛሬ ትጠይቃላህ፣ ታመዛዝናለህ፤ የምትላክበት ስፍራ ካንተ አላማ ጋር መሔዱን ታገናዝባለህ። የመሸወድ፣ የመታለል፣ የመበላት ጊዜ አብቅቷል። ጥለውህ ስለሔዱ፣ ስለካዱህና የማይሆን ስም ስለሰጡህ ጥግ ይዘህ የምታለቅስ ወይም የማይሆን ሱስ ውስጥ የምትገባ አይደለህም። ዋጋህን ከፍ በማድረግ፤ ጥራትህን በመጨመር፤ ደረጃህን በማስተካከል ማንነትህን ታሳያለህ። ሲጫወቱበት ነበሩት ሰው ሁሌም መጫወቻ ሆኖ አይቀጥልም፤ ሲቀለድበት የነበረ ሰው ሁሌም መቀለጃ ሆኖ አይቀርም። ማንም ደጋግሞ ቢጥልህ ደጋግመህ እራስህን የማንሳት ግዴታ አለብህ። ለእራስህ ማድላትን፣ ለእራስህ መወገንን ምርጫ አታድርገው። ካንተ ቦሃላ የሚመጡትን ነገሮች አቆያቸው፤ አስቀድመህ እራስህን ታደግ፤ እራስህን አጠንክር።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q