Get Mystery Box with random crypto!

የወሎ ልጅ አፍቅሬ የገጠምኳት ግጥም የሙሐባ ችግኝ የፍቅር አዝመራ፣ ደሴ ላይ ተዘርቶ ሐይቅ ላይ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የወሎ ልጅ አፍቅሬ የገጠምኳት ግጥም

የሙሐባ ችግኝ የፍቅር አዝመራ፣
ደሴ ላይ ተዘርቶ ሐይቅ ላይ አፈራ።
ውጫሌና እሮቢት ሊብሶን ይዞ ሐብሩ፣
ውብ ይወጣበታል ጋራው ሸንተረሩ።
ጊራና ወርጌሳ ሐራና ወልዴያ፣
የማይጠገበው የቆንጆ መብቀያ።
መርሳ ራያ ቆቦ የጀግኖቹ መንደር
በክፉ ለመጡ የማይደራደር።

ኧረ ወሎ ወሎ ምድሩ ገደላማ፣
ያበቅላል ከስሩ አንገተ መለሎ አይነ ኮለምላማ።
ኮምቦልቻና ባቲ ደጋንና ገታ፣
ደግነት ልምዳቸው ሳቅና ፈገግታ።

ሐርቡና ከሚሴ ሚጢቆሎ አንቻሮ፣
ፍቅር በጅምላ ነው የለም በችርቻሮ።
ተንታና መቅደላ ከላላ ወግዴ፤
ልቤ ናፍቆብኛል አልቀረም መሄዴ።
አቃስታ ገነቴ ለሚና ቀይመብራት፣
ትዝታው ከመጣ አያስበላም እራት።

ወረኢሉ ካቤ ጃማና ልጓማ፣
ያፈራል ሸበላ ቆንጆ ውብ አይናማ።
መካነሰላምን የሸሆቹን አገር፤
አይቼው በመጣሁ ሂጄ በወፍ በረር።
አጅባርና ማሻ ተንታና ደጎሎ፣
ልጆቹ ሸንቃጦች አንገተ መለሎ።

ጉጉፍቱና ጊንባ አየረ ቀዝቃዛ፣
የሚታፈስበት ፍቅር እንደዋዛ።
ዋድላና ደላንታ መገን ወገልጤና
ሐገሩ እህል አብቃይ ሰው መልከቀና።
ወረባቦን ብየ ልዝለቅ በቢስቲማ:
ገደራ ነው ምንጩ ፍቅር ለተጠማ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q