Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.43K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-28 07:43:26 ዛሬ መልካም ይሆናል!

እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እነሆ ዛሬ መልካም ቀንን ለማየት በቃን። ያለፈው እንዳለፈ ሆኖ፣ የቀረውም ቀርቶ፣ የመጣውም መጥቶ ለዚህ በቅተናል። ማግኘት የሚገባንን አግኝተናል፤ የሚገባን ስፍራ ተገኝተናል፤ የማይታለፉ የሚመስሉ ጊዜያት አልፈው ታሪክ ሆነዋል፤ እንደ አምላክ ፍቃድ በሰላም በጤና ልናመሰግነው በቅተናል። የሆነው ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ የሚነጋው የሚመሸው፣ የምናርፈው የምንነቃው ዳግም የምንታደሰው እንደ እርሱ መልካም ፍቃድ ነው። ያኔ ብቻህን ስትሆ ውስጥህ ምን ይልህ ነበር? ያኔ አጣብቂኝ ውስጥ ሆነህ ምን ይሰማህ ነበር? ያኔ ተስፋህ ከጫፍ ሲደረስ ምን ታስብ ነበር? ዛሬ ከባዶቹ ጊዜያት አልፈዋል፤ ዛሬ መጥፎዎቹ ቀናት ታልፈዋል፤ ዛሬ አስጨናቂዎቹ ወቅቶች ታሪክ ለመሆን በቅተዋል።

አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬ መልካም ይሆናል! ዛሬ እፁብ ድንቅ አስደሳች ቀን ይሆናል። መልካም ይሆን ዘንድም ያንተ ስራ በአምላክህ ፍፁም እንከን አልባ ተግባር መተማመን ነው፤ ሁሉን ለእርሱ መተው ነው፤ ተስፋህን በማይናወጠው ክንዱ ላይ ማድረግ ነው። በእግዚአብሔር የሚታመኑ፣ በአምላካቸው የሚተማመኑ፣ ፈጣሪያቸውን የሚደገፉ ነፍሳት ብፁዓን ናቸው። መከራ አያገኛቸውም፤ ስቃይ አይቀርባቸውም፤ ተስፋ መቁረጥ አይጠጋቸውም። ምክንያቱም የሚሆነው ሁሉ በእርሱ ፍቃድ እንደሚሆን ያውቃሉና ነው፤ ምክንያቱም እየሆነ ያለውም በእርሱ ይሁንታ መሆኑን ስለሚረዱ ነው፤ ምክንያቱም ትንሹንም ትልቁንም ተግባር ከመፈፀማቸው በፊት ከአምላካቸው  ስለሚማከሩ ነው። የቀንህ መልካምነት፣ የውሎህ ስኬታማነትና አስደሳችነት ካሳሰበህ ከምንም በፊት እጆችህን ለዚች ውብ ንጋት ብለህ ለምስጋና ዘርጋ፤ ስላለህና ስለሌለህ ነገር ሁሉ ለአምላክህ የሚገባውን ስጠው።

አዎ! "ከእኛ የሆነ አንዳች የለም ሁሉም ከእርሱ ነው።" እንደሚል ቃሉ፣ ነገሮች ሲሆኑ ለመልካም፣ ሳይሆኑም ሲቀሩ ለመልካም፣ ለበጎ እንደሆነ ማሰብ ተገቢ ነው። አሸናፊነት ቀንን በንጋት ከማሸነፍ ይጀምራል፤ ስኬት የአምላክን መልካም ፍቃድ በበጎ ከመረዳት ይነሳል። ሮጠህ ሮጠህ አንድ ቀን ትደክማለህ፤ ለፍተህ ለፍተህ አንድ ቀን ትዝላለህ፤ ውስጥህ ያለው የህያው አምላክ መንፈስ ግን መቼም አይደክምም፤ መቼም አይዝልም። ገና ሳትኖር "ህይወት በቃኝ፣ ከበደኝ፣ ደከመኝ፣ አሰቃየኝ" አትበል። ድካምህ ምን ይዞልህ እንደሚመጣ አታውቅም፤ ስቃይህ ልምን እንደሚያበቃህ አታውቅም። አምላክህ ስራውን ሰርቶ እስኪጨርስ ጊዜ ስጠው፤ ከዛ ቦሃላ ሁሉም ውብና እጅግ ያማር መልካም እንደሚሆን ትመለከታለህ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
5.9K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 07:42:54 በአሉታዊነት አትሰለጥንም!

በህይወት የማያጋጥም ነገር የለምና ጠንቅቀህ ስለምታውቀው፣ በሚገባ ስለተረዳሀውና ስለገባህ ነገር አሉታዊ ንግርን ትሰማ ይሆናል። ካንተ ምላሽ የሚሹ ነገሮች ደጋግመው ይመጡብሃል፤ ሰምተህ እንዳልሰማ ለመሆን ብትሞክር ሌላ ስም ይወጣልሃል፤ እንደ ሰማህ ምላሽ ብትሰጥ ደግሞ ይበልጥ ማንነትህ ይፈተናል። አሉታዊ ንግግሮች ላይ ብለሃትህን መጠቀም ካልቻልክ ተጠልፈህ መውደቅህ የማይቀር ጉዳይ ነው። አሸናፊነትህ አሉታዊነትን ለመሻገር የምትጠቀመውን ጥበብ ይፈልጋል፤ ትልቁ መዳረሻህ መሰናክሎችህን ለመሸጋገሪያነት የምትጠቀምበትን ብለሃት ይፈልጋል። ለረጅም ጊዜ ተምረሃል፤ ከብዙ ሰዎች ጋር አውርተሃል፤ ብዙ ጓደኞችም አፍርተሃል ነገር ግን ያተረፍከው ምን እንደሆነ ለማወቅ ለእነርሱ ያለህን ስሜት አስተውል።

አዎ! ጀግናዬ..! በአሉታዊነት አትሰለጥንም! በጥላቻ የትም አትደርስም፤ ክፍተቶችን ብቻ በመቁጠር ለምንም አትበቃም። ከምንም በላይ የአሉታዊነትህን ምንጭ መርምር፣ ምክንያቱን እወቅ። ቂም ነው? በቀል ነው? ጥላቻ ነው? ወይስ ምክንያት አልባ የመንጋ አስተሳሰብ ነው? አንተ አሉታዊ ባትሆንና አካባቢህ ዘወትር ክፍተትና ህፀፅ የሚደረድርልህ ከሆነ ወደህ ሳይሆን ተገደህ የአካባቢህ ነፀብራቅ ትሆናለህ። ብልህ ሰው የማይመቸው ስፍራ ሰከንዳትን ማሳለፍ አይፈልግም። የምታየው ነገር ምንም ስሜት የማይሰጥህ፣ የምትሰማው ወሬ ከልብህ የማይገባ ከሆነ ምን እያደረክ እንደሆነ እራስህን ጠይቅ። እራሱ እየጠፋ ለሌሎች ብረሃን ለመሆን ከሚሞክር አይነት ማንነት ካለው ሰው እራስህን ነጥል። ጫና ውስጥ ልትወድቅ ትችላለህ፣ አማራጭም አጥተህ ይሆናል ለአሉታዊነት መገዛትና በእርሱ መንገድ ህይወትን መምራት ግን አማራጭ ሊሆንህ አይገባም።

አዎ! በፍፁም ከማትደራደርባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ከመልካም ተግባር ተቃራኒዎች ጎራ ተሰልፈህ መገኘት ነው። ችግሮችህን መቀነስ ከፈለክ ቃላት እየቀያየርክ ደጋግመህ አትተነትናቸውም፤ ወደፊት መጓዝ ከፈለክ በአሉታዊነት አጥር ውስጥ እራስህን አታስቀምጥም፤ መሰናክሎችህን መሻገር ከወደድክ በጭፍን ጥላቻ ሰንሰለት እራስህን አታስርም። ጨለማን በብረሃን እንደምታሸንፈው፣ አሉታዊውን ሰባሪና ተስፋ አስቆራጭ ሃሳብም የምታሸንፈው በአዎንታዊነትና በላቀ፣ በማይናወጥ ፅኑ ተስፋ ወእምነት ነው። ስልጣኔህን ከአሉታዊነት ይልቅ አዎንታዊነትን ለማጉላት፣ ስጦታዎችህን ለማንፀባረቅ፣ ምርጫዎችህን ለመኖር ተጠቀመው። ህይወትህን ለማሸነፍ አንደኛው መሳሪያህ አዎንታዊነት እንደሆነ አስታውስ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 07:42:25 አንተ ብቻ ነህ!

አዎ! ቀንህ ላይ የምትወስነው፣ ምስጋናን የምታስቀድመው፣ ተስፋን የምትሰንቀው፣ ህይወትህን በሙላትና በትጋት የምትኖረው፣ ከቀደመው ታሪክህ የምትማረው፣ ለመጪው ይበልጥ የምትጠነክረው፣ እራስህ ላይ የምትሰለጥነው አንተ ብቻ ነህ። የሚረብሹ ነገሮች ቢኖሩም የማትረበሸው፣ ተስፋ አስቆራጭ ተግባራትን ብትመለከትም ተስፋ የማትቆርጠው፣ ቢደክምህም የምትበረታም፣ ቢደብርህም የምትነቃቃው አንተ ነህ። በየእለቱ ለምታያቸው አዳዲስ ቀናቶች፣ አዳዲስ እድሎች ከምንም በላይ ማመስገንና በእነርሱ መደሰት ይገባሃል። በረከቶችህን ለመቁጠር ምን ነገር አድርገሃል? ፀጋህን ለማብዛት፣ ስጦታህን ለመጨመርስ የትኛውን መንገድ ተከትለሃል? አንሶኛል፤ አይበቃኝም፤ እኔ ተጎድቼያለሁ ጨምርልኝ? ወይስ ባለኝ ደስተኛ ነኝ፤ ያለኝ ይበቃኛል፤ የጎደለኝን አንተው አይተህ ሙላልኝ?

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ብቻ ነህ! ምንም እንኳን አሁን ባለህበት ሁኔታ ደስታና እርካታ ባይሰማህ ከዚህ ለመውጣት ካንተ ውጪ ሊረዳህ የሚችል አካል የለም። እግዚአብሔርም የሚረዳህ፣ አምላካህም የሚያግዝህ በሃይል አምነህ፣ ከልብህ ተማምነህበት፣ እራስህን ሰጥተህ፣ ወደርሱ ቀርበህ መሻትህን ስታስረዳው፣ ጭንቀትህን ስታካፍለውና ምላሹን በተስፋ ስትጠብቅ ነው። ሃላፊነት የሚሰማህ ከሆነ በቅድሚያ አሁን ስላለህበት ሁኔታ ማስተዋልና ማጤን ጀምር፤ የት እንዳለህ ጠንቅቀህ እወቅ፤ በረከቶችህ ምን እንደሆኑ፣ ምን እንደተሰጠህ፣ ከምን ላይ ምንን ማግኘት እንደምትችል ተገንዘብ። በረከቶችህን እንድትመለከት አይንህን ይገልጡልህ ይሆናል እንጂ ማንም ይህን አለህ፣ ያንን አለህ የሚልህ ሰው እንደሌለ እወቅ።

አዎ! በሚታዩህ ብዙ ችግሮችና ክፍተቶች ልትሞላ ትችላል፣ ዘወትር ደካማ ጎንህ እየተገለጠም ያስቸግርህ ይሆናል። ነገር ግን የእይታህን አቅጣጫ ማስተካከል ከቻልክ፣ ማድረግ የሚገባህን ካስተዋልክ፣ ፍላጎትህን ከተረዳህ ህይወትህን ለማስተካከል በምታሳየው ቆራጥነት ካለህበት የዝቅታ ስፍራ ተነስተህ ከከፍታው መድረስ ትችላለህ፤ ካለህበት ክፍተት ተነስተህ የብዙዎችን ክፍተት መሙላት ትችላለህ፤ ከእራስህ የግል ችግር በመነሳት ለቦዙዎች ችግር መፍትሔ መሆን ትችላለህ። ቆም ብለህ እራስህን ተመልከት። "አይዞህ፣ ትችላለህ፣ በርታ!" የሚልህን መስማት ያዋጣሃል ወይስ በችግር ላይ ችግርን እየደራረበ የሚተነትንልህን መስማት? ምርጫው ያንተና ያንተ ብቻ ነውና ለእራስህ ህይወት ሃላፊነት በመውሰድ ለእራስህ ተገን፣ ለእራስህ ድጋፍ መሆኑን እወቅበት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 21:08:24 በኢትዮጵያ በየትኛውም ሃይማኖት የሚደርስ ግፍን እቃወማለሁ ። ሰሞኑን የእስልምና ሃይማኖት ፀሎት ቤት በሆኑት መስጂዶች ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም እላለሁ ! ፈጣሪ ሁሉ ነገር አስተካክሎ ነገሮች ወደነበሩበት ይመልስልን ። ሰላም ለኢትዮጵያ
4.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 14:42:46 በሆኑ ሰዎች ትወገዛለህ!
ማንም ሁን ፣ ምንም አድርግ ፣ እንዴትም አድርግ ፣ እንደምንም ተገኝ ፣ የቱንም ድንቅ ተዓምር ነገር ስራ ብቻ የሆኑ ሰዎች ይጠሉሃል ፤ በሆኑ ሰዎች ትወገዛለህ ፣ በሆነ ማህበረሰብ ዘንድ እንድ መጥፎ ትታያለህ ፤ በሆነ ቡደን ጥፋተኛ ትደረጋለህ ። በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ አንደኛው የህይወት እውነታ ነው ፤ በማንነትህ የሚገጥምህ ነገር ነው ። እንዲሁ ሳያውቁህ አይተው የሚጠሉህ ሰዎች አሉ ፤ እንዲሁ ከባዶ "ቀልቤ አልወደደውም" የሚሉህ ሰዎች አሉ ። ለመጥላታቸው ምክንያት ቢጠየቁ ግን "ይህን አድርጎኛል ፣ በዚህ መልኩ በድሎኛል" የሚሉት ምክንያት እንኳን የላቸውም ። እንዲሁ ስሜታቸው ስላልወደደህ ብቻ አትመቻቸውም ፣ ሲያዩህ ይጎረብጣቸዋል ፤ ድምፅህን ሲሰሙ ይነዝራቸዋለ ፤ ስላንተ ሲያወሩ ይጠየፉሃል ፤ መጥፎ ቃላት ይመርጡልሃል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ይህ ህይወት ነው! በሆኑ ሰዎች ትወገዛለህና ምንም ማድረግ አይቻልም ። የሚጠሉህ ሰዎች ምክንያት ቢኖራቸው መልካም ነበር ፣ ያደረካቸው ነገር ቢኖር ጥሩ ነበር ። ነገር ግን ምንም በሌለበት ፣ ይባስ ብሎ ማንነትህን ፣ ስራህን እንኳን በቅጡ ሳያውቁት ስላንተ ክፉ ያወራሉ ፣ ያሙሃል ፣ ያንቋሽሹሃል ፣ ይተቹሃል ፣ ይንቁሃል ። አንተ ወደላይ እየገሰገስክ ነው ፣ እነርሱ ግን በሃሳባቸው ሊያወርዱህ ይታገሉሃል ፤ አንት ህልምህን በሙላት እየኖርክ ነው ፣ እነርሱ ግን ዘወትር ቡና መጠጫ ያደርጉሃል ፤ አንተ የሚያዋጣህን ይዘህ ደስተኛ ሆነሃል እነርሱ ግን ባንተ ምክንያት ቀናቸውን ያበላሻሉ ። የህይወትን ሚዛን መጠበቅ ከፈለክ ሁሉንም እንዳመጣጡ የማስተናገድ ግዴታ አለብህ ። እንዲሁ አይቶ የሚወደህ ሰው እንደመኖሩ እንዲሁ በባዶ የሚጠላህና እንከን የሚያወጣልህም እንዳለ መቀበል ይጠበቅብሃል ። አንዳንዴ ተቃዋሚዎችህ ምክንያት እንደሌላቸው አውቀህ ችላ ልትላቸው ይገባል ።

አዎ! ለሁሉ መልስ እየሰጠህ ፣ ሁሉንም እያስረዳህ ፣ ከሁሉም ጋር ለመስማማት እየጣርክ የተረጋጋ ህይወት ለመኖር አትሞክር ። ያለምክንያት የሚጠላህን ሰው ልታደርግለት የምትችለው ብቸኛ ነገር እንዲያውቅህ እንድሉን ማመቻቸት ብቻ ነው ። አንተ በደስታ እየኖርክ ፣ ውስጥህ ሰላም ሆኖ ፣ እራስህን እየቀየርክ ፣ ለእራስህ ቦታ እየሰጠህ ፣ ከአምላክህ ጋር በፍቅር እየኖርክ ማንም እንዲ ነህ ፤ እንደዛ ነህ ቢልህ ምን የሚቀንስብህ ነገር አለ ? ፈጣሪህን አታሳዝን ፣ ህይወትህን አታበላሽ ፣ ሰዎችን አትጉዳ እንጂ በፈለከው መንገድ እራስህን መሆንህ ከማን ምንን ያጎድላል ? ከማን በታችስ ያደርግሃል ? በአንዳንድ ሰዎች ያለምክንያት መጠላትህ ፣ በተወሰኑ ሰዎች መገፋትህ ፣ ዋጋህን ማጣትህ ምንም ማለት እንዳልሆነ እወቅ ። ተፈጥሮን መቃረን ከማትችልባቸው ነገሮች አንዱ ያለምክንያት የሚጠሉህ ሰዎች መኖራቸው እንደሆነም ተረዳ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.9K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 14:40:28 በህልምህ አትፈር!
አዎ! ላንተ ብቻ በታየህ አንተንና ዙሪያህን ቀያሪ ህልም በፍፁም አትፈር ፤ አንተ ብቻ ስታስበው አስደናቂ ስሜት እንዲሰማህ በሚያደርግህ ህልምህ አትሸማቀቅ ፤ ለአንተ ብቻ በህሊናህ ለሚመላለሰው ተዓምራዊ ሃሳብ እራስህን አትውቀስ ። ህልምህ ስለሚገባህ ወዳንተ መጥቷል ፤ አላማህ ያንተ ስለሆነ ለአመታት ተከትሎሃል ፤ ራዕይህ ባንተ ላይ መስራት ስለፈለገ አንተን ተዋህዷል ። በእግዚአብሔር ስጦታ አይታፈርም ፤ በአምላክ ድንቅ ምርጫ መሸማቀቅ ፣ አንገት መድፋት የለም ። ሁሉን ለእራስህ የምትሰጠው አንተ አይደለህም ፤ ሁሉን ለእራስህ የምትመርጠው ፣ የሚበጅህን ለእራስህ የምታደርገው አንተ አይደለህም ። ይህ ሁሉ ስራ የፈጣሪ ነው ። ሲፈጥርህ ላንተ የሚሆን ስራ አዘጋጅቶልሃል ፤ ከእራስህ በላይ ምድር ላይ ተፅዕኖ የምትፈጥርበትን ዘርፍ አስቀምጦልሃል ፤ ባንተ ብቻ ምርጥ ተደርጎ ለሚሰራ ተግባር በእጩነት አዘጋጅቶልሃል ። በህልሙ የሚያፍርና የሚሸማቀቅ ሰው በአምላኩ ድንቅ ስጦታ የሚያፍር ሰው ብቻ ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! በህልምህ አትፈር! ስንተ አሳፋሪና አስነዋሪ ነገር በአደባባይ ሲደረግ በማያሳፍርበት አለም ስለምን በአዎንታዊውና ተዓምራዊው የእግዚአብሔር ስጦታ ታፍራለህ ? እንዴትስ አንተን ፣ ቤተሰቦችህን ፣ ሀገርህን ፣ አህጉርህንና አለምን መቀየር በሚችል ድንቅ የአምላክ ፖኬጅ ትሸማቀቃለህ ? የሰጠህ አምላክ ነው ፤ ባንተ መልካም ፍቃድም የሚያኖርህ ፣ እንድትለወጥበት ፣ ተፅዕኖ እንድትፈጥርበት የሚደርግህም እርሱ እራሱ ነው ። ተፈጥሯችን ድንቅ መሆኑን ለማወቅ ህልማችንን ስንኖር የሚሰማንን ድንቅ ስሜት ማጤን ሌላኛው መንገድ ነው ። እራሱን ፈልጎ ፣ ህልሙን ለይቶ ፣ በእርሱ ውስጥ ተረጋጋጎቶ እራሱንና ከባቢውን እየቀየር ያለን ሰው የሚሰማው ስሜት ከአምላኩ ፣ ከፈጣሪው የሚታደለው እንጂ ምንም ምድራዊ ቁስ የሚሰጠው ስሜት የለም ።

አዎ! በህይወት ዘመናችን ብዙ ስህተት ልንሰራ እንችላለን ፣ ባልተገባ መንገድም ተጉዘን ይሆናል ፣ የማይጠበቅብንን ተግባርም ፈፅመን ይሆናል ፣ በዚህም ልናፍር ፣ ልንሸማቀቅና ልናዝን እንችላለን ። ከብዙ ድካም ፣ ከረጅምህ የእራስን ፍለጋ ጉዞ ፣ ከአድከሚው ሙከራ ቦሃላ ላገኘነው ህልምና የህይወት አላማችን ግን መደሰት ቢገባን እንጂ በፍፁም ልንሸማቀቅና ልናፍር አይገባም ። ህልምህ አለምአቀፍ ፊልም ላይ መተውን ከሆነ የዛሬ ደረጃህን አይተህ ስታስበው ልትሸማቀቅ አይገባም ፤ የህይወት አላማህ አለማቀፍ ደራሲ በመሆን ሰዎች ላይ በአዎንታዊነት ተፅዕኖ መፍጠር ከሆነ አሁን ብዙ ሰዎች በማያዩት ፣ ያነበቡትም የበዛ አስተያየት በሚሰጡህ ፅሁፍ ሃፍረት አይሰማህ ። ራዕይህ ፖሮፌሽናል እግርኳስ ተጫዋች መሆኑን ስትናገር በዛሬው አቋምህና ተክለሰውነትህ ምክንያት እንደዛ መሆን እንደማትችል ቢነገርህ አትገረም ፤ አትሸማቀቅ ። ማሳካት የምትፈልገውን አላማ ለማሳካት በምትጓዘው መንገድ ውስጥ ፣ በሂደቱ መሃል የሚሰማህን ስሜት በደስታና በፍቅር ካጣጣምከው ከዚህ በላይ ልዩ የአምላክ ስጦታ እንደሌለህ እውቅ ። ህልመኛ በመሆንህ ኩራ ፤ የአምላክህን ውድ ስጦታ ስላገኘህ በእጅጉ ደስ ይበልህ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.2K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 14:38:14 የት ናቸው?
እንዲረዱህ ፣ እንዲገነዘቡህ የምትጠብቃቸው ሰዎች የት ናቸው ? እንደሚያበድሩህ የተማመንክባቸው ሰዎች የት ናቸው ? ህይወትህን እንደሚቀይሩልህ ተስፋ ያደረክባቸው ሰዎች የት ናቸው ? ብትወድቅ እንደሚያነሱህ ፣ ብትቸገር እንደሚያግዙህ ፣ ብታጣ እንደሚሰጡህ ፣ ብትታረዝ እንደሚያለብሱህ በልበሙሉነት ስታወራላቸው የነበርክላቸው ሰዎች የት አሉ ? በእርግጥም ስትፈልጋቸው የት ገቡ ? ከምርም ሲያስፈልጉህ ወዴት ተሸሸጉ ? አንድ ሰሞን ከአምላክህ በላይ በእነርሱ ተማምነህ ነበር ፤ የሆነ ጊዜ ከእራስህ በተሻለ እነርሱን ጠብቀህ ነበር ። ምንም ነገር ልታይባቸው ትችላለህ ፣ ምንም ሊያሳዩህ ይችላል የመታለሉ ፋንታ ግን ያንተ ጉዳይ ነው ፤ በእነርሱ ንግግር የመበላትህ ታሪክ ግን ያንተ ሃላፊነት ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! የት ናቸው ? እንደዛ የከነፍክላቸው ፣ ልበህ እስኪጠፋ የምትሟገትላቸው ፣ መቼም እንደማይተውህ የመሰከርክላቸው ሰዎች የት ናቸው ? በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን ጠንቅቆ የማወቅ ሃላፊነቱ ያንተ ጉዳይ ነው ። ምናልባትም አውቀህ ባትጨርሳቸው እንኳን እራስህን ለመጠብ የሚያስችልህ እውቀት ያስፈልግሃል ። ወዳጅ የነበረው ሰው መቼ ጠላትህ እንደሚሆን አታውቅም ፤ አብሮአደግህ የነበረ ሰው መቼ አታሎህ እንደሚጠፋ አታውቅም ። እንደሚወድህ ፣ እንደሚያስብልህና እንደሚያከብርህ እየነገረህ ከጎን የውድቀትህን ሴራ የሚተበትብብህ ሰው አለ ። ያንተ ለውጥና እድገት ባይጎዳውም እለት እለት ከእርሱ በታች እንደትሆን ይመኛል ። አንተ ግን በእርሱ በኩል እንደሚያልፍልህ ታልማለህ ። ማንም ላንተ እድገትና ለውጥ ግድ እንደማይሰጠው ብታውቅ ምን ይሰማህ ነበር? የተማመንከውም ሆነ የተደገፍከው ሰው ምንም ያክል ቢያስብልህና ቢያዝንልህ አንተ ለእራስህ የምታዝነውን ያክል የሚያዝንልህ ይመስልሃልን ?

አዎ! መዳረሻ የሌላቸው ሰዎች ላይ እምነትህን አትጣል ፤ ደግፈው ወደ አፋፍ የሚወስዱህን ሰዎች አትጠጋ ፤ አንተን ረግጠው ከፍ ለማለት ከሚተጉ ፣ ያንተ በእነርሱ መተማመን ምንም ከማይመስላቸው ሰዎች ጋር ህብረት አትፍጠር ። አዝነህ ፣ ተሰብረህ ፣ አንገትህን ደፍተህ በነበርክበት ሰዓት ከጎንህ ያልነበሩ ወዳጆች መቼም እንደማይጠቅሙህ እወቅ ። ማንን ማመን እንዳለብህ ለማወቅ የክፉ ጊዜ ወዳጆችህን ብቻ ለይተህ እወቅ ። በእራሱ ህይወት ሰዎች የእርሱን ድርሰት እንዲፅፉለት ፣ የእርሱን ድርሻ እንዲጫወቱለት ፣ ገፀባህሪውን እንዲተውኑለት ፣ ህልሙን እንዲኖሩለት ፣ አላማውን እንዲያሳኩለት የሚጠብቅ ሰው ባለበት ከመቅረቱ በላይ ደጋግሞ በሰዎች መሰበሩ ያሳዝናል ። ማመን ካለብህ በቅድሚያ ፈጣሪህን እመን ፤ መጠበቅ ካለብህ የእራስህን ድርሻ እየተወጣህ አምላክህን ጠብቅ ፤ በመቀጠል በእራስህ እመን ፤ የእራስህን የስራ ውጤቶች ጠብቅ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 17:22:41 ምርጥ ጽሑፎች pinned «ኢንተርኔት በመጠቀም በቀን 5 ደቂቃ ብቻ በመስራት ከ9000 ብር እስከ 100,000 ብር ገቢ ማግኘት የሚችሉበት ቀላል ስራ ለኢትዮጵያውያን 100% አስተማማኝ !!! ስራው CMV ይባላል ። የሚያስፈልጉን ነገሮች 1. የ ኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር 2. የቀበሌ መታወቅያ ወይም ፓስፖርት 3. email 4. Whatsapp ቅደም ተከተል 1. ቀጥሎ ያለው ሊንክ በመጫን ወደ CMV ዌብሳይቱ መግባት። ht…»
14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 17:21:29 አዕምሮህን አሰልጥን!

አነቃቂ ንግግር ባትሰማ፣ አነቃቂ ፅሁፍ ባታነብ፣ አይዞህ በርታ የሚልህ ሰው ባታገኝ፣ ከጎንህ የሚቆም አጋዥ ባታገኝ ህይወትህን ሙሉ በሙሉ በእራስህ አነቃቂነትና በችግሮችህ አስገዳጅነት የምትቀይረው ይመስልሃል? ሁሌም ንቁ አትሆንም፤ ሁሌም ዝግጁ አትሆንም። ነገር ግን ከምንም በላይ ንቁና ዝግጁ የሚያደርግህን ተግባር በመፈፀም ንቃትን መላበስና ዝግጁ መሆን ትችላለህ። ያለህበት የገንዘብ እጦት የሚጠበቅብህን ሁሉ እንድታደርግ ካላነሳሳህ አንድ አነቃቂ ንግግር ወይም ፅሁፍ ሊያነቃና ሊያነሳሳህ አይችልም። አንተ ካለህበት ሁኔታ በተሻለ ጠንካራ ሰው እንድትሆን የሚያደርግህ ነገር የለም። የህመምህን ስሜት ታውቀዋለህ፤ የማጣት ስቃይ ደርሶብሃል፤ የመናቅ፣ የመገፋት ሃፍረት አጋጥሞሃል። በሌለህ ነገር መለካት ምንያክል እንደሚያም ታውቀዋለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! አዕምሮህን አሰልጥን! እራስህ ላይ ሰልጥን፤ ማንነትህ ላይ ንገስ። ማድረግ ያለብህን ለማድረግ፣ መገኘት የሚገባህ ቦታ ለመገኘት ቆራጥ ሁን። ማመንታት የስኬትህ ጠላት ነው። መወሰን ባለብህ ነገር ላይ በፍጥነት ወስን። ህልምህን ለመኖር ብዙ ያልተሟሉ ነገሮች ይኖራሉ፤ ነገር ግን አዕምሮህን ካሰለጠንክ፣ ማንነትህን ከህልምህ ጋር ካዋሃድክ፣ በአዎንታዊ አመለካከት ከተሞላህ ባለህ ነገር ህልምህን መኖር ትችላለህ። ስልጡን አዕምሮ አነቃቂ (motivation) አይጠብቅም፤ ህልመኛ ማንነት ሰበብ (excuse) አያበዛም፤ አዎንታዊ ስብዕና የአላማውን መሰናክሎች (obstacles) አይቆጥርም። ወደፊት የምትሔደው ሲመችህና የሚገፋህ ስታገኝ ብቻ አይደለም፤ ጉዞህን የምትቀጥለው አበረታች ድጋፍ ስታገኝ ብቻ አይደለም።

አዎ! ማድረግ ላለብህ ነገር የሚያስፈልግህ ምክንያት ሳይሆን ምግባር ነው። እያስጠላህ ጠንክሮ የመስራት ምግባር፤ እየታመምክ እስከጥግ የመታገል ምግባር፤ በማጣት ውስጥ የመፍጨርጨር ምግባር፣ እየተገፉ፣ እየተጠሉ፣ እየተሰደቡና እየተተቹ ህልምን የመኖር ምግባር። ማንም ቢሆን ሰው የሚያወጣው አዕምሮው ውስጥ ያለውን ሃሳብ እንጂ አንተን የሚገልፀውን ነገር  አይደለም። እንደምታስጠላ ሲናገር እራሱን እየሰደበ እንደሆነ አይረዳም፤ አትችልም ሲልህ ለእራሱ እንደማይችል እያረጋጋጠ መሆኑ አይገባውም። የምትባለውን እንዳልሆንክ አምነህ ለእራስህ በሰጠሀው ልክ መጓዝም እራሱን የቻለ አንድ ትልቅ ምግባር ነው። በህልሙ ጉዳይ ከማንም የማይደራደር፣ ለራዕይው እውንነት ምንም ምክንያት የማያቀርብ፣ አላማውን ለማሳካት ማንንም የማይጠብቅ መሪ የሆነ ስልጡን አዕምሮ አለህ። በምንም ሁኔታ እንዲረበሽና በአሉታዊ አስተሳሰብ እንዲመረዝ አትፍቀድ። ስልጡኑን አዕምሮ ተጠቅመህ በምትፈልገው መንገድ፣ የምትፈልገውን ህይወት ኑር።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 14:57:45 ኢንተርኔት በመጠቀም በቀን 5 ደቂቃ ብቻ በመስራት ከ9000 ብር እስከ 100,000 ብር ገቢ ማግኘት የሚችሉበት ቀላል ስራ ለኢትዮጵያውያን 100% አስተማማኝ !!!
ስራው CMV ይባላል ።

የሚያስፈልጉን ነገሮች
1. የ ኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር
2. የቀበሌ መታወቅያ ወይም ፓስፖርት
3. email
4. Whatsapp

ቅደም ተከተል
1. ቀጥሎ ያለው ሊንክ በመጫን ወደ CMV ዌብሳይቱ መግባት።

https://coinmv.com/#/reg?code=GBUAKJ

2. በሚመጣልን ፎርም አዲስ አካውንት ለመክፈት ስልክ ቁጥራችን ከ+251 ቀጥለን 0 ትተን 9 ብለን በመጀመር እናስገባለን (ለምሳሌ951128380 ) ። password ና email በማስገባት አካውንት እንፈጥራለን።

3. አካውንት ከፈጠርን በኋላ ወደ አካውንታችን ለመግባት Whatsapp / phone number በሚለው 0 በመተው 9 ብለን በመጀመር ስልክ ቁጥራችን (ለምሳሌ 951128380) እና password በመፃፍ እንገባለን ።

4. ከገባን በኋላ ማንነታችን ማረጋገጥ አስፈላጊ ስለሆነ ከታች Mine በሚለው ገብተን በመቀጠል ከላይ በቀኝ በኩል ያለውን የ >  ምልክት በመጫን የሚመጣልን ፎርም ሙሉ ስማችን ፣ የመታወቅያ ወይም ፓስፖርት ቁጥር ፣ መታወቅያችን ወይም ፓስፖርታችን ከፊትና ከጀርባ ፎቶ ኣንስተን Upload እናረጋለን ። ከተወሰነ ደቂቃ Approve እንደረጋለን ።

5. ስራ ለመጀመር USDT እንገዛለን ። Home >> c2c transaction በሚለው ገብተን ከላይ  Buy የሚለውን ስንጫን USDT የሚሸጡ ብዙ ሰዎች ዝርዝር ያመጣልናል ። ከነዚህ ኣንዱን መርጠን Buy እንላለን (ለምሳሌ Efrem Tsehaye ) ። የሚሸጠውን ሰው ስልክና የባንክ ሂሳብ ያመጣልናል ።
የምንገዛው መጠን 75 ከሆነ በወር 9,000 ብር ገቢ እናገኛለን
የምንገዛው መጠን 175 ከሆነ በወር 21,000 ብር ገቢ እናገኛለን
የምንገዛው መጠን 350 ከሆነ በወር 37,000 ብር ገቢ እናገኛለን
ለምንገዛው ሰው በስልክ ደውለን በማነጋገር በ 15 ደቂቃ ገቢ በማድረግ I have paid የሚለውን ተጭነን የገዛነውን ሰው Approve ያረግልናል ።

6. ሂሳባችን ከ75 በላይ ሲሆን ስራ እንጀምራለን ።

7. ስራው click ማድረግ ብቻ ነው ። ከታች ያለውን ሜኑ Robot በሚለው በመጫን የ 75 ፣ የ175 ወይ የ 350 እንመርጣለን ። ከዛ ወደ Whatsapp ግሩፕ ያስገባናል ። ከዛ በየቀኑ 10 ሊንክ ያመጣልናል ። አስሩን ሊንክ በየቀኑ ክሊክ እያረግን የምንሸጠው USDT እናገኛለን ።

8. ክፍያችን / ገንዘባችን ለማግኘት c2c transaction በመጫን Sell በሚለው ገብተን ለፈለግነው ሰው መርጠን በሚመጣልን ፎርም የባንክ ሂሳብ ቁጥር ፣ የባንክ ስምና የራሳችን ስም በመፃፍ  Sell ብለን ገንዘቡ ገቢ ሲደረግልን Approve እናረጋለን ። ለመሸጥ የሚመረጥ ቀን አርብ / Friday ነው ። ምክንያቱም በሌላ ቀን ከሆነ 10% ተቆራጭ ይሆናል ። በተጨማሪም ከዌብሳይቱ App Download በማድረግም መጠቀም ይችላሉ ።


ለተጨማሪ መረጃ በስልካችን ይደውሉ

+251942740568
+251942740568
+251942740568

እናዳያመልጥዎ ሊንኩን በመጫን ኣሁኑኑ ስራ ይጀምሩ።

https://coinmv.com/#/reg?code=GBUAKJ
2.3K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ