Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ መልካም ይሆናል! እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እነሆ ዛሬ መልካም ቀንን ለማየት በቃን። | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ዛሬ መልካም ይሆናል!

እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እነሆ ዛሬ መልካም ቀንን ለማየት በቃን። ያለፈው እንዳለፈ ሆኖ፣ የቀረውም ቀርቶ፣ የመጣውም መጥቶ ለዚህ በቅተናል። ማግኘት የሚገባንን አግኝተናል፤ የሚገባን ስፍራ ተገኝተናል፤ የማይታለፉ የሚመስሉ ጊዜያት አልፈው ታሪክ ሆነዋል፤ እንደ አምላክ ፍቃድ በሰላም በጤና ልናመሰግነው በቅተናል። የሆነው ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ የሚነጋው የሚመሸው፣ የምናርፈው የምንነቃው ዳግም የምንታደሰው እንደ እርሱ መልካም ፍቃድ ነው። ያኔ ብቻህን ስትሆ ውስጥህ ምን ይልህ ነበር? ያኔ አጣብቂኝ ውስጥ ሆነህ ምን ይሰማህ ነበር? ያኔ ተስፋህ ከጫፍ ሲደረስ ምን ታስብ ነበር? ዛሬ ከባዶቹ ጊዜያት አልፈዋል፤ ዛሬ መጥፎዎቹ ቀናት ታልፈዋል፤ ዛሬ አስጨናቂዎቹ ወቅቶች ታሪክ ለመሆን በቅተዋል።

አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬ መልካም ይሆናል! ዛሬ እፁብ ድንቅ አስደሳች ቀን ይሆናል። መልካም ይሆን ዘንድም ያንተ ስራ በአምላክህ ፍፁም እንከን አልባ ተግባር መተማመን ነው፤ ሁሉን ለእርሱ መተው ነው፤ ተስፋህን በማይናወጠው ክንዱ ላይ ማድረግ ነው። በእግዚአብሔር የሚታመኑ፣ በአምላካቸው የሚተማመኑ፣ ፈጣሪያቸውን የሚደገፉ ነፍሳት ብፁዓን ናቸው። መከራ አያገኛቸውም፤ ስቃይ አይቀርባቸውም፤ ተስፋ መቁረጥ አይጠጋቸውም። ምክንያቱም የሚሆነው ሁሉ በእርሱ ፍቃድ እንደሚሆን ያውቃሉና ነው፤ ምክንያቱም እየሆነ ያለውም በእርሱ ይሁንታ መሆኑን ስለሚረዱ ነው፤ ምክንያቱም ትንሹንም ትልቁንም ተግባር ከመፈፀማቸው በፊት ከአምላካቸው  ስለሚማከሩ ነው። የቀንህ መልካምነት፣ የውሎህ ስኬታማነትና አስደሳችነት ካሳሰበህ ከምንም በፊት እጆችህን ለዚች ውብ ንጋት ብለህ ለምስጋና ዘርጋ፤ ስላለህና ስለሌለህ ነገር ሁሉ ለአምላክህ የሚገባውን ስጠው።

አዎ! "ከእኛ የሆነ አንዳች የለም ሁሉም ከእርሱ ነው።" እንደሚል ቃሉ፣ ነገሮች ሲሆኑ ለመልካም፣ ሳይሆኑም ሲቀሩ ለመልካም፣ ለበጎ እንደሆነ ማሰብ ተገቢ ነው። አሸናፊነት ቀንን በንጋት ከማሸነፍ ይጀምራል፤ ስኬት የአምላክን መልካም ፍቃድ በበጎ ከመረዳት ይነሳል። ሮጠህ ሮጠህ አንድ ቀን ትደክማለህ፤ ለፍተህ ለፍተህ አንድ ቀን ትዝላለህ፤ ውስጥህ ያለው የህያው አምላክ መንፈስ ግን መቼም አይደክምም፤ መቼም አይዝልም። ገና ሳትኖር "ህይወት በቃኝ፣ ከበደኝ፣ ደከመኝ፣ አሰቃየኝ" አትበል። ድካምህ ምን ይዞልህ እንደሚመጣ አታውቅም፤ ስቃይህ ልምን እንደሚያበቃህ አታውቅም። አምላክህ ስራውን ሰርቶ እስኪጨርስ ጊዜ ስጠው፤ ከዛ ቦሃላ ሁሉም ውብና እጅግ ያማር መልካም እንደሚሆን ትመለከታለህ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q