Get Mystery Box with random crypto!

በሆኑ ሰዎች ትወገዛለህ! ማንም ሁን ፣ ምንም አድርግ ፣ እንዴትም አድርግ ፣ እንደምንም ተገኝ ፣ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

በሆኑ ሰዎች ትወገዛለህ!
ማንም ሁን ፣ ምንም አድርግ ፣ እንዴትም አድርግ ፣ እንደምንም ተገኝ ፣ የቱንም ድንቅ ተዓምር ነገር ስራ ብቻ የሆኑ ሰዎች ይጠሉሃል ፤ በሆኑ ሰዎች ትወገዛለህ ፣ በሆነ ማህበረሰብ ዘንድ እንድ መጥፎ ትታያለህ ፤ በሆነ ቡደን ጥፋተኛ ትደረጋለህ ። በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ አንደኛው የህይወት እውነታ ነው ፤ በማንነትህ የሚገጥምህ ነገር ነው ። እንዲሁ ሳያውቁህ አይተው የሚጠሉህ ሰዎች አሉ ፤ እንዲሁ ከባዶ "ቀልቤ አልወደደውም" የሚሉህ ሰዎች አሉ ። ለመጥላታቸው ምክንያት ቢጠየቁ ግን "ይህን አድርጎኛል ፣ በዚህ መልኩ በድሎኛል" የሚሉት ምክንያት እንኳን የላቸውም ። እንዲሁ ስሜታቸው ስላልወደደህ ብቻ አትመቻቸውም ፣ ሲያዩህ ይጎረብጣቸዋል ፤ ድምፅህን ሲሰሙ ይነዝራቸዋለ ፤ ስላንተ ሲያወሩ ይጠየፉሃል ፤ መጥፎ ቃላት ይመርጡልሃል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ይህ ህይወት ነው! በሆኑ ሰዎች ትወገዛለህና ምንም ማድረግ አይቻልም ። የሚጠሉህ ሰዎች ምክንያት ቢኖራቸው መልካም ነበር ፣ ያደረካቸው ነገር ቢኖር ጥሩ ነበር ። ነገር ግን ምንም በሌለበት ፣ ይባስ ብሎ ማንነትህን ፣ ስራህን እንኳን በቅጡ ሳያውቁት ስላንተ ክፉ ያወራሉ ፣ ያሙሃል ፣ ያንቋሽሹሃል ፣ ይተቹሃል ፣ ይንቁሃል ። አንተ ወደላይ እየገሰገስክ ነው ፣ እነርሱ ግን በሃሳባቸው ሊያወርዱህ ይታገሉሃል ፤ አንት ህልምህን በሙላት እየኖርክ ነው ፣ እነርሱ ግን ዘወትር ቡና መጠጫ ያደርጉሃል ፤ አንተ የሚያዋጣህን ይዘህ ደስተኛ ሆነሃል እነርሱ ግን ባንተ ምክንያት ቀናቸውን ያበላሻሉ ። የህይወትን ሚዛን መጠበቅ ከፈለክ ሁሉንም እንዳመጣጡ የማስተናገድ ግዴታ አለብህ ። እንዲሁ አይቶ የሚወደህ ሰው እንደመኖሩ እንዲሁ በባዶ የሚጠላህና እንከን የሚያወጣልህም እንዳለ መቀበል ይጠበቅብሃል ። አንዳንዴ ተቃዋሚዎችህ ምክንያት እንደሌላቸው አውቀህ ችላ ልትላቸው ይገባል ።

አዎ! ለሁሉ መልስ እየሰጠህ ፣ ሁሉንም እያስረዳህ ፣ ከሁሉም ጋር ለመስማማት እየጣርክ የተረጋጋ ህይወት ለመኖር አትሞክር ። ያለምክንያት የሚጠላህን ሰው ልታደርግለት የምትችለው ብቸኛ ነገር እንዲያውቅህ እንድሉን ማመቻቸት ብቻ ነው ። አንተ በደስታ እየኖርክ ፣ ውስጥህ ሰላም ሆኖ ፣ እራስህን እየቀየርክ ፣ ለእራስህ ቦታ እየሰጠህ ፣ ከአምላክህ ጋር በፍቅር እየኖርክ ማንም እንዲ ነህ ፤ እንደዛ ነህ ቢልህ ምን የሚቀንስብህ ነገር አለ ? ፈጣሪህን አታሳዝን ፣ ህይወትህን አታበላሽ ፣ ሰዎችን አትጉዳ እንጂ በፈለከው መንገድ እራስህን መሆንህ ከማን ምንን ያጎድላል ? ከማን በታችስ ያደርግሃል ? በአንዳንድ ሰዎች ያለምክንያት መጠላትህ ፣ በተወሰኑ ሰዎች መገፋትህ ፣ ዋጋህን ማጣትህ ምንም ማለት እንዳልሆነ እወቅ ። ተፈጥሮን መቃረን ከማትችልባቸው ነገሮች አንዱ ያለምክንያት የሚጠሉህ ሰዎች መኖራቸው እንደሆነም ተረዳ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q