Get Mystery Box with random crypto!

አይንህን ግለጥ! ወደኋላ ዞረህ እራስህን ስትመለከት ምን ይታይሃል? ብዙ ርቀት ወደፊት ተጉዘሃል | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

አይንህን ግለጥ!

ወደኋላ ዞረህ እራስህን ስትመለከት ምን ይታይሃል? ብዙ ርቀት ወደፊት ተጉዘሃል ወይስ እዛው አካባቢ በቅርብ ርቀት ነህ? ሃሳቦችህን በሚገባ አሳክተሃል ወይስ ከነጭራሹ ትተሃቸዋል? አምስት አመታትን ወደኋላ ስትቆጥር የነበሩ ችግሮችህ ዛሬም አሉ ይሆን? ያኔ ሲያስጨንቁህ የነበሩ ጉዳዮችስ ከምን ደረሱ? በጊዜ ፍጥነት ነገሮች በቶሉ ይቀያየራሉ። የሆነ ጊዜ እራስን ማወቅ፤ እራስ ላይ መስራት፣ እራስን ማዳን፤ ከእራስ በላይ ለሰዎች መኖር የሚባለውን ነገር አናውቀውም ነበር። ዛሬ ግን ህይወት በእራሷ በተግባር እያስተማረችን ነው። ዝም ብሎ በዘፈቀድ መኖር፣ ያለምንም እቅድና አላማ ምድር ላይ መመላለስ ህይወትን የባሰ ከባድና ውስብስብ እንደሚያደረግው እራሷ ህይወት በሚገባ አስረድታናለች።

አዎ! ጀግናዬ..! አይንህን ግለጥ፤ በአፅንዖት መመልከት ጀምር፤ እራስህን በሚገባ መርምር። ከአመታት በፊት የነበርክበት ስፍራ ነህ ወይስ እየተጓዝክ ነው? ዛሬም ባለፉት አመታት ችግሮችህ ተከበሃል ወይስ ከእንቅስቃሴህ ጋር ከተቀየሩ አዳዲስ ችግሮችህ ጋር ነህ? የት ነበርክ? የትስ አለህ? ምን ይዘሃል? ከምንስ ደርሰሃል? እድሜ እስከጨመረ ድረስ የፊት ገፅታ፣ የሰውነት አቋምና ድምፅ መቀየሩ አይቀርም። ዋናው ቁብነገር ግን እርሱ አይደለም። በግል ስብዕና፣ በአመለካከት፣ በአስተሳሰብ ልኬት፣ በማስተዋል ችሎታ እራስህ ላይ የተመለከትከው ለውጥና እድገት ምንድነው? ምናልባት በቻልከው መጠን ትጥር ይሆናል፤ ብዙ ስራ እየሰራህ፣ ብዙ ወዳጆችህን አፍርተህም ይሆናል። ሂደቱ ካልሰራህ ግን እራስህ ቆም ብለህ ማሰብ ይጠበቅብሃል።

አዎ! ምንም ቢሆን አንተን የማይቀይር፣ እሴት የማይጨምርብህ፣ ዋጋህን ከፍ የማያደርግ፣ ካለህበት ቦታ ፈቀቅ የማያደርግህ ጥረት ምንም ትርጉም የለውም። ከፍጥነቷ የተነሳ ህይወትን ትናንት ብለን ዛሬ ለማለት ጊዜ ልናጣ እንችላለን፤ ያለምንም ቁብነገርና አለማ የሚደረግ ሩጫ ደግሞ ጠዓም እያሳጣት በብዙ እጥፍ ያሳጥራታል። የመኖርህን ትርጉም ለመረዳት ጊዜ አታጥፋ፤ አይንህን በቶሎ ግለጥ፤ እርሱን ለማወቅ ማድረግ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ። በዚህ ጉዳይ ቀጠሮ ሰጠህ ማለት ህይወትህን ሙሉ፣ ትርፋማ፣ አስደሳችና በእግዚአብሔር የተወደደ ለማድረግ እያቅማማህ እንደሆነ እወቅ። ህይወትህን መቀየር እንደምትችል፣ የተሻለ ስፍራ ማድረስ እንደምትችል ማወቅህ ብቻ በቂ አይደለምና ውስጥህ የሚመላለሰውን ግሩም ሃሳብ በመተግበር በመግለፅ እውቀትህን ተግባራዊ አድርገው።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q