Get Mystery Box with random crypto!

በጥልቀት ቆፍር! 'አሸናፊዎች እስኬት ይጓዛሉ?' ብለህ ብትጠይቅ 'እስከ አሸናፊነታቸው' ትባላለህ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

በጥልቀት ቆፍር!

"አሸናፊዎች እስኬት ይጓዛሉ?" ብለህ ብትጠይቅ "እስከ አሸናፊነታቸው" ትባላለህ፤ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መዳረሻቸው የት ነው?" ብትል "በገነቡት ማንነት ተፅዕኖ መፍጠር የጀመሩበት ቦታ" ትባላለህ፤ "መሪዎች መጨረሻቸው የት ነው?" ብትል "የሚመሩትን አካል መርተው የሚያደርሱበት ከፍታ" ትባላለህ፤ "ጠንካራ ተማሪዎች እስኬት ይማራሉ?" ብለህ ብትጠይቅ "የሚያኮራቸው የእውቀት ደረጃ እስኪደርሱ" ትባላለህ። ያንተስ ጉዞ እስኬት ነው? ለምን ጀመርክ? ለምንስ በዚህ ልክ ትፋለማለህ? ለምን በዚህ ልክ ዋጋ ትከፍላለህ? ውስጥህ እንዳታቆም እየገፋህ፣ ደጋግሞ እየታገለህ፣ እንቅልፍ እየነሳህ፣ ዋጋ እያስከፈለህ ከሆነ በእርግጥም ብርቱ የማይበገር ሃይል አግኝተሃል፤ ፅኑ የማይናወፅ ድጋፍ ተሰጥቶሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ውስጣዊ ድጋፍ ካለህ፣ ስሜት የሚሰጥህን ተግባር ከጀመርክ፣ የምታገኘው ገቢ ካላሳሰበህ፣ ተቀባይነት ማግኘትህ ካላስጨነቀህ ያለምን ፍረሃት፣ ያለምንም መሳቀቅና ድካም በጥልቀት አርቀህ ቆፍር፤ እስከጥግ ተፋለም፤ እስከመጨረሻው ታገል። ተስፋ መቁረጥ፣ ወደኋላ መመልከት፣ በታሪክ መታሰር፣ በቀድሞ ማንነት መታቀብ የሚባሉ ነገሮችን እርሳቸው። ድሮ በዚህ ማንነት ላትታወቅ ትችላለህ፣ አሁን ግን መታወቅ ትጀምራለህ፤ ቀድሞ ለፍረሃት እንደ ምሳሌ ልትታይ ትችላለህ፣ ዛሬ ግን በድፍረትህ እስከመወደስ ትደርሳለህ፤ በፊት በተጠራህበት ቦታ ሁሉ ትገኝ ይሆናል፣ አሁን ግን ውድነትህ ለብዙዎች እየገባቸው ይመጣል። ዋጋ መክፈል ካለብህ ከላይ ከላይ፣ ለነገሩ፣ እንዳይቀር የሚባል ነገር የለም። በጅማሬህ ከተማመንክ ጉዞህ እስከ ፍፃሜው ነው፤ በሃሳብህ ትልቅነት ጥርጣሬ ከሌለህ ተግባርህ ጥም ቆራጭ፣ አንጀት አርስ መሆን ይኖርበታል።

አዎ! ትልቅ ህልም ኖሮት የሚተኛ ሰው የለም፤ ከእራሱ በላይ ለሰዎች መኖርን ግቡ አድርጎ በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጥ አይኖርም፤ የተፈጠረለት አላማ ኖሮ መሞት ብቻ እንዳልሆነ የተገነዘበ ሰው በፍፁም አላማውን ሳይኖር ማለፍ አይችልም። እውቀቱ ወደ ተግባር ይገፋዋል፤ ተነሳሽነቱ ለአላማው ያቀርበዋል፤ እያንዳንዱን ቀኑን በሙላት እንዲኖር ያደርገዋል። የውልደትህ ምክንያት ታላቅነት እንደሆነ አስታውስ፤ ወደ ምድር የመጣሀው ለእራስህ ብቻ ኖረህ ለማለፍ እንዳልሆነ አስታውስ፤ በህይወት መኖርህ ሸክም ሳይሆን በረከት እንደሆነ እወቅ። እግዚአብሔር ዋጋ ያለው የተለየ ድንቅ የሰው ልጅ አድርጎ ፈጥሮሃል፤ አምላክህ በሚያምር ማንነት፣ በሚገርም ክብር፣ እጅግ በሚወደድ ጥበብ አበጅቶሃል። ክብርህን ማስጠበቅ፤ ለላቀ ደረጃ መብቃት ያንተ ድርሻ ነው። በጥልቀት መቆፈርህን እንዳታቆም፤ እራስህን ከመፈለግ እንዳትገታ፤ በምክንያት ተፈጥረሃልና ለምክንያትህ፣ ለህይወት አላማህ እስከመጨረሻው ተፋለም።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q