Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.29K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-26 15:12:31
በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰጠት የተጀመረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የጠዋቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡

በጠዋቱ መርሃ ግብር የእንግሊዝኛ ፈተና የተሰጠ ሲሆን ከሰዓት (ከ9፡00-12፡00) የሒሳብ ትምህርት ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

ምስል፦ አምቦ ዩኒቨርሲቲ 

@tikvah_education
14.6K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 12:27:28 የሁለተኛ ደረጃ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚችሉ ተገለፀ፡፡

የሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበን ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ሚያዝያ 17/2015 ዓ.ም አጽድቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸው እና የሁለተኛ ደረጃ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ እንደሚችል በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) በመድረኩ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ የመከላከያ ሠራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል አባላት የሚሆኑ ከሆነ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠበቁላቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የሕ/ተ/ም/ቤት

@minster_of_education
2.7K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:41:07
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችሉትን ዝግጅቶች ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው "ራስ ገዝ" ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ገልጸዋል፡፡

በዚህም የፋይናንስና የሰው ኃይል አደረጃጀት መመሪያ ተዘጋጀቶ ከሰራተኞች ጋር ውይይት መደረጉንና መመሪያው በቀጣይ ለቦርድ ውሳኔ የሚቀርብ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ለኢዜአ ተናግረዋል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውይይት እየተደረገበት ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የአዋጁን መጽደቅ እየጠበቀ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች “ራስ ገዝ” መሆን የአካዳሚ፣ የአስተዳደር፣ የፋይናንስ እና የሰው ኃብት አስተዳደራቸው ላይ ነጻነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በትምህርት ሚኒስቴር ተገልጿል።

በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የምርምር ተልዕኮ የተሰጣቸውና የመጀመሪያው ትውልድ ተብለው የተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝ" እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

@Minster_of_education
651 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:40:50
"በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ ይጀመራል።"

የትምህርት ሚ/ር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በአገር አቀፍ ደረጃ ከ47 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አዲስ ወግ በተሰኘ የውይይት መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተገቢውን መስፈርት ባሟላ መልኩ የተገነቡ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።

በመሆኑም በአገር አቀፍ ደረጃ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ዘመቻ ለማከናወን ዕቅድ መዘጋጀቱን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ዘመቻው በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ አካባቢዎች የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት እንደሚሰራም ሚኒስትሩ መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል፡፡

@Minster_of_education
596 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:40:34
የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነዎት?

የተፈጥሮም ሆነ የማህበራዊ ሳይንስ፤ የመደበኛም ሆነ የተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር ተማሪዎች የሚወስዱትን የጄነራል ሳይኮሎጂ (General Psychology) ኮርስን በጥልቀትና በስፋት ለመረዳት እንዲችሉ ታስቦና ኢትዮጵያዊ አውድን የዋጁ ማሳያዎችን መሰረት አድርጎ በ Psych in Amharic የYouTube ቻናል ቀርቦልዎታል!

ኮርሱን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ16 ዓመታት በብቃት ያስተማሩት መምህር ታምሩ ደለለኝ ሳቢ በሆነ መልኩ  ያቀርቡታል!

ከዚህ በታች ያለውን የቻናሉን ማስፈንጠሪያ (link) በመጫን ሁሉንም ምዕራፎች ማግኘት ይችላሉ!

https://youtube.com/@psychinamharicwithtamirude674?feature=shares

Subscribe በማድረግ ራስዎን ለዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ ትምህርት ዝግጁና ውጤታማ ያድርጉ! ሳይኮሎጂን ይተዋወቁ!

Psych in Amharic with Tamiru Delelegn!
519 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:40:23
ወደፊት የሚቋቋሙ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ" የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የውይይት መድረክ የትምህርት ሚኒስትር
ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የማድረጉ ሂደት በተያዘው ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሮ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ በስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።

“መስፈርቱን አሟልተው የሚፈጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲኖሩ"፤ አዋጁ ወደፊት የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎችንም የሚመለከት መሆኑን ዶ/ር ሳሙኤል አስረድተዋል።

ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከፍለው የሚማሩ መሆን እንዳለባቸውም ዶ/ር ሳሙኤል አመልክተዋል።

“ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ አይመደብላቸውም” ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፤ ፍትሃዊነትን ለማምጣት ሙሉ እና ከፊል-ነጻ የትምህርት ዕድል ለተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

ረቂቁ “ጠንካራ የፋይናንስ አቅም እና አካዳሚያዊ ተወዳዳሪነት” ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ከሚያበቁ መስፈርቶች መካከል እንደሚካተቱ ይጠቅሳል።

ለዚህም “ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኳቸው ውጤታማ ለመሆን ሀብት ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው።

ሀብት ለማመንጨት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎቹ “የንግድ ድርጅት ሲያቋቁሙ፤ ሌላ ነጋዴ መስራት የሚችለውን ሳይሆን ከተልዕኳቸው ጋር የሚመጋገብ” መሆን እንዳለበት ዶ/ር ሳሙኤል አስረድተዋል፡፡

@Minster_of_education
479 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:40:05
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ የሰራተኞች የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ሠራተኞች በተቋሙ እንቅስቃሴ እና ቀጣይ ተግባራት ላይ ተወያይተዋል።

አክሱም፣ መቐለ፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።

@Minster_of_education
479 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:39:49
ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ፍቃድ ሊሰጥ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ፍቃድ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ባለሥልጣኑ ከህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት ማቆሙ ይታወቃል።

ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የተሻሻሉት መመሪያዎቹ ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ፈቃድ የነበራቸውን ጨምሮ ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ እንደ አዲስ ምዝገባ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ምዝገባው በዘንድሮ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን በ2016 ዓ.ም አዲስ ፍቃድና የእድሳት አገልግሎት መስጠት ሊጀመር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ 360 የሚጠጉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን መረጃ ያሳያል።

@Minster_of_education
566 views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 13:39:32
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 135 የገጠር መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች አስመርቋል፡፡

ከሲዳማ፣ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የተውጣጡት ሰልጣኞቹ ለ30 ቀናት የተሰጣቸውን ስልጠና ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

ሰልጣኞቹ በተለያዩ የገጠር አካባቢዎች ከሚታየው የሕዝብ ብዛት መጨመር ጋር ተያያዞ የሚከሰቱ የመሬት አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል የሚያስችል ስልጠና መውሰዳቸውን የኮሌጁ ዲን ሳሙኤል በቀለ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

@Minster_of_education
610 views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 07:23:01
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ፕሮግራሞች የሦሥተኛ ዲግሪ (PhD) ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው በ Accounting & Finance እና በ Management ፕሮግራሞች በተያዘው በጀት ዓመት ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በሦሥተኛ ዲግሪ (PhD) ትምህርት የሚሰጥባቸው ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች፦

• PhD in Accounting
• PhD in Finance
• PhD in Human Resource Management
• PhD in Marketing Management
• PhD in Business Leadership

@Minster_of_education
1.7K views04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ