Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-08 13:47:15
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል

LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው መማር ለሚቸገሩና የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን በነጻ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

ኮሌጁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መልዕክት በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጾ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም እንዳሉት ጠቅሷል።

ከዚህም በተጨማሪ መስፈርቱን አሟልተው ለሚመረጡ ተማሪዎች በነጻ ማስተማር ብቻ ሳይሆን የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን እንደሚሸፍን ገልጿል።

ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፦

1. መንግስት ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ያስቀመጠዉን የቴክኒክና ሙያ የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ፤

2. የኮሌጁን መግቢያ ፈተና  ማለፍ የሚችሉ፤

3. ከፍለው ለመማር  የማይችሉ ይኽንን የሚገልጽ ማስረጃ ከሚኖሩበት ቀበሌ ካመጡ ቅድሚያ ያገኛሉ።

የትምህርት መስኮች፦

#Electronics: Electrical Electronics equipment servicing management[ Level III & IV]

#IT : Hardware and network servicing [Level III & IV]

#የማመልከቻ_ጊዜ፡ ከየካቲት 24 - መጋቢት 22 ባሉት 21 ተከታታይ የስራ ቀናት

#አድራሻ: ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር ከጠዋቱ 2፡00 - 1፡00 ሰአት

#ስልክ:  011-6-67-75-64 / 011-6-66-18-29

@Minster_of_education
2.1K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 13:46:58
#AmboUniversity

በ2015 ዓ.ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 07 እና 08/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ አሳዉቋል።

የምዝገባ ቦታ፡-

የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ➧ በዋናው ግቢ

የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ➧ በሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ ከ8–12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ስምንት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Minster_of_education
1.8K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 13:46:46
#AksumUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቅርቧል።

ለሁለት ዓመት አካባቢ በቆየው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከባድ ውድመት እንደገጠመው ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል።

የአይሲቲ መሰረተ ልማት፣ የወርክሾፕ ማሽነሪዎች፣ የላቦራቶሪ ዕቃዎች፣ የግብርና መሰረተ ልማት፣ የዲጂታል ቤተ መጻሕፍት፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች እና ሌሎችም መዘረፋቸውን ወይም መውደማቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ለዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ ላለፉት ሃያ ወራት ደመወዝ ባለመክፈሉ የተቋሙ ሠራተኞች የስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ላይ እንደሚገኙም ተቋሙ ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው በሚያደርገው የዳግም ግንባታና ጥገና ሥራ፤ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉለት ጥሪ አቅርቧል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

+251910593109

E-mail: nega1221@gmail.com

@Minster_of_education
1.7K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 13:46:30
#AAU

የቻይና መንግሥት ለ116 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቻይና ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጥቷል።

ተማሪዎቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ እስከ ሦሥተኛ ዲግሪ እየተማሩ የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህም በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይንኛ ቋንቋ፣ ለ6 የሦሥተኛ ዲግሪ ተማሪዎች፣ ለ12 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች እንዲሁም ለአንድ ተማሪ የጥናትና ምርምር ነጻ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷል።

ነጻ የትምህር ዕድል የተሰጣቸው ተማሪዎች በትምህርታቸው እገዛ የሚያስፈልጋቸው እንደሆኑ የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ገልጸዋል፡፡

"የቻይና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ነጻ የትምህርት ዕድል" / China-Ethiopia Friendship Scholarship ከአምስት ዓመት በፊት የተጀመረ ሲሆን በትምህርታቸው ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል።

@Minster_of_education
1.7K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 13:46:12
#ተራዝሟል

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለመጋቢት 11 እና 12/2015 ዓ.ም አድርጎት የነበረውን ጥሪ ወደ መጋቢት 16 እና 17/2015 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Minster_of_education
2.0K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 00:35:51
ከኢትዮጵያ የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር አባል ናቸው?

እ.አ.አ. በ1967 የተቋቋመው የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር (AAU) በአህጉሪቱ ለሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድምጽ በመሆን እየሠራ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

የማኅበሩ የአስተዳደር ቦርድ የተለያዩ አገራት ዩኒቨርሲቲዎችን ማመልከቻ መርምሮ የአባልነት ሰርተፊኬት ይሰጣል።

የማህበሩ አባል መሆን ለዩኒቨርሲቲዎች በርካታ የምርምር፣ መማር ማስተማር እና የማማከር ጥቅሞችን ያስገኛል።

12 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር (AAU) አባል ናቸው። ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ የማህበሩ አባል የሆነ ብቸኛው የግል ዩኒቨርሲቲ ነው።

➧ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ፣
➧ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ እና
➧ ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ የማኅበሩ አባላት ናቸው።

መቀመጫውን አክራ፣ ጋና ያደረገው ተቋሙ፤ 433 ዩኒቨርሲቲዎችን ከመላው አፍሪካ በአባልነት ይዟል።

@Minster_of_education
1.9K views21:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 00:35:28
#AmharaEducationBureau

በ2014 ዓ.ም በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 294 ተማሪዎች የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

ሽልማቱ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ550 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 279 ተማሪዎች ፤ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ450 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 15 ተማሪዎች ተሰጥቷል።

ከተሸላሚዎቹ መካከል 70 ተማሪዎች 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ናቸው፡፡

በእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ርዕሰ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል።

@Minster_of_education
1.8K views21:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 00:35:13
#WallagaUniversity

በ2015 ዓ.ም በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል የትምህርት ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን መጋቢት 7 እና 8/ 2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በቅጣት ለመመዝገብ ➧ መጋቢት 11/2015 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣
➧ ማጣቀሻ መጻሕፍት።

@Minster_of_education
1.6K views21:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 00:35:01
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም በመደበኛው መርሐ ግብር 996 ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

አጠቃላይ ገለጻ ለተማሪዎቹ ከተሰጠ በኋላ መጋቢት 4/2015 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

@Minster_of_education
1.5K views21:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 00:34:47
#MaddaWalabuUniversity

በ2015 ዓ.ም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 7 እና 8/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➧ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣
➧ የኮቪድ-19 መከላከያ ማስክ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Minster_of_education
1.7K views21:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ