Get Mystery Box with random crypto!

Arba Minch University

የቴሌግራም ቻናል አርማ arbaminch_university — Arba Minch University A
የቴሌግራም ቻናል አርማ arbaminch_university — Arba Minch University
የሰርጥ አድራሻ: @arbaminch_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.05K
የሰርጥ መግለጫ

The official telegram channel of Arba Minch University

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 16:01:21
672 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:39:01
862 views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:39:01
859 views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:36:06 የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትና ም/ፕሬዝደንቶች የ2015 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ቁልፍ የውጤት አመላካች (KPI) ላይ የውል ስምምነት ተፈራረሙ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ቁልፍ የውጤት አመላካች (KPI) ላይ ነሐሴ 20/2014 ዓ/ም ከዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዝደንቶች ጋር የውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ ወቅት እንደተገለጸው የዩኒቨርሲቲው የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ የጸደቀ ሲሆን የም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤቶች የዕቅድ ቁልፍ ተግባራትም በዚሁ ዕቅድ ተመሥርተው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በቀጣይ ዕቅዱን እስከ ባለሙያዎች ድረስ በማውረድና ውል በመፈራረም እንደሚሠራና በግለሰብ ደረጃ የሥራ አፈፃፀም ምዝና ሲደረግም በዚሁ መሠረት ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶበታል፡፡

በፕሮግራሙ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት፣ ም/ፕሬዝደንቶች፣ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች፣ ዳይሬክተሮችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
845 views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:50:51
1.5K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:25:50
1.4K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:25:31 በሴፍጋርዲንግ ፖሊሲ/Safeguarding Policy/ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ

የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከክርስቲያን ኤይድ/Christian Aid/ ጋር በመተባበር ከተለያዩ ጥቃቶች ለመከላከልና የተሞከሩ ወይም የተፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስተካከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚያሳይ ፖሊሲ ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ዳይሬክተሮችና ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች ከነሐሴ 19-20/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ም/ፕሬዝደንት ተ/ፕሮፌሰር በኃይሉ መርደኪዮስ ዩኒቨርሲቲው ከክርስቲያን ኤይድ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር ከዚህ ቀደም የተለያዩ ሥራዎችን መሥራቱን አስታውሰው ሴፍጋርዲንግ ፖሊሲን አስመልክቶ የተሰጠው ሥልጠና ዩኒቨርሲቲው እንደ ተቋም ሁሉን ያማከለ ፖሊሲ ለመቅረጽ የሚያስችል ግንዛቤ ማስጨበጡን ገልጸዋል፡፡ ም/ፕሬዝደንቱ ሴፍጋርዲንግ ፖሊሲ ከተለያዩ የውጭ ሀገር ተቋማት ጋር ትብብሮችን ለመፈጸም ቀዳሚና ዋና መስፈርት በመሆኑ በትኩረት ይዘጋጃል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቶሌራ ሴዳ በበኩላቸው ሥልጠናው እየተሠሩ ያሉና ወደ ፊትም የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን ለማስተዳደር የሚያስችል ልምድ የተወሰደበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ቶሌራ ከሕግ አገልግሎት፣ ከሰው ሀብት አስተዳደር፣ ከሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች እንዲሁም ከምርምር ዘርፎች የተወጣጡ ሰባት አባላት ባሉት ኮሚቴ ፖሊሲው በአጭር ጊዜ ተዘጋጅቶና ተገምግሞ አገልግሎት ላይ እንዲውል ይደረጋል ብለዋል፡፡

የክርስቲያን ኤይድ ኢትዮጵያ አስተባባሪ አሠልጣኝ ፋንታሁን ዓለሙ እንደገለጹት ድርጅታቸው በእንሰትና በአነስተኛ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር እየሠሩ መሆኑን ገልጸው ድርጅታቸው አብሮ ከሚሠራባቸው ተቋማት ጋር በ‹‹Safeguarding Policy›› የመሥራት ግዴታ ስላለበት ሥልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ ድርጅታቸው ሴፍጋርዲንግ ፖሊሲ የሌላቸው ተቋማት ጋር የሚሠራ ከሆነ ስለ ድርጅቱ ሴፍጋርዲንግ ፖሊሲ አስመልክቶ ስምምነት እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡

የጥቃት አይነቶች፣ ደረጃዎች፣ ጥቃትን መጠበቅ፣ መከላከል፣ ሪፖርት ማድረግና ምላሽ አሰጣጥ፣ የሴፍጋርዲን ፖሊሲ ስታንዳርድ፣ የአስተማማኝ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አቀራረጽ፣ የአደጋ መቀነሻ ስልቶች፣ የመረጃ ማጋራት አስፈላጊነት፣ የግብረ መልስ አሰጣጥና የቅሬታ አፈታት መርሆዎች በሥልጠናው ከተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች የተወሰኑት ናቸው፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የተገኘው ልምድና ግንዛቤ ዩኒቨርሲቲው በሚቀርጻቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ላይ በቀጥታ ተግባራዊ ስለሚደረግ ሥልጠናው ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ሥልጠናው ለሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የሚሰጥበት ሁኔታ ቢኖር በተለይ ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ አካላትን ከጥቃት ለመጠበቅ የሚያስችል ግንዛቤ የሚፈጥር በመሆኑ ታቅዶ እንዲተገበርም ጠይቀዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
1.4K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:16:13
1.3K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:14:47 NOTICE

US Embassy is pleased to announce the application period of the 2023 Mandela Washington Fellowship for Young African Leaders Initiative, sponsored by the US Department of State, opened on August 16, 2022, and will close on September 13, 2022.

This is an opportunity for outstanding young leaders aged 25-35 from Ethiopia to hone their skills through academic coursework, leadership training and networking in the US. The US Embassy staff will conduct information session for all interested applicants on August 31, 2022 at 8:30 am in the morning.

You are invited to participate in the orientation which will be held at AMU Main Campus new hall near to the main gate.

Communication Affairs Directorate
1.3K viewsedited  15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:27:33
1.6K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ