Get Mystery Box with random crypto!

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትና ም/ፕሬዝደንቶች የ2015 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ቁልፍ የውጤት አመላካ | Arba Minch University

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትና ም/ፕሬዝደንቶች የ2015 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ቁልፍ የውጤት አመላካች (KPI) ላይ የውል ስምምነት ተፈራረሙ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ቁልፍ የውጤት አመላካች (KPI) ላይ ነሐሴ 20/2014 ዓ/ም ከዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዝደንቶች ጋር የውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ ወቅት እንደተገለጸው የዩኒቨርሲቲው የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ የጸደቀ ሲሆን የም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤቶች የዕቅድ ቁልፍ ተግባራትም በዚሁ ዕቅድ ተመሥርተው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በቀጣይ ዕቅዱን እስከ ባለሙያዎች ድረስ በማውረድና ውል በመፈራረም እንደሚሠራና በግለሰብ ደረጃ የሥራ አፈፃፀም ምዝና ሲደረግም በዚሁ መሠረት ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶበታል፡፡

በፕሮግራሙ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት፣ ም/ፕሬዝደንቶች፣ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች፣ ዳይሬክተሮችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት