Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-26 15:01:34
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለአዲስ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት አቆመ።

ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማትና ተቋማቱን የሚከፍቱ ባለሀብቶች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎችን እያዘጋጀ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በዚህም ከኅዳር 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት ማቆሙን በተቋሙ የፈቃድ እና ጥራት ኦዲት ም/ዋ/ዳይሬክተር ውብሸት ታደለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

አዲስ ለሚከፈቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት በማቆም ያሉትን የማጥራት ሥራዎች ላይ ትኩረት መደረጉን ኃላፊው ይገልጸዋል።

በተያዘው ዓመት አዲስ ፈቃድ የመስጠት ሥራ ይጀምራል የሚል እምነት እንደሌላቸው ኃላፊው ጠቁመዋል።

@minster_of_education
2.0K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 15:01:18
#SPHMMC

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በሕክምና የዲግሪ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁና የቅበላ መስፈርቶችን ያሟላችሁ የመግቢያ ፈተና እሁድ የካቲት 19/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ኮሌጁ አሳውቋል።

የመፈተኛ ቦታ ➧ መድኃኒአለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ተፈታኞች የማንነት መለያ መታወቂያ፣ እስኪቢርቶ፣ እርሳስ፣ መቅረጫ እና ላጲስ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

ለበለጠ መረጃ፦

https://sphmmc.edu.et/2023/02/23/1842/

@minster_of_education
2.1K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 15:01:17
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጆርናል ማሳተም ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው ‘ኮተቤ የትምህርት ጆርናል’ ( KOTEBE JOURNAL OF EDUCATION, KJE ) የተሰኘ ጆርናል ለማስጀማር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳውቋል።

ተቋሙ ጆርናሉን ለማስጀመር የሚያስችሉ ፖሊሲና መመሪያን አስገምግሟል፡፡

ጆርናሉ የተቋሙ ምሁራን ጥናትና ምርምሮቻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ባሻገር ለሦሥተኛ ወገን ተጠቃሚ የሚያደርሱበት ድልድይ እንደሚሆን የዩኒቨርሲቲው
ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

@minster_of_education
2.0K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 15:00:42
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሀላባ ቁሊቶ የርቀትና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ማዕከል በይፋ አስጀምሯል።

ማዕከሉ ከመማር ማስተማሩ በተጨማሪ የሀላባ ማህበረሰብ ቋንቋ፣ ባህል እና የጋራ እሴቶችን በጥናትና ምርምር አስደግፎ ለማሳደግ እንደሚሠራ
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሀላባ ቁሊቶ ማዕከልን ጨምሮ ስምንት የተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ማዕከላት አሉት።

@minster_of_education
2.4K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 04:13:25
#AASTU

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ  የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 20/2015 ዓ.ም ብቻ መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመኝታ ቤት ምደባችሁንና መታወቂያ ቁጥራችሁን ለማወቅ➧

http://www.aastu.edu.et/freshmaninfo/ 

ማስፈንጠሪያውን ከተጫናችሁ በኋላ በሬጅስትሬሽን ቁጥሩ ምትክ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መፈተኛ ቁጥራችሁን አስገቡ፡፡

የአድሚሽን ቁጥራችሁ በዜሮ የሚጀምር ከሆነ የመጀመሪያዋን ዜሮ በመተው ሌሎቹን ቁጥሮች በማስገባት መታወቂያ ቁጥራችሁንና የመኝታ ቤት ድልድላችሁን ማወቅ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

@minster_of_education
3.1K views01:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 04:13:14
የምርምር እና የፈጠራ ሥራዎቻችሁን ያቅርቡ!

የትምህርት ሚኒስቴር በቀጣይ ወር በሚያዘጋጀው ሀገር አቀፍ አወደ ጥናት እና አውደ ርዕይ ላይ የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ተቋማት የምርምር እና የፈጠራ ውጤቶቻችሁን እንድታቀርቡ ጋብዟል፡፡

ሚኒስቴሩ ከፌደራል የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ‘’የኢትዮጵያ ምርምር ስነ-ምህዳር፣ ተግዳሮቶች እና ተስፋዎች’’ በሚል ጭብጥ ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የምርምር አውደ ጥናት እና አውደ ርዕይ ከመጋቢት 28-30/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ያካሂዳል፡፡

የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሚታደሙበት መድረክ፤ የምርምርና ፈጠራ ሥራዎች በተመረጡ የከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ተቋማት ለዕይታ ይቀርባሉ፡፡

ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው የምርምር እና የፈጠራ ውጤቶች ያሏችሁ ተቋማት እስከ የካቲት 25/2015 ዓ.ም ድረስ የምርምር ፈጠራውን ስም፣ የተሰራበትን ተቋም እና ጊዜ እንዲሁም የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በጽሑፍ እና በምስል በማስደገፍ ለ tesfamariam.shimekit@ethernet.edu.et መላክ ትችላላችሁ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ➧ 0912887336

@minster_of_education
2.9K views01:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 04:13:07
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 9ኛ ሀገር አቀፍ አወደ ጥናት ማካሄድ ጀምሯል።

“ምርምር ለልማት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው አወደ ጥናት፤ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው አወደ ጥናት ላይ 45 ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።

@minster_of_education
2.6K views01:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 04:12:37
#MoE

106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ተካተዋል፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡

የ Remedial ፕሮግራሙ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፕሮፌሰሮች ኮሚቴ በማዋቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት የትምህርት አይነት ይዘቶችን መለየቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዘኛ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ የትምህርት አይነቶችን የሚወስዱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ እንግሊዘኛ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ትምህርት አይነቶችን እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ይዘቶቹን መሰረት አድርጎ በተቋማት የሚዘጋጅ (ከ30 በመቶ) እና በማዕከል የሚዘጋጅ (ከ70 በመቶ) የሚያዝ ፈተና በመፈተን በድምሩ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚያገኙ ተማሪዎች መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ይችላሉ ብለዋል፡፡

@minster_of_education
2.9K views01:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:33:47
#Update

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡ ተማሪዎች የካቲት 15 እና 16/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ፦

➧ በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣
➧ በላምበረት መናኸሪያ፣
➧ በአቃቂ መናኸሪያ እና
➧በአስኮ መናኸሪ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡

@minster_of_education
1.6K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:33:33
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከ635 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 10 ተማሪዎች የላፕቶፕ ሽልማት ሰጥቷል።

ተሻሚዎቹ ስምንቱ ከየይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲሆኑ ሁለቱ ከደሴ ከተማ ትምህርት ቤት መሆናቸው ተገልጿል።

ለሽልማቱ ዩኒቨርሲቲው ከ8 መቶ 50 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጓል።

በተመሳሳይ ከ600 እስከ 634 ውጤት ላስመዘገቡ 19 ተማሪዎች የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቦርድ እና የደሴ ከተማ አስተዳደር በጋራ ለእያንዳንዳቸው ተማሪዎች የ6 ሺህ ብር ሽልማት ሰጥተዋል።

የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ላስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራን እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

@minster_of_education
1.5K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ