Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-02-28 14:09:25
ክቡር ኮሌጅ ለአራት ወራት የሚቆይ የአቅም ማሻሻያ መርሃ ግብር (Remedial Program) ለመስጠት ምዝገባ ጀምሯል!

ትምህርቱ የሚሰጠው ብቃት ባላቸው መምህራን እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አሰጣጥ ልምድ ባለው ተቋም በመታገዝ ነው፡፡

ለአራት ወራት ተምረው ፈተናውን ካላለፉ የከፈሉት ብር ሙሉ ተመላሽ ይደረግልዎታል!

Natural Science:


English, Mathematics, Biology, Chemistry and Physics.

Social Science:

Mathematics, English, Geography and History.

+ Study and Test-taking Skills Training

ምዝገባ ጀምረናል! ክቡር ኮሌጅ!

Website: https://kibur.net

አድራሻ:- መካኒሳ /ጀሞ ሚካኤል ከአፍሪካ ህንፃ አጠገብ

0113854042 / 0904848586

Telegram: https://t.me/kiburcollege
Facebook: https://www.facebook.com/kiburcollege
2.3K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 14:09:24
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትምህርት ዘርፉን የተመለከቱ የተለያዩ አዋጆችና ደንቦች አጽድቋል፡፡

የጸደቁት አዋጆችና ሰነዶች፦

• የትምህርትና ስልጠና ረቂቅ ፖሊሲ፣

• የዩኒቨርሲቲ አውቶኖሚ (ራስ ገዝ) የሚደነግግ አዋጅ፣

• በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶችን ተግባር፣ ኃላፊነትና ጥቅማጥቅም ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ፣

• የከፍተኛ ትምህርት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የምርምር ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ አዋጅ።

በምክር ቤቱ የጸደቁት አዋጆችና ደንቦች ለትምህርት ዘርፉ ዕድገት ቁልፍ ሚና ያላቸው መሆኑን የትምህርት ሚኒሰትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

በቀጣይ ለጸደቁት አዋጆችና ደንቦች ማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች በማዘጋጀት ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተገልጿል።

@minster_of_education
2.1K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 14:08:51
#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት አዘጋጅቷል።

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዘገባ የካቲት 22 እና 23/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው መግለጹ ይታወቃል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አውቶብሶች መነሻ ቦታዎች፦

➧ አዲስ አበባ መርካቶ መናኸሪያ፣

➧ አዲስ አበባ ቃሊቲ መናኸሪያ፣

➧ አዳማ ፍራንኮ ሆቴል አካባቢ፣

➧ አዳማ ፒኮክ እና ሚጊራ መናኸሪያዎች።

@minster_of_education
2.1K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 14:08:45
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ለዶ/ር ነጋ አሰፋ እና ለዶ/ር ገላና አመንቴ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት፤ ቦርዱ ለዶ/ር ነጋ አሰፋ በእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም ለዶ/ር ገላና አመንቴ በፊዚክስ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷቸዋል፡፡

@minster_of_education
2.1K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 14:08:44
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ መደበኛ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 20 እስከ 22/2015 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወቃል።

መንግስት ዘንድሮ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች
ምደባ ካደረገባቸው 15 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺህ 100 በላይ ተማሪዎች በቀዳሚነት የመረጡት ዩኒቨርሲቲ ነው።

@minster_of_education
2.4K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 20:55:08
#MoE

የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት ተከታዮቹን አማራጮች ይጠቀሙ፦

Website:

https://placement.ethernet.edu.et

SMS: 9444

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ እንደማያስተናግድ አሳውቋል።

@minster_of_education
2.3K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 15:03:56
በጣልያን የሙሉ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ ይሁኑ!

የጣልያን መንግስት በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ሙሉ ስኮላርሺፕ ሰጥቷል።

የስኮላርሺፑ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ በ @rasbitwededservices ያነጋግሩን።

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ፦

https://t.me/+f1BRMl9qxWYxYjdk

ለተጨመሪ መረጃ፦

0964826768 / 0944442700

አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ሽመክት ህንጻ፣ 10ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 08
@minster_of_education
3.0K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 15:03:23
#ArbaMinchUniversity

በ2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ቀን የካቲት 22/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ጊዜ ➧ የካቲት 23 እና 24/2015 ዓ.ም

ትምህርት የሚጀምረው ➧ የካቲት 27/2015 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣

➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣

➧ የ10 እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣

➧ ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ (4)፣

➧ የሌሊት አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ።

የመመዝገቢያ ቦታ ➧የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፤ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በጫሞ ካምፓስ

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@minster_of_education
2.7K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 15:03:13
#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት ተሹሞለታል።

ባይሳ ለታ (ዶ/ር) የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት አወዳድሮ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ በጥቅምት 2015 ዓ.ም አውጥቶ የነበረ መሆኑ አይዘነጋም።

አዲሱ ተሿሚ ተቋሙን ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት እንደሚመሩ ይጠበቃል፡፡

@minster_of_education
2.3K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 15:02:28
#KARVARD_COLLEGE

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ላጠናቀቃችሁና በሪሚዲያል / የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለምትሳተፉ ተማሪዎች በሙሉ!

ካርቫርድ ኮሌጅ በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም የተካተቱ ተማሪዎችን በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማኅበራዊ ሳይንስ መስኮች ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ካርቫርድ ኮሌጅ ሙሉ ዕውቅና ያለው!

ምዝገባ ጀምረናል!

ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የመቁረጫ ነጥብ የምታሟሉ ተማሪዎች መመዝገብ ትችላላችሁ።

ለበለጠ መረጃ፦

       0933686868 / 0903676869

አድራሻ፦  አዲስ አበባ፣ ከፒያሳ ወደ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ዳሞት ህንፃ
2.2K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ