Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-04-06 07:22:36
የፈረንሳይኛ ቋንቋ መማሪያ ማዕከል በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለመክፈት ውይይት ተደርጓል።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ የተመራ ልዑክ ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር ተወያይቷል።

ዩኒቨርሲቲውን ከሁለት ዓመት በኋላ በድጋሜ ሥራ ለማስቀጠል ኤምባሲው ሊያደርገው በሚችለው ድጋፍ ላይ ውይይት ተደርጓል።

የዩኒቨርሲቲውን የተማሪዎች ጤና ማዕከል መልሶ ለማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል።

@Minster_of_education
1.6K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 07:22:18
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምስለ ፍርድ ቤት ክርክር (Moot Court ) እያካሄደ ነው።

ከ3ኛ እስከ 5ኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የምስለ ፍርድ ቤት ክርክር እያደረጉ እንደሆነ የሕግ ትምህርት ቤት ዲን ቶሎሳ በዳዳ ገልጸዋል።

ክርክሩ እስከ ሐሙስ መጋቢት 28/2015 ዓ.ም ለተከታታይ ሦሥት ቀናት ይካሄዳል።

@Minster_of_education
1.4K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 07:21:48
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በሦሥት የክልል ከተሞች ያቋቋማቸውን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በቅርቡ ሥራ ያስጀምራል፡፡

ባለሥልጣኑ በአምስት የክልል ከተሞች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለመክፈት በሂደት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በድሬዳዋ፣ ሀዋሳ እና ባህር ዳር ከተሞች እየተቋቋሙ የሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምሩ የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቸሩጌታ ገነነ በተለይ ለቲክቫህ ተናግረዋል።

ይህም ባለሥልጣኑ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር ለማጠናከርና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለው ገልጸዋል።

ባለሥልጣኑ በተጨማሪም ደሴ እና ጅማ ከተሞች ላይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ለመክፈት እየሠራ ይገኛል።

@Minster_of_education
1.4K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 07:21:24
ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለሁዋዌ የአይሲቲ ዓመታዊ ውድድር የመጨረሻ ዙር አልፈዋል፡፡

15 ተማሪዎች 20 የአፍሪካ አገራት በተወከሉበት ቀጣናዊ የአይሲቲ ውድድር ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከነዚህም ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና ለሚካሄደው የመጨረሻው ዓለም አቀፍ ውድድር ማለፋቸው ታውቋል፡፡

ስድስቱ ተማሪዎች ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መሆናቸውን ሁዋዌ አሳውቋል፡፡

ተማሪዎቹ ከኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ፣ ከኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ከሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ ከኮሚዩኒኬሽን ኢንጂነሪንግ እና ከአይሲቲ ትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ ናቸው።

@Minster_of_education
1.6K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 00:09:23
ሩሲያዊው ጠፈርተኛ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ልምዱን አካፍሏል፡፡

ለ185 ቀናት በጠፈር ላይ የቆየዉ ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ሰርጌ ሰቨርችኮቭ፤ በህዋ ሳይንስ ያካበተውን ዕውቀትና ልምድ ለኢትዮጵያውያን ምሁራንና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጋርቷል፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ፣ በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በተዘጋጀው መድረክ፤ ጠፈርተኛው ልምዱን አጋርቷል።

ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ከጠፈር ላይ የወሰደውን የዳሎል ምሥል ትላን በአዲስ አበባ ተገኝቶ ለኢትዮጵያውያን አስረክቧል።

@Minster_of_education
1.1K views21:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 00:08:48
በድረ-ገጹ ላይ ለመግዛት የሚፈልጉትን ዕቃዎች መፈለግ ይችላሉ

https://www.ishururu.com

በተጨማሪም የምርቶቹን የቅርብ ጊዜ ዋጋ ማግኘት ይችላሉ።

Our Customer Support Team is on hand to answer any of your questions.

Shop with us today @ ishururu.com and get the best experience!

If you want to stay on Telegram to shop join our Telegram Channel @ishururu
1.0K views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 00:08:32
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሚያሳትመው "EAJVAS" ጆርናል ብሔራዊ ዕውቅና አጊኝቷል።

East African Journal of Veterinary and Animal Sciences የተሰኘው ጆርናሉ ፤ ለሦሥት ዓመት የሚቆይ ዕውቅና በትምህርት ሚኒስቴር ተሰጥቶታል።

ጆርናሉ በሦሥተኛ ዙር ዕውቅና ከተሰጣቸው 15 የአገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች አንዱ መሆን ችሏል።

ጆርናሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘ አምስተኛ የተቋሙ ጆርናል መሆኑ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@Minster_of_education
894 views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 00:08:23
ነጻ የትምህርት ዕድል!

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ወይንም Menschen für Menschen Foundation ስር የሚተዳደረው የሐረር ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን ብቁ የሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመጋቢተ 18 እስከ 30/2015 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን አሳውቋል።

የመመዝገቢያ መስፈርት፦

ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም ያወጣውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት የምታሟሉ ወይም በአገር አቀፍ ፈተና 50 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፡፡ 

ምዝገባ የሚፈጸመው፦

➧ በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት፣
➧ ሐረር በኮሌጁ ቅጥር ግቢ፣
➧ የድርጅቱ ፕሮጀክት ጽ/ቤቶች በሚገኙባችው፣
➧ በድረ-ገጽ http://www.mfmattc.edu.et

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦

በስልክ ቁጥር 0256663738 / 0256661139 ወይም 0114714579 ይደውሉ።

(ሰዎች ለሰዎች ድርጅት Menschen für Menschen Foundation)
995 views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 00:08:11
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የስፔስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ASTU-X2 የተሰኘ የድሮን ፕሮቶታይፕ አበልጽጓል።

የተሳካ የበረራ ሙከራ ያደረገው ድሮኑ፤ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህ ቀደም በኮርያ መንግስት ልገሳ የተገኙ ግብዓቶችን በመገጣጠም የተሠራ ASTU-X1 የተሰኘ ድሮን የበረራ ሙከራ ማድረጉንም የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ፕ/ር ሆንግዩል ፓይክ ገልጸዋል።

ለተለያዩ የልማት ሥራዎች የሚውሉ ድሮኖችን የማበልጸጉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@Minster_of_education
801 views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 00:08:00
አዲስ የስቴም ማዕከል በራያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተመርቋል።

ማዕከሉ በ STEMpower, SmartAID እና DHL ትብብር የተቋቋመ ነው።

ማዕከሉ አነስተኛ ሰው-አልባ በራሪ ሄሊኮፕተርሮች (ኳድኮፕተሮች)፣ 3-D ፕሪንተሮች፣ ስማርት ኮምፒውተሮች እንዲሁም ኤሌክትሮኒክ ላቦራቶሪዎች ተሟልቶለታል።

በራያ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመው ማዕከል፤ በኢትዮጵያ የተከፈተ 57ኛ የስቴም ፓወር ማዕከል ነው።

@Minster_of_education
820 views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ