Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-02-22 16:33:16
ክቡር ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው ዕድሜያቸው ከ 17-21 የሆኑ ተማሪዎችን ያሳተፈ ክቡር ሃካቶን (Kibur Hackathon) የማጠቃለያ  ፍፃሜ ውድድር ተካሂዷል።

ውድድሩ መሰረታዊ የኮዲንግ ቴክኖሎጂና የፈጠራ ክህሎትን በመጠቀም ማህበረሰብ ተኮር ችግሮችን መፍታትን አላማው ያደረገ ነው።

ለውድድሩ መስፈርቱን ያሟሉ ከ100 በላይ ተወዳዳሪ ቡድኖች ተመዝግበው የነበረ ሲሆን ከተለያዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ 11 ቡድኖች ለፍጻሜ ደርሰዋል።

በመጨረሻም በውድድሩ ከ1 እስከ 3 የወጡ አሸናፊዎች የተለዩ ሲሆን አንደኛ ለወጡት 10 ሺህ ብር፣ ሁለተኛ ለወጡት 5 ሺህ ብር እንዲሁም ሦሥተኛ ለወጡት 3 ሺህ ብር ከሜዳሊያ ጋር ተሸልዋል።

ለጠቅላላ ተወዳዳሪዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት እኖደሚሰጥ ኮሌጁ ገልጿል።

@minster_of_education
1.3K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:33:02
#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 190 ተማሪዎች አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 131 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 27 በህክምና ስፔሻሊቲ እና 2 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎችን አስመርቋል።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ 30 ተማሪዎችንም በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።

@minster_of_education
1.1K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:32:49
#HawassaUniversity

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ አምጥታችሁ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን ከየካቲት 20 እስከ 26/2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ተቋሙ ገልጿል።

የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ የካቲት 27 እና 28/2015 ዓ.ም በዋናው ግቢ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣

➧ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው፣

➧ጉርድ ፎቶግራፍ (4)

➧ የሌሊት አልባሳት

➧ የስፖርት ትጥቅ

የመልሶ ቅበላ አመልካች ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የካቲት 29 እና 30/2015 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል፡፡

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@minster_of_education
1.1K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:32:32
#BahirDarUniversity

በ2015 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 20 እስከ 22/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣

➧ጉርድ ፎቶግራፍ (4)

➧ የሌሊት አልባሳት

➧ የስፖርት ትጥቅ

የአንደኛ ዓመት አንደኛ ሴሚስተር የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ማመልከቻ ጊዜ የካቲት 24/2015 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

(ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል።)

@minster_of_education
1.1K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:32:08
#DebreMarkosUniversity

በ2015 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ የካቲት 20 እስከ 21/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣

➧ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣

➧ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣

➧ 3×4 ፎቶግራፍ (8)፣

➧ የሌሊት አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

የሬመዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@minster_of_education
1.1K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:31:56
#HaramayaUniversity

በ2015 ዓ.ም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 24 እስከ 26/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣

➧ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣

➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣

➧ ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ (6)፣

➧ የሌሊት አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ።

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@minster_of_education
1.1K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:31:44
ተራዝሟል!

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የምታመለክቱ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ እስከ ነገ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ተራዝሟል።

በመሆኑም በቀረው አንድ ቀን የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን አማካይነት እንድታስተካክሉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

በሬመዲያል ፕሮግራም ያልተካተቱ ዩኒቨርሲቲዎች፦

➧ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
➧ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና
➧ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

@minster_of_education
1.1K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:31:28
#InjibaraUniversity

በ2015 ዓ.ም በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 27 እስከ 28/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣

➧ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣

➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣

➧ 3×4 ፎቶግራፍ (4)፣

➧ የሌሊት አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ።

የአንደኛ ዓመት አንደኛ ሴሚስተር የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ለመልሶ ቅበላ ማመልከት እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

@minster_of_education
1.1K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:31:11
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 5 ሺህ 100 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲተው በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ 5 ሺህ 100 ተማሪዎችን ከዛሬ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይቀበላል፡፡

ከአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ መካከል 3 ሺህ 51 በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተመደቡ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ሽብሩ ተመስገን (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በ11 ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸው ይታወቃል፡፡

@minster_of_education
1.4K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 06:15:27
#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 190 ተማሪዎች አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 131 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 27 በህክምና ስፔሻሊቲ እና 2 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎችን አስመርቋል።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ 30 ተማሪዎችንም በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።

@minster_of_education
2.4K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ