Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 38

2022-07-14 23:50:53
ወጣቱ የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ

ወጣቱ የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ ትንሳኤ አለማየሁ አሊ በ2022 ተሰፋ ከተጣለባቸው 30 የህዋ መሪዎች አንዱ ተብሏል።

ትንሳኤ አለማየሁ የዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ፌደሬሽን በዚህ ዓመት Emerging Space Leaders ብሎ ከመረጣቸው 30 ተመራማሪዎች አንዱ ሆኗል።

ይህም መስከረም ላይ ፓሪስ በሚደረግ ዓለም አቀፍ የህዋ ጉባኤ እንዲሳተፍና ሁለት የምርምር ጽሁፎች እንዲያቀርብ እድል የሚፈጥርለት መሆኑን ለVOA ተናግሯል።

ወጣቱ ተመራማሪ የኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ ማህበር አባል እና የዓለም ዐቀፉ የህዋ ጄነሬሽን አማካሪ ም/ቤት (SGAC) የአፍሪካ ቀጣናዊ አስተባባሪ ነው።

ወጣቱ ከህዋ ሳይንስ ጋር የተያያዙ በርካታ መድረኮች ላይ በመሳተፍ በጉዳዩ ዙሪያ የማህበረሰብ ግንዛቤና ተሳትፎን በኢትዮጵያና አፍሪካ ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል።

የ24 ዓመቱ ትንሳኤ በሜካኒካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አጊኝቷል።

ትንሳኤ ለህዋ ኢንዱስትሪ ባለው ራዕይ እና ለዘርፉ ላደረገው አበርክቶ፤ Space In Africa በተባለ ተቋም በ2021 እድሜያቸው ከ30 በታች የሆኑ 10 ተሸላሚዎች መካከል አንዱ እንደነበር ይታወሳል።

ትንሳኤ 'ሳተላይትን መሠረት ያደረገ የሠብል ምርት አያያዝ' ምርምር ከ'SGAC' ጋር ሲሠራ ቆይቷል።

https://t.me/minster_of_education
1.3K views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:50:38
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ (ስቴም) ማዕከል የክረምት ስልጠና ለመከታተል ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የመግቢያ እና ምዝገባ ቀን ሐምሌ 12/2014 ዓ.ም
መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በመሆኑም በዩኒቨርሲቲ 'ኦዳያአ' ግቢ ስቴም ማዕከል (ህንፃ ቁ. 616) በመገኘት ምዝገባ አድርጉ ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

• ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
• የሌሊት አልባሳት (ከዲላ ከተማ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች)

https://t.me/minster_of_education
1.3K views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:50:21
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምሀርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 238 ተማሪዎች ቅዳሜ ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሃ ግብር በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 163ቱ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ብርሀኑ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ 9ኛ ዙር ሰልጣኞቹን የሚያስመርቅ ሲሆን 369ኙ ሴት ተማሪዎች ናቸው።

https://t.me/minster_of_education
1.3K views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:50:06
#ደምቢ_ዶሎ_ዩኒቨርሲቲ

በ2014 ዓ.ም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አድስ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነዉ ሐምሌ 18 እና 19/2014 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

https://t.me/minster_of_education
1.3K views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:49:43
የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተሰምቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፤ በኮቪድ -19 እና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት በተቀመጠለት ጊዜ አለመጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

በመሆኑም የ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ከሐምሌ 20 እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲቆይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲዎቹ ሐምሌ 20 እና 21/2014 ዓ.ም ምዝገባ በማከናወን፥ ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም መጀመር እንዳለባቸው ተገልጿል።

ለተማሪዎቻቸው አስቀድመው ጥሪ ያደረጉ ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ማስተካከያ እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ችሏል።

https://t.me/minster_of_education
1.3K views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:49:17
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ.ም በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ
• በግንባታ ቴክኖሎጂ እና አስተዳደር
• በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ
• በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
ለመማር በኦንላይን ላመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና ሐምሌ 11/2014 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ለፈተናው የተመረጡ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ እና በድረ-ገጽ መመልከት ይቻላሉ ተብሏል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )

https://t.me/minster_of_education
1.3K views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:49:17
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ.ም በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ
• በግንባታ ቴክኖሎጂ እና አስተዳደር
• በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ
• በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
ለመማር በኦንላይን ላመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና ሐምሌ 11/2014 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ለፈተናው የተመረጡ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ እና በድረ-ገጽ መመልከት ይቻላሉ ተብሏል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )

https://t.me/minster_of_education
1.4K views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:49:03
በሶማሌ ክልል ከ25 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዚህ ዓመት ይወስዳሉ።

ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በክልሉ ከ25 ሺህ 140 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አብዱላሂ አደን ተናግረዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ማጭበርበር ለመከላከል እንደሚያስችል ገልጸዋል። #SMMA

https://t.me/minster_of_education
1.7K views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:13:35 A Concise Introduction to Logic
13th Edition (Latest Edition)
#logic #freshman #book

Freshman ተማሪዎች ከሆናችሁ ይሄ መፅሃፍ በጣም ያስፈልጋችኋል። Course module ላይ እንደ ማጣቀሻ (Reference) የተወሰደ እና በመምህራን ዘንድ ልዩ ማረጋገጫ የተሰጠው መፅሃፍ ነው።

በአጭሩ የዚህ መፅሃፍ ማስታወሻዎች በደንብ ከገቧችሁ እና ሁሉንም መልመጃዎች ከሰራችሁ Logic አያሳስባችሁም። A+++

አንዳንድ ጊዜ መምህራን ጥያቄዎችን ከዚህ መፅሃፍ ላይ ግልብጥ አድርገው ያመጣሉ።

Join and Share
3.8K views11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:13:23 A Concise Introduction to Logic
13th Edition (Latest Edition)

ANSWER KEY
#logic #freshman #book

ZIP ፋይል ነው። በZ-archiver extract ማድረግ ትችላላችሁ።

ለጊዜው እስከ Chapter 5 ብቻ ነው ያለው። ሌሎቹን በቅርብ ጊዜ ለማሟላት እንሞክራለን።

Join and Share
3.3K views11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ