Get Mystery Box with random crypto!

MINSTER OF EDUCATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION M
የቴሌግራም ቻናል አርማ minster_of_education — MINSTER OF EDUCATION
የሰርጥ አድራሻ: @minster_of_education
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.41K
የሰርጥ መግለጫ

Hello, dear and respected members of my channel, the main purpose of opening this channel is to share with you the knowledge that I have learned in my working life. In addition, I will show you how to make money online

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 39

2022-07-10 06:16:22
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሦሥተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የሁለተኛ ሴሚስቴር ምዝገባ ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም
እንደሚከናወን አሳውቋል።

በመሆኑ በተገለጸው ቀን በተቋሙ በመገኘት ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

https://t.me/minster_of_education
3.9K views03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 06:15:08
የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ/በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡን ሙሉ ለሙሉ አውቶሜት ለማድረግ ከቻይና መንግስት ጋር እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል።

ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በርካታ ታብሌት ኮምፒዩተሮች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በኮቪድ-19 ምክንያት አምራች ድርጅቱ ኮምፒዩተሮቹን በተያዘለት ጊዜ ማምረት አለመቻሉን ገልጸዋል።

ኮምፒዩተሮቹ በተያዘላቸው ጊዜ ከደረሱ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የቀጣይ ዓመት ፈተና ኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

ታብሌቶቹ በሚጠበቀው ጊዜ ካልደረሱ፥ መንግስት የፈተና ስርቆት የሚቀነስበት የተሻለ አሰራር በመከተል ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።

https://t.me/minster_of_education
3.6K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 06:13:38
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም ያከናውናል።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዕለቱ ያስመርቃል።

የመማር ማስተማር ሥራውን በ2010 ዓ.ም የጀመረው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፤ ዘንድሮ 3ኛ ዙር ሰልጣኞቹን ያስመርቃል።

https://t.me/minster_of_education
3.0K views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 06:13:20
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የጤና ዘርፍ ተቋማዊ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቷል።

ይህም ዩኒቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የያዘውን ግብ ለማሳካት ያግዘዋል ተብሏል።

ፍኖተ ካርታው በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ አካላት ከተገመገመ በኋላ እንዲጸድቅ ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ተመርቷል።

“የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ” የሆነው ተቋሙ፤ በ2022 ዓ.ም "ቴክኖሎጂ መር የግብርናና የጤና ልህቀት ማዕከል"ለመሆን እየሠራ ይገኛል።

https://t.me/minster_of_education
3.0K views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 06:12:38
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሃ ግብር ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

ዩኒቨርሲቲው የነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 11 እና 12/2014 ዓ.ም ይከናወናል ማለቱ አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ ምዝገባው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መደረጉን በመግለጽ፤ ተማሪዎች ሌላ ጥሪ እስከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

https://t.me/minster_of_education
3.2K views03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ